- A
ውድ የሀገሬ ልጆች ከዚህ ቀደም በነጋሽ ሚዲያ ላይ እና በደረጄ ዘወይንዬ ሚዲያ ላይ ቀርቤ በሰጠሁት ሐሣብ ምክንያት ለደረጄ ዘወይንዬ እና ለጋዜጠኛ ነጋሽ በዳዳ መታሠር ምክንያት በመሆኔ በጣም ከፍተኛ ጸጸት ውሥጥ ነበርኩ።በዚሕም የተነሣ ዳግም በፍጹም ለሌሎች ወንድሞቼ መታሠር ምክንያት ላለመሆንና አገልግሎቴን በራሴ ሚዲያ ከፍቼ ለማገልገል የተከበራችሁ ምእመናን የቻላችሁትን እንድታግዙኝ በቤተክርስቲያን አምላክ ሥም በፍቅር እጠይቃለሁ። ለዚህም ትብብራችሁ በቅድሚያ በቸሩ እግዚአብሔር ስም አመሠግናለሁ :: እግዚአብሔር በሁላችንም ቤት በረከቱን ያብዛልን አሜን::




