Foto principal da arrecadação

Donate to Save Keita's Life Today

Doação protegida

የዕርዳታ ጥሪ

በዚህ ምስል ላይ የምትመለከቱት ወንድማችን እምላዕለ ግርማ በአካባቢ እና በሰፈር ስሙ ኬታ ይባላል።  በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ  ያደገ፣ በግል ስራ የሚተዳደር ባለትዳርና የሁለት ወንድ ልጆች አባት ነው።

ኬታ  በእግር ኳስ ተጫዋችነት በቀድሞ ስሙ ለአቃቂ ወረዳ በአሁን ስሙ ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ  ምርጥ ቡድን ውስጥ ከዚያም ለአቃቂ ቆርቆሮ ፋብሪካ (ሳቢያን) እና ለአቃቂ ጋርመንት ፋብሪካ  በመጫወትም  አካባቢውን አስጠርቷል።

ወንድማችን ዛሬ ግን ኳስን በተለያየ አቅጣጫ እንደልብ የሚያሽከረክሩት እግሮቹ ጭን አጥንት ላይ በተፈጠረ የጤና እክል ለኩላሊት ህዋስ ካንሰር ተጋልጦ መንቀሳቀስ ተስኖታል።

ኬታ እግሮቹን እና ኩላሊቱን ወደ ቀድሞ ጤና ለመመለስም ወዳጅ ዘመድ በማስቸገር በሀገር አሉ የተባሉ እስፔሻሊስት ሀኪሞች ዘንድ በሀገር ውስጥ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና በሌሎችም  የግል ሆስፒታሎች ህክምናውን ቢያደርግም ጤናው ሊመለስ አልቻለም።

እስካሁን ያጠራቀመውን ጥሪት ተጠቅሞ ህክምናውን ቢከታተልም በሀገር ውስጥ መዳን እንደማይችል በሀኪሞች ተነግሮታል።

የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቦርድም በአጭር ጊዜ ከሀገር  ውጪ  ሄዶ መታከም ካልቻለ ሕይወቱን ሊያጣ እንደሚችልም አሳውቀውታል። ህክምናውን በውጪ ሀገራት ሄዶ ለመታከም ከ20 ሺህ ዶላር በላይ እንደሚያስፈልገውም ተገልፆለታል። በውጪ ሀገር ሄዶ ለመታከም እንዲችል መላ ኢትዮጵያውያንን ይማጸናል ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ኬታን በጋራ ተረባርበን እንታደገው።

ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ በሚከተለው የጎፈንድ ሚ አካውንት እንዲሁም  በሀገር ውስጥ ደግሞ በዚህ የባንክ የሂሳብ ቁጥር የእርዳታ እጆቻችሁን እንድትዘረጉ በፈጣሪ ስም  እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገላን ቀርሳ ቅርንጫፍ           
የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000345127667
እምላዕለ ግርማ መንግስቱ


Donate to  Save Keita’s Life Today

Emlaele Girma, known by his nickname Keita, was born and raised in Akaki. Keita’s unfailing pursuit of life left him a legacy of excellence in soccer and ownership in small business. Keita has two adorable sons from his wife.

Keita is known for his humbleness and hard work all along his life.

Today, luck is no more with Keita, whose supersonic legs are shackled by an internal fatal tumor found on his hip. As time went by, the tumor has developed itself as likely to cause kidney failure. Keita’s running up and down to get medical help was to no avail within Ethiopia, and the medical board at Black Lion hospital decided that advanced urgent surgery be done to save his life.

Keita’s advanced surgery can only be done out of Ethiopia which demands about 20 thousand USD,  that is in no way within his reach. We can all save Keita from this tragedy by donating to share the horrible burden today. Let’s all stretch our helping hands and open our hearts to him and his family in the name of God!


Friends of Keita in North America

Doações 

    Organizador

    Genet Moges
    Organizador
    Silver Spring, MD

    Seu lugar confiável, poderoso e fácil para obter ajuda

    • Fácil

      Doe com rapidez e facilidade

    • Poderoso

      Envie ajuda diretamente às pessoas e causas importantes para você

    • Confiável

      Sua doação é protegida pela Garantia de Doação GoFundMe