እህታችን ዘማሪ የምስራች ሲሞን በደረሰባት በሽታ በጠና ታማ ሆስፒታል ትገኛለች። የምርመራ ውጤቱ የሚያሳየው ጥሩ ነገር አይደለም። እርግጠኛ ለመሆን የባዬፕሲ ምርመራ እየተደረገ ሲሆን ዶክተሮች በአፋጣኝ ምርመራና ህክምና እንዲጀመርላት አሳስበዋል። እህታችን በትጋት ጌታን ስታገለግል የነበረች የተወደደች እህት ነች። አሁን የገጠማትን የህክምና ችግር ለመፍታት ወጪው ከፍተኛ ስለሆነ ወገኖች የእናንተን ትብብር ትጠይቃለች። ለታሳዪት የጌታ ፍቅር ጌታ ብድራታችሁን ይክፈላችሁ።


