የቢላል ሱልጣን የኩላሊት ንቅለ-ተከላ ህክምና ወጪ እርዳታ ማሰባሰቢያ

26 donors
0% complete

$3,080 raised of $30K

የቢላል ሱልጣን የኩላሊት ንቅለ-ተከላ ህክምና ወጪ እርዳታ ማሰባሰቢያ

ጤና ይስጥልኝ! ስሜ ቢላል ሱልጣን ይባላል። በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ (AWTI) የሜካኒካል ምህንድስና ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪዬን በምከታተልበት ወቅት እና የሁለተኛ አመት ተማሪ እያለሁኝ (በ1993 ዓም) ባጋጠመኝ ድንገተኛ የስኳር በሽታ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAU) ተዛውሬ በፈጣሪ ድጋፍ እና በከፍተኛ ጥረት ትምህርቴን ማጠናቀቅ ችያለሁኝ። በመቀጠልም በሙያዬ በተለያዩ ድርጅቶች በማገልገል አገራዊ ሀላፊነቴን እየተወጣሁኝ እገኛለሁኝ። በግል ህይወቴም ራህመት ጀማል ከምትባል የትዳር አጋሬ ጋር ይምኖር ሲሆን፥ የፈጣሪ ፈቃድ ሆኖ የሁለት ልጆች አባትም ሆኛለሁኝ።
በአሁኑ ሰአት በስኳር በሽታው ምክንያት ሁለቱም ኩላሊቶቼ የደከሙ መሆናቸው በህክምና ባለሜያዎችና በተለያዩ ምርመራዎች የተረጋገጠ ሲሆን፥ የኩላሊት እጥበት (DIALYSIS) በሳምንት ለ3 ጊዜ በማድረግ ላይ እገኛለሁኝ። ባደረግኩት የህክምና ምርመራ መሰረትም፥ ሁለቱም ኩላሊቶቼ በአፋጣኝ ንቀለ-ተከላ (TRANSPLANT) ተከናውኖ መተካት እንደሚያስፈልጋቸው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ቦርድ የተነገረኝ ሲሆን፥ እህቴ ኩላሊቷን ለመለገስ ፈቃደኛ ሁና መለገስ መቻሏም በምርመራ ተረጋግጧል።
ይሁን እንጂ፥ውጤታማ የንቀለ-ተከላ ህክምና ለማከናወን እንዲቻል በህንድ አገር ወዳሉ የህክምና ተቋማት በአፋጣኝ መጓዝ እንደሚያስፈልግ እና በዚያ ህክምናውን ለማከናወን ይቻል ዘንድም አስከ ሰላሳ አምስት ሺህ የአሜሪካን ዶላር (35,000 USD) እንደሚያስፈልግ ተነግሮኛል። ነገር ግን ይህንን ወጪ ለመሸፈን የናንተን የወዳጆቼን ድግፍ ለመጠየቅ ተገድጃለሁ።
በመሁኑም፥ አቅምችሁ የፈቀደውን ድጋፍ ከታች በተጠቀሰው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ወይንም በስሜ በተከፈተው የ GOF-FUND ME አካውንት ታገርጉልኝ ዘንድ በትህትና እየጠየቅኩኝ፥ ለአብሮነታችሁም ፈጣሪ ውለታችሁን አብዝቶ ይከፍላችሁ ዘንድ ፀሎቴ ነው።

ፈጣሪ ምህረትን ይሰጠኝ ዘንድም በፀሎታችሁ አትለዩኝ።

አመሰግናለሁ!
ቢላል ሱልጣን

የባንክ ሂሳብ ባለቤት ስም፡ ቢላል ሱልጣን
የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡1000010980295
ለተጨማሪ መረጃ በ+251911567307 መደወል ይቻላል።

Hello,
My name is Bilal Sultan,
I live in Addis Ababa with my beloved wife Rahmet Jemal, and our two beautiful children. In the year 2000, while doing my undergraduate studies in Mechanical Engineering at Arba Minch University, I was diagnosed with diabetes and was transferred to Addis Ababa University (AAU) to receive better treatment as I studied.
Since then, I have been facing difficulties with my health.
Presently, I am facing kidney fatigue caused by diabetes, a condition confirmed by medical experts and various tests. I am currently undergoing dialysis three times a week to manage this health challenge.

Following my medical assessment, the medical board at Black Lion Hospital advised an urgent need for a kidney transplant for both of my kidneys. Fortunately, my sister has expressed her willingness to donate her kidney for this purpose.
However, to undergo a successful kidney transplant treatment, it has been recommended that I immediately travel to medical facilities in India. The cost for the treatment there amounts to thirty-five thousand American dollars (35,000 USD). Regrettably, I am compelled to seek support from friends to help cover this expense.

Hence, I humbly request your assistance by contributing to the bank account number provided below or the GoFundMe account created for this cause.
Kindly keep me in your prayers.
Thank you.
Bilal Sultan






Organizer

Alem Aweke Embiale
Organizer
Coppell, TX
  • Medical
  • Donation protected

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee