
ድምፅ ከራማ ተሰማ! ከራማ ድምፅ ሰምቶ ዝም የሚል ኦርቶዶክሳዊ የለም!!!
Donation protected
ድምፅ ከራማ ተሰማ !
ከራማ ድምፅ ሰምቶ ዝም የሚል ኦርቶዶክሳዊ የለም!!!
የራማ ቅድስት ኪዳነምሕረት አንድነት ገዳም በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በራያ ቆቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ዞብል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትገኛለች፡፡ ከተሰዓቱ ቅዱሳን መካከል በአባ ጉባና በአባ ገሪማ አማካኝነት በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መመሥረቷን ታሪክ ያስረዳል፡፡
ገዳሟ በየጊዜው የተለያዩ ፈተናዎች እንደገጠሟት የሚታወቅ ሲሆን በ8ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በተነሣችው ዮዲት ጉዲት እና በ15ኛው መቶ ክ/ዘመን የተከሰተው የግራኝ አህመድ ያደረሱባት ጥፋቶች የሚጠቀሱ ሲሆን ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ ገዳሟና ገዳማውያኑ በመከራ ተፈትነውና ፈተናውን በኃያሉ እግዚአብሔር ተወጥተው ከአጼ ዮሐንስ 4ኛ ዘመነ መንግሥት ደርሳለች፡፡
እስከ አጼ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት ድረስ ታቦተ ሕጓ ለ300 ዓመታት ተሰውራ በቅዱሳንና ንጹሐን አባቶች ስትገለገል የነበረች ሲሆን በንጉሡ ዘመን በእግዚአብሔር ፈቃድ በተዓምር ተገልጻለች፡፡ እርሳቸውም ገዳምነቷ እንደጥንቱ እንዲጸና አዝዘው ተገድማለች፡፡
በማያቋርጥ ተዓምር አድራጊነቷና ድንቅ ሥራዋ የምትታወቀው ይህች ገዳም ከጊዜ ወደ ጊዜ ዝናዋ እየገነነ እና የቅዱሳን መናኸሪያ በመሆን ዛሬ ለአለችበት ወቅት ደርሳለች፡፡
ይህች ቅዱስ ቦታ በርካታ በእድሜ የገፉና ለበርካታ ዓመታት ከገዳሟ ሳይለዩ ጸንተው የሚኖሩ አባቶችና እናቶች እንዲሁም የወጣትነት ሕይወታቸውን ለፈጣሪያቸው የሰጡ መናንያን በአንድነት ገዳምነቷ የሚተዳደሩባት ስትሆን የነገ የቤተክርስቲያን ተረካቢ የሆኑ የአብነት ተማሪዎችንም በሥሯ በማስተዳደር ሃይማኖትና ሀገር የጣሉባትን ኃላፊነት እየተወጣች የምትገኝ ድንቅ ገዳም ናት፡፡
በተጨማሪም ዝናዋን የተረዱ ምዕመናን በቦታዋ ተገኝተውም ሆነ በአሉበት ሆነው ሲማጸኗት በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን የምታድል ቅድስት ቦታም ናት፡፡
ገዳሟ በሥሯ የሚተዳደሩትን የልጆቿን ፍላጎት የምታሟላው በሁለት መንገዶች ከሚገኝ ገቢ ነው፡፡
- 1ኛ ከአላት አነስተኛ የእርሻ መሬት ላይ የሚገኝ አነስተኛ የእህል ምርት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ በዝናብ እጥረት ምክንያት በቂ አዝመራ መሰብሰብ ስለማይቻል አስተማማኝነት የለውም፡፡
- 2ኛ ደግሞ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ የሚገኙ ወዳጆቿ የሚያደርጉላት ልገሳ ሲሆን ይህም ዘላቂነት ስለሌለው ራሷን ችላ ለመተዳደር አልቻለችም፡፡ ይህ ደግሞ በገዳሟ የሚሰጠውን አገልግሎትና ለኃይማኖታችን መቀጠልና መስፋፋት ተስፋ የሚሆኑ የአብነት ተማሪዎችን በቋሚነት ለማስተማር የሚደረገውን ጥረት እየፈተነው ይገኛል፡፡
በሃገራችን በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ከበጎ አድራጊ ወዳጆቿ ሲገኝ የነበረው ድጋፍ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ከአስከተለው ፈተና መውጣት ሳይቻል ገዳሟ በራያ ቆቦ፣ በአፋር ዞብል እንዲሁም በዋጃ አላማጣ አዋሳኝ ሥፍራ ላይ የምትገኝ በመሆኗ ምክንያት ከፍተኛ የጦርነት ቦታ ስለነበረች በቅርቡ በተካሄዱት ተከታታይ ጦርነቶች ምክንያት ገዳሟ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል፡፡ በመሆኑም፡-
- በጸሎትና በሥራ ገዳሟን ከልብ ሲያገለግሉ የነበሩ 3 አባቶችና 3 የአብነት ተማሪዎችን በሞት ነጥቋታል፣
- ሦስት የአብነት ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በሕክምና ላይ እንዲቆዩ ምክንያት ሆኗል ፣
- የገዳሙ ማኅበረሰብ በምግብ፤ በአልባሳትና በመጠለያ ችግር እንዲሰቃይና ጦርነት ለሚያስከትለው የስነልቦና ጉዳት እንዲጋለጡ
አድርጓቸዋል ፣
- ረጅም ዕድሜ ያለውና ታሪካዊው የኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያንና በመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ፣
- በእናቶች መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም በአገልግሎት መስጫ ቦታዎችና እቃዎች ላይ ጥፋት አድርሷል፣ ለምሳሌ ያህል ሁለት ባለ 10 ሺህ ሊትር የውሃ ታንከሮች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል፣
እንግዲህ ከላይ የተዘረዘሩት ወቅታዊ ችግሮች በመከሰታቸው ምክንያት በገዳሟ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድረዋል፡፡ በመሆኑም ዛሬ ነገ ሳይባል መፍትሔ መስጠት ተቀዳሚ ተግባር እንደሆነ መገንዘብ ያሻል፡፡ ለገዳሟ መናንያን እና የአብነት ተማሪዎች ዓመታዊ ቀለብ የሚያስፈልገው ዝርዝር ከዚህ እንደሚመለከተው ነው፡-
- 60 ኩንታል ሽሮ፣
- 250 ኩንታል ዳጉሳ (ቀደም ሲል 150 ኩንታል ተገዝቷል)፣
- 15 ኩንታል በርበሬ ፣
- 100 ኩንታል በቆሎ፣
- ለአብነት ተማሪዎች - 100 ኩንታል ስንዴና 100 ኩንታል በቆሎ
- እንዲሁም ለመነኮሳት ልብስና ፎጣ በጣቃ ማሟላት ይጠበቃል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ገዳሟ ዘላቂ የገቢ ማስገኛ እንዲሆን በደሴ ከተማ በአንድ በጎ አድራጊ ምእመን ለገዳሟ በተሰጠ መሬት ላይ እየተሠራ ያለውን ባለ 7 ወለል ሕንፃ በፍጥነት በማጠናቀቅ ወደ ሥራ በማስገባት ገዳሟን ከዘወትር ልመናና ጥገኝነት ማላቀቅ ቸል ሊባል የማይገባው ትልቅ ቁም ነገር ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የሕንፃው የመጀመሪያ ወለል ኮለሞቹ የተጠናቀቁ ሲሆን ቀጣይ የሁለተኛ ሦሌታና ኮለሞችን ሥራ ለማከናወን፡-
- የሁለተኛው ስላብ፣ 34 ኮለኖች እና ደረጃ ዋጋ ---- ብር 2,479,790
- አንድ ኮለን ቁሳቁስ እና የሰው ጉልበት ጨምሮ ---- ብር 20,000
- ሁሉንም ኮለን ቁሳቁስ እና የጉልበት ዋጋን ጨምሮ ---- ብር 618,560.00
- ሁለተኛው ስላብ ከነደረጃው ------ ብር 1,861,230.00
- የብረት ዋጋ ---- ብር 1,184,230
- ሲሚንቶ -------- ብር 356,400 (330 ኩንታል)
- ጠጠርና አሸዋ --- ብር 112,000
- የጉልበት ዋጋ ---- ብር 208,800 ያስፈልጋል፡፡
ገዳሟን እስከአሁን ሲደግፏትና ከጎኗ በመሆን መከራዋን ሲያቀሉላት፣ ሸክሟንም ሲያራግፉላት የነበሩ ወዳጆቿና ልጆቿ ላደረጉት ሁሉ ቸሩ እግዚአብሔር ዋጋቸውን በነፍስም ሆነ በሥጋ እንደሚከፍላቸው እያመንን ዛሬም በሐዘኗና በጉዳቷ ጊዜ በጎ አገልግሎታቸው እንዳይለያት እናሳስባለን፡፡
በዚህ አጋጣሚም ጥሪዋን ለሚሰሙት ሁሉ ለሚያደርጉት ሁሉን ዓቀፍ ድጋፍ የባንክ ሒሳብ ቁጥርና የስልክ አድራሻ ከዚህ በታች ተጠቅሷል፡፡
- የራማ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም በዚህ የ GoFundMe የገቢ መርጃ ድህረ ገፅ
- በውጭ ሐገር ለምትኖሩ በ Zelle ለመላክ በስልክ ቁጥር [1 6183329989] መጠቀም ትችላላችሁ።
- የራማ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ የሒሳብ ቁጥር - 1000037597426
- የስልክ ቁጥሮች ፡- 0911025881, 0911639820, 0920052423, 0914613824, 0911705996, 0914714220,
- 0911688592, 0911121292, 0914710039, 0914313120
የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከትና አማላጅነቷ በሁላችሁም ላይ እንዲያድርባችሁ እንጸልያለን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፤
Organizer
Woldearegawi Abi
Organizer
Bridgeton, MO