የስፖርት ጋዜጠኛዋ ብርቱካን አካሉ የህክምና መርጃ

የብርቱካን ጥሪ
"ከአጠገቤ ሆና አትዳብሰኝ....እናት የለኝ፤ በርቺ ጠንክሪ አይለኝ.....አባት የለኝ፤ መድሀኒት አያቀብለኝ....ወንድም የለኝ፤እንዳታፅናናኝ.....እህት የለኝ..... አሁን ተስፋዬ እግዚአብሄር ነው። አሁን አጋዤ ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው። እናም ድረሱልኝ።”

ገና በአፍላነት ዕድሜዋ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን "ብርቱካን ከቦሌ" በሚለው ስሟ አስተያየት በመስጠት ከአድማጭና ከስፖርት ወዳጅነት የመሰረተችው ብርቱካን አካሉ በመቀጠል ወደ ሚዲያው ብቅ ብላ ለሀገራዊ እግር ኳስ ትኩረት በመስጠት "ሀበሻ ሊግ "የሚባል ፕሮግራም መስርታ ከሙያ አጋሮቿ ጋር በመሆን ጨዋታዎችን በቀጥታ ማስተላለፍ ትታወቃለች። በርካታ የሀገር ውስጥ ጨዋታዎችን እንዲሁም የአፍሪካ ዋንጫን ጨምሮ አህጉራዊ ውድድሮችን በፕሮግራሟ ሽፋን ሰጥታለች።

ብርቱካን የባለፉትን ሶስት አመታት ግን ሄድ መለስ ከሚል ህመም ጋር በደቡብ አፍሪካና በኬኒያ ማሳለፏን ትናገራለች።
በዚህ ሁሉ ጉዞዋ ህመሙ እየባሰ በመምጣቱ ለህክምና ብዙ ገንዘብ ማውጣቷን፣ ከስራ በተለያዩ ምክንያቶች መራቋን በዚህም ምክንያት ተከራይታ መኖር ባለመቻሏ ማረፊያ ጎጆ በማጣቷ ብሎም የዕለት ጉርስ በመቸገሯ በጥቂት ወዳጆቿ ጥረት ከኬኒያ ወደ ዱባይ ለስራና ለተሻለ ህክምና እንደተጓዘች ትናገራለች። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ሁሉን በሆዷ ይዛ ነበርና የት እንዳለች ምን እንዳጋጠማት የሚያውቅ ሰው ውስን ነበር።

አሁን ግን ህመሟ ከአቅሟ በላይ ሆኖ አልጋ ላይ ወድቃለች፤ ዱባይ በሚገኙ ልበ ቀና ኢትዮጵያዊያን ፈቃደኝነት ከ12 ሰዎች ጋር አብራ ትኖራለች፤ ከጨጓራ ጋር በተያያዘው ጋዝትሪክ አልሰር በተባለው ፅኑ ህመሟ ምክንያትም መደበኛ ምግቦችን መብላት አቁማለች። ጥቂት ፈሳሽ ብቻ ዕለታዊ ቀለቧ ሆኗል፤ ከህመሙ ጋር በተያያዘም ሆዷን ጨምሮ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ዕብጠት ተከስቷል፤ በፍጥነት አስፈላጊውን ህክምና ካላገኘችም በሽታው ወደ ካንሰር እንደሚቀየር የህክምና ባለሙያዎች ነግረዋታል።

ከሰሞኑ ከፍተኛ ድካም እየተሰማት በመሆኑ ከአልጋ እንደማትወርድና በሳምንት ሁለት ቀን ማስታገሻ ብቻ የሚሰጣት ብርቱካን ለሶስት አመታት ያፈነችውን ህመሟን አሁን ይፋ አድርገዋለች፤ዕንባ ባጀቡት ተስፋ የመቁረጥ አንደበቷ ለኢትዮጵያዊያን የድረሱልኝ ጥሪ አቅርባለች። ያቺ ለሁሉ ፈጥኖ ደራሿ ወጣት አሁን አልጋ ላይ ወድቃለች።

ብርቱካን በአጠቃላይ ለህክምና 6ሺህ ዶላር እንደጠየቋት ይፋ አድርጋለችና ሁላችንም ልንደርስላት ይገባል። በሰው ሀገር ያለ በቂ ህክምና ክትትል በገንዘብ ዕጦት ለተኛችው ዕህታችን አለንልሽ ልንላት ይገባል።

ጎጃም ደንበጫ የተወለደችው ብርቱካን አካሉ ለቤተሰቦቿ ብቸኛ ልጅ ከመሆኗ በተጨማሪ ወላጆቿን በሞት ያጣችው ገና ታዳጊ ሆና ነው። ያለ ወላጅ፣ ያለ ዕህትና ወንድም ከዚህች አለም ጋር ተፋጣ ሳለ በብዙ የልጅነት ውጣውረድ ካሳለፈች በሗላ በ1997 ወደ አዲስ አበባ መጥታ ኑሮን በማሸነፍ ላይ የነበረች ብርቱ ልጅ ዛሬ በበሽታ ዕንዳትሸነፍ እናግዛት።

በሀገር ቤት ያሉ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎችና የስፖርቱ ባለድርሻዎች በዚህ ሳምንት ውስጥ ዝርዝር የዕርዳታ መንገዶችን ይፋ ስለሚያደርጉ ለብርቱካን እንድረስላት።

ብርቱካን  ዱባይ የምትገኝበት ስልክ፥ +971569460828

Legal Notice
Sole Benneficiary of this campaign is
Birtukan Akalu Ambaw
Dubai, UAE
Since Birtukan does not have a Bank account in Dubai all the money collected in this campaign will be sent to Birtukan Akalu Ambaw via Western Union Money transfer so that she can get it as soon as possible to cover her medical expenses.

 • Aschu Asabie 
  • $50 
  • 59 mos
 • Wengel Hagos 
  • $40 
  • 59 mos
 • Abo Gedel 
  • $30 
  • 59 mos
 • Asfaw Yilma 
  • $50 
  • 59 mos
 • Mekonnen Gulelat 
  • $50 
  • 59 mos
See all

Organizer

Yitayal Mengistu 
Organizer
Seattle, WA