- K
- B
- F
አሐዱ ባንክ 0037496611701
ኦሮሚያ ባንክ 1655036000001
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000260413717
ባልጪ ደ/ገ/ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን 1000260413717 CBC
አጭር የቤተ-ክርስቲያኒቱ ታሪክ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን በኢ/ኦ/ተ/ቤተ-ክርስቲያን በአሁኑ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ዳሎቻ ወረዳ ዳሎቻ ከተማ በሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት በስልጤ ዞን ወረዳ ቤተክህነት ስር የምትገኘዋ እድሜ ጠገቧ 115 አመት ያስቀጠረችው የባለጪ ደ/ገነት ቅ/ማርያም ቤተ-ክርስቲያን እና 107 አመት ያስቆጠረው ስእለት ሰሚው የዳንጌ ደ/ሳህል ቅ/ሚካኤል ቤ/ያን በከተማው ውስጥ የሚገኙ የዞኑ አንጋፋ ደብሮች ናቸው ከተማውም ከወራቤ 12 ኪ.ሜ. ፣ከአዲስ አበባ 180 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
በሁለቱም አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሚገለገው ምእመናን ቁጥር ከ300 አባወራ ከ1500 የምእመናን ቁጥር የማይበልጥ ስንሆን እነኚህ ሁለት ደብሮች እስከ ዛሬ ድረስ በየቦታው ብዙ መከራና እና መገፋት ብሎም የቤተ-ክርስቲያን ቃጠሎ ሲደርስ በራሳቸው ተአምር በብዙ መከራ አልፈው እስከ ዛሬ ድረስ በሁለት ካህናት ብቻ በፈረቃ አንድ ሳምንት የሚካአል ቤ/ያንን በመዝጋት ሌላኛውን ሳምንት የእመቤታችን ቤ/ያንን በመዝጋት የቅዳሴ አገልግሎት እየተካሄደባቸው ይገኛል ፡፡
በመቀጠልም የባለጪ ደ/ገነት ቅ/ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ታሪኳን ስንቃኝ በዘመኑ በነበሩ አባቶች በብራና ተፅፎ ባገኘነው መረጃ ከግራኝ አህመድ ወረራ ወዲህ ከጣሊያን ምላሽ እራስ ልዑልሰገድ ድጆ ወንዝ በፈሰሰ ቦቦዶ ወንዝ በመለሰ የአርጩማን ሜዳ አካተው በሺ ጊደር በሺ ሰንጋ ከአፄ ሚኒሊክ መሬት ገዝተው በባልጪ ተራራ ላይ (ከከተማው 12ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በሚገኝ ቦታ) በጠፍር በታሰረ ጥድ በቀርከሃና በተለያዩ የእፅዋት እንጨት ተጠቅመው የሳር ቤተ-ክርስቲያን አሰርተው ከአንኮበር የእመቤታችን ቅ/ድ/ማርያምን ፅላት አስመጥተው በወርሀ ጥር በ1891 ዓ/ም በዘመነ ማርቆስ ተከሉ፡፡
በ1952 ዓ/ም የዳሎቻ ወረዳ ምስለኔ ገዢ ሆነው ተሹመው የመጡት አባት አቶ አዘነ ውቤ የእመቤታችንን ቤተ-ክርስቲያን ለመሳለም ከከተማው 12 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀው ባልጪ ተራራ ላይ ወጥተው ከተሳለሙ በኋላ የመጀመሪያ ስራቸው ያደረጉት ፅላቷን ከነአገልጋዮቿ ከነበሩት አባቶች ጋር መክረው ከዚያም ለቤተ-ክርስቲያን መስሪያ ቦታ ከልለው ዛፍ አስተክለው አሁን ያለችበትን ቤተ-ክርስቲያን አሰርተው ጥር 21/1955 ዓ/ም ጽላቷ ከነ አገልጋዮቿ ዳሎቻ ከተማ እንድትገባ አደረጉ፡:
አሁን ስላለንበት የእመቤታችን ቤተ-ክርስቲያን ስናወሳ በዳሎቻ ወረዳ በዳሎቻ ከተማ ውስጥ የምትገኘው የባልጭ ደብረ ገነት ቅ/ድ/ማርያም ቤተ-ክርስቲያን በዕድሜ ብዛት ያረጀች በመሆኑ አዲስ ህንፃ ቤተ-ክርስቲያን ለመስራት ኮሚቴ ተመርጦ በማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት እስከ 200000 ብር የሚፈጅ የቤተ-ክርስቲያኑን ሙሉ ዲዛይን በነፃ በማሰራት በብጹእ አባታችን አቡነ ህርያቆስ መልካም ፈቃድ ህዳር 2011 ዓ/ም የመሰረት ድንጋይ አኑረው የህንጻ ቤ/ያኑን ግንባታ ሀገር ውሰጥ እና ውጭ ሀገር ባሉ በጣት በሚቆጠሩ ጥቂት ምእመናን እና የአካባቢውን ህዝበ-ክርስቲያኑን በማስተባበር አሁን በደረስንበት ደረጃ ግንባታው እየተሰራ ነው፡፡ በመሆኑም የአካባቢው ምእመን በቁጥር በጣም አነስተኛ እና በኢኮኖሚውም በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ የቤተ-ክርስቲያኑን ህንፃ ግንባታ በዘላቂነት ለማስኬድ ትልቅ ፈተና ሆኖብናል ይህን ፈተና ለማለፍ የቤተ-ክርስቲያኑን ስራ በተፋጠነ መልኩ ለማስኬድ የሁሉንም የቤተ-ክርስቲያን ልጅ ድጋፍና እርዳታ የሚጠይቅ ነው፡፡
በተጨማሪም ይህን ሁሉ ታሪክ የያዘች ቤተ-ክርስቲያን ታሪኳ ተዳፍኖ እንዳይቀር እና አሁን እየታነፀ ያለው የእመቤታችን ህንፃ ቤተ-ክርስቲያን ያለንበትን ቁመና ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ለማሳወቅና ታሪኳ ለትውልድ እንዲተላለፍ በታሪክ ማህደር ተቀርጾ እንዲቀመጥ ለማስቻል እና የጀመርነው ህንፃ ቤተ-ክርስቲያን 1040 ካ.ሜ ላይ ያረፈ ስለሆነ ሁላችንም በመተጋገዝ ከፍፃሜ ለማድረስ፣ ከበረከቱ ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉ ምእመናን ለማግኘት የሁሉም ሰው ድጋፍና ትብብር ይበልጥኑ ያስፈልገናል፡፡
ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር!!

