Main fundraiser photo

ለመሎ ላሃ የሃይማኖት እስረኞች የድጋፍ ጥሪ

Donation protected
ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የኾነባቸው ብዙ አውራጃዎች በሀገራችን ኢትዮጵያ ተፈጥረዋል። ከእነዚህ መካከል በጋሞ ጎፋ ዞን በመሎ ኮዛ ወረዳ የምትገኘው ላሃ አንዷ ናት። በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት ትገኛለች። 

የወረዳው አስተዳደር ለ፶፫ ዓመታት የጥምቀተ ባሕር እና የደመራ ቦታ አድርጋ ስትጠቀምበት የነበረውን የቤተክርስቲያን ይዞታ በመንጠቅ ለአውቶቡስ መናኸሪያ አደረገው። ከ፳፻ (2000)ዓ.ም. ጀምሮ ሙከራ ሲያደርግ የነበረ ቢኾንም በኦርቶዶክሳውያኑ ተጋድሎ ተከብሮ እስከ ፳፻፲፩ (2011) ዓ.ም. ቆይቷል። ፳፻፲፩ ዓ.ም. ላይ ግን በኃይል ነጥቆ ተቆጣጠረው። 

ወቅቱ በሲዳማ የ፲፩-፲፩-፲፩ (11-11-11) ቀጠሮ የተያዘበት ነበር። በሲዳማ አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ ክርስቲያኖች ሲታረዱ የላሃ ደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያም የገፈቱ ቀማሽ ኾነ። በዚያው ዕለት እዚያ ሲነድድ እዚህ የጨሰበት ምክንያቱ ግልጽ ነው። የፖለቲካ ጥያቄያቸው መዳረሻ ከኦርቶዶክሳውያን ነፃ ቀጠና መመሥረት ከኾነ ሰነበተ። 

ሕዝበ ክርስቲያኑ የላሃ አስተዳደር የወሰደውን ሕገወጥ ሥራ ባለመቀበሉ የተለያዩ ሰላማዊ የይመለስልን ጥያቄ ሲያቀርብ ቆይቷል። ከክልሉ ባለ ሥልጣናት እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ ቤተ መንግሥት ጩኸታቸውን አሰምተዋል። ጥቃቅኖቹን ፈርዖኖችን ግን የሚነቀንቅ አልኾነም። 

ይዞታችን ለምን ይነካል? ካሉት መካከል ዋኖች ያሏቸውን መርጠው ፈርዖኖቹ በ፳፪ (22) ክርስቲያኖች ላይ እስር ፈጸሙ። ከ፩ ዓመት በላይ ሰብአዊ አያያዝ በጎደለው ሥርዓት የዋስትና መብታቸውን ገፍፎ ሲያንገላታቸው ከረመ። ፳፪ቱም ወንጀለኛ ተባሉ። ኦርቶዶክስ ኾኖ መብት መጠየቅ ያልተጻፈ ወንጀል ነዋ። በ፲፩ዱ ላይ ከ፯-፱ (7-9) ዓመት እስራት ከገንዘብ ክፍያ ጋር ፈረደባቸው። በ፲፩ዱ ደግሞ የገንዘብ ክፍያ ጫነባቸው። 

ኦርቶዶክስ ስትኾን ካለ ኃጢአትህ ትከሰሳለህ፣ ባይኖርህም የገቢ ምንጭ ትደረጋለህ። ከፍተኛው የአንድ ሰው ቅጣት ፴ሺ (30,000.00) ብር ነው። አንድ ዓመት ሙሉ ከሥራ ውጭ አክርሞ ፴ሺ ክፈል ማለት ምንድን ነው ትርጉሙ?  አማርሮ ከሀገር እንዲሰደዱ የተቀየሰ ስልት መኾኑ ነው። 

ከጀርባቸው ብዙ ቤተሰቦች አሉ። ከታሳሪዎቹ አብዛኛዎቹ የቤተሰቡ ብቸኛ ጥቂቶቹ ደግሞ ዋነኛ ገቢ ምንጭ ነበሩ። ግን ታሰሩ። 

✤ ቤተሰቦቻቸውስ እንዴት ይሁኑ? 
 
✤ በምን አቅማቸው ጠበቃ ያቁሙ?
 
✤ የተከሰሱትስ ለእኛ ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ብለው አይደለም ወይ?

፳፪ቱ በአጠቃላይ የሚረዱ የሚጦሯቸውን የቤተሰብ አባላት ጨምሮ ፻፺፯ (197) ሰዎችን ያስተዳድራሉ። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ፻፹፱ሺ፭፻ (189,500.00) ብር ይከፍሉ ዘንድ ተፈርዶባቸዋል። እነዚህ ሰዎች ሕሊና ያለውን ሁሉ ባለዕዳ ያደርጋሉ። 

የአባቶችን ርስት አንሰጥም ባሉ ተገፉ። ትእምርተ መስቀሉ በማያምኑ እጆች ተነቅሎ በማይመጥነው ቦታ ተጣለ። ለመስቀል አዲሱ አይደለም። ግን ባለጊዜ ነን ያሉ #ጽንፈኛ_ፕሮቴስታንቶች ይህን አደረጉ። እኛስ?

አጋርነታችንን የምናሳይበት ዕድል ተመቻችቶልናል። በዚህ የGoFundMe  የሚችሉትን ያድርጉ። የቻሉትን በመደገፍ ከሕሊና ተጠያቂነት እፎይታ ያግኙ። 

የሚሰጥ በልግስና ይስጥ።  ሮሜ ፲፪ ፡ ፰። 

#ሁሉም_ኦርቶዶክሳዊ_ለአንድ_ኦርቶዶክሳዊ_አንድ_ኦርቶዶክሳዊ_ለሁሉም_ኦርቶዶክሳዊ

አስተባባሪ ፡- ዲያቆን ዓባይነህ ካሤ እና ዋልድባን እንታደግ ማኅበር 
 
በሀገር ቤት ለሚረዱ እንዴትና የት ይከፈት? የሚለውን ከሚያስተባብሩልን ጋር ተነጋግረን እንደተከፈተ እናሳውቃለን።  በርቱ እንበርታ እጃችን ይፈታ!

Organizer and beneficiary

Save Waldba
Organizer
Springfield, VA
Save Waldba
Beneficiary

Begin your fundraising journey

Create a fundraiser for any person, cause, or nonprofit - it's free and every cause matters.

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.