Main fundraiser photo

ኑ !ስደታቸው በክረምትና በሰንበት ለሆነባቸው ወገኖቻችን እንድረስላቸው !

Tax deductible
ኑ !ስደታቸው በክረምትና በሰንበት ለሆነባቸው ወገኖቻችን እንድረስላቸው !
 
“እኛ አባቶቻችሁ በስቃይ ውስጥ መሆናችንን አስባችሁ ድረሱልን”
የተፈናቃይ ካህናት የሲቃ ድምጽ
***
“አንተ ልትበላው ያልፈለግኸው እንጀራ የተራቡት ሰዎች እንጀራ ነው። በቁም ሳጥንህ ውስጥ ሰቅለህ የተውከው ልብስ ዕርቃኑን የሆነው ሰው ልብስ ነው። የማታደርጋቸው ጫማዎችህ ባዶ እግሩን የሚሔድ ሰው ጫማዎች ናቸው። የቆለፍክበት ገንዘብ የደሃው ገንዘብ ነው። የማትፈጽማቸው የቸርነት ሥራዎች ሁሉ ኢፍትሐዊ ድርጊቶችህ ናቸው”
ቅዱስ ባስልዮስ
ማኅበረ ቅዱሳን በሀገራችን እየደረሰ ባለው ማኅበራዊ ቀውስና ሃይማኖታዊ ጥቃቶች ሰለባ የሆኑ መምህራን፣ ካህናት፣ ምእመናንና ልዩ ልዩ አካላት ፕሮጀክት እየቀረጸ በጎ አድራጊ ምእመናንና ተቋማትን በማስተባበር ባለፈው 2 ዓመታት በአርሲ፣ በሻሸመኔ፣ በሐረር፣ በመተከል፣ በአጣየ፣ በትግራይና በሌሎችም የሀገራችን ክፍል ለሚገኙ ተፈናቃዮች የአልባሳት፣ የምግብ እና መሠል አስቸኳይ ድጋፎችን በስፋት ሲያደርስ ቆይቷል። አሁንም ድጋፉን አጠናክሮ ቀጥሏል።
በዚህ ወቅት በሰሜኑ ሀገራችን ክፍል ባጋጠመው ጦርነት ተፈናቅለው በደሴ ዙሪያ ለሚገኙ ተጎጅዎች የመጀመሪያ ዙር አስቸኳይ ድጋፍ አድርጓል። በቀጣይም ተጎጅዎች በሚገኙባቸው ቦታዎች ሁሉ ደርሶ የነፍስ አድን ሥራዎችን ለማከናወን የእናንተን የተለመደ የድጋፍ ትብብር እየጠየቅን ለወገኖቻችን እንድረስላቸው ስንል የአስቸኳይ ድጋፍ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
 

Donations 

    Organizer

    Mahibere Kidusan
    Organizer
    Silver Spring, MD
    Mahibere Kidusan
    Beneficiary

    Your easy, powerful, and trusted home for help

    • Easy

      Donate quickly and easily

    • Powerful

      Send help right to the people and causes you care about

    • Trusted

      Our Trust & Safety team works around the clock to keep our community safe