Let's Finish Our Sunday School Bldg
የነገዪቷን ቅድስት እና ሃዋርያዊት ቤተክርስቲያናችንን ተረካቢ ትውልድ በምግባር ፣በሃይማኖት እና በማንኛውም ረገድ የሚረከብ ትውልድን ለመቅረጽ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በላይ ስትደክም እዚህ ደርሳለች። በአሁኑ ሰዓትም በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን አዲስ ኹለ-ገብ የአገልግሎት ሕንጻ በቅርቡ ለማጠናቀቅ እና ውጤቱን ለማየት የኹላችንንም የገንዘብ ዕርዳታ ትለምናለች። የዕርዳታ ትንሽ የለውምና የሚቻለንን ለማድረግ በመተባበር ታሪክ እንሥራ።
Over the last fifty years, our beloved Sunday School endeavored to shape the next generation of our holy apostolic church in every means. Currently, we are at the finishing point of the most anticipated multi-purpose facility building and we are pleading everyone’s financial assistance to see the long yearned outcome. No help is too small so let’s unite, donate and make history.