ኑ የእግዚአብሔርን ቤት እንስራ
Donation protected
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱአምላክ አሜን!!
በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረስብከት በጡሎ ወረዳ በመጣቀሻ ደብረ ሥጋዌ ቅዱስ አማኑኤል (ደበሶ አማኑዔል) ቤተክርስቲያን ህንፃ ፃአሰሪ ኮሚቴ::
የመጣቀሻ ቅዱ ስአማኑኤል ቤተክርስቲያን የምትገኘው በመጣቀሻ ንዑስ ከተማ ውስጥ ነው:: በቀደመው ዘመን ደበሶ አማኑኤሌ ትባል ነበር ::
ይህቺ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በ1886ዓ.ም በመምሬ ዛማኑኤል ቢሰጡኝ ሲሆን ከምስረታዋ ጋር ልዩ አስገራሚ ታሪክ ያላት ቤተክርስቲያን ናት:: ይህቺ ደብር በአሁኑ ግዜ በሌላ ተቀናቃኝ እምነት ተከታዮች የተከበበችና ከሱ ጋር ተያይዞ ባለው የዘመኑ ፖለቲካ ተፅእኖ ስር የወደቀች በመሆኗ ብረቱ ፈተና ውስጥ ሆናም ታሪክና ሀይማኖታቸውን አንለቅም ባሉ አቅመ ደካማ ምእመኗ ብርታት በመንገዳገድም ቢሆን ከዚህ ደርሳለች!!. የምእመኗ ማነስና አቅመ ደካማነት የተነሳ ለቤተክርስቲያኗ ዘላቂ አገልግሎት የሚበቃ ንዋይ ማግኘት ተስኗት ብትገኝም ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም በሚለው የአበው ምሳሌ በመበርታትና በአማኑኤል ፈቃድ እንዳትዘጋና ትውልዱን ወደ እስልምናና ፕሮቴስታንት ሀይማኖት እንዳይነጠቅ በመንፈሳዊ በተጋድሎ ላይ ትገኛለች:: ከዚህ ሁሉ ፈተና በላይ ቤተ ክርስቲያኗን የገጠማት አደጋ ;ከእርጅና የተነሳ በመፍረስ አደጋ ላይ በመሆኗ አሁን ውልቅልቋ ወጥቶ ከአገልግሎት ውጪ የመሆኗ ሁኔታ እርግጥ የመሆኑ ነገር ነው::
ምእመኗ ይህን ሁሉ ሸክም ለመሸከም ከማይችል የኑሮ ችግር ውስጥ ያሉ ከመሆኑ የተነሳ ሊታደጓት የሚችሉበት አቅም የሌላቸው ሙልጭ ያሉ ደሆች በመሆናቸው ለኦርቶዶክስ ክርስቲያን እምነት ቀናኢ የሆናችሁትን; እንዲሁም በዚህች ቤተክርስቲያን የተገለገላችሁ;ያደጋችሁ; ክርስትና የተነሳችሁ ;ትሩፋቷ የደረሳችሁ ;የታሪኳ ተቋዳሽ የሆናችሁ በአለም ለተበተናችሁት ዝርያና ልጆቿ ሁሉ ትደርሱላት ዘንድ በአማኑኤል ስም ለልመና መጥተን በራችሁን አንኳኩተናል!!
የአካባቢው ተወላጅና በዚህችው ቤተክርስቲያን ክርስትና የተነሳ አሁን አዲስ አበባ የሚኖር ቀና ልጇ ድንገት መጥቶ ይሄን ችግር ተመለክቶ ስሜቱ ስለተነካ በግሌ እሰራለሁ ብሎ በለ ሶስት ጉልላት አዲስ ህንፃ ለማሰራት ጀምሮ ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ እንደሚባለው ሆነበትና 60% ቱን ስራ ቢያገባድድም 6 ሚሊዮን ብር ፈጅቶበት በተለያየ የግል ጉዳዩ ሊጨርሰው ባለመቻሉ የተጀመረው ህንፃ ሳያልቅ(በፎቶው ላይ እንደምታዪት) ፀሀይና ቁር እየተፈራረቀበት ስራው ከቆመ አመት ስላለፈው ይህ ወንድማችን ሸክም የሆነበትን ሀምሳ ሎሚ ለሀምሳ ሰው ጌጡ ነውና ብትራዱ ከጌጥም አልፎ በረከት እንዲሆንላችሁ ደግሞ ለመቶ; ለሁለት መቶ ;ለአምስት መቶ ;እንደጠበል ብንራጨው የቀረውን 40% ስራ ለማስፈፀም ይቻላልና ልባችሁን አማኑኤል ያነሳሳና ቤቱን ትሰሩና በረከት ታገኙበት ዘንድ አሁንም በቅዱስ አማኑኤል ስም የልመና መልእክታችንን እናቀርብላችሁለን!!
የመጣቀሻ አማኑኤል ህንፃ ኮሚቴ እና ሰበካ ጉባኤ ፅ/ቤት
1ኛ የደብሩ አስተዳዳሪ መላከ
ምህረት ቀሲሥ ደመና ታደሰ
ስ /ቁ 0912 846 067
2ኛ ኢንጅነር ተፈራ ከበደ
የደብሩ ህንፃ ኮሚቴ ሰብሳቢ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ acct# 1000086907481
Gofundme አስተባባሪና ሰብሳቢ ነዋሪነቱ በአሜሪካ የሆነው
አባይነ ረታ ( ሰለሞን አበበ) መሆኑ በእክብሮት እንገፃለን!!!
************************
ኑ በአንድነት የእግዚአብሔርን ቤት እንስራ!!!
************************
በዚህ በጎ አገልግሎት ላይ ለምትሳተፉ በሙሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም ቀድመን እናመሰግናለን !!

Organizer
Solomon Abebe
Organizer
Snellville, GA