Main fundraiser photo

7ተኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ - ኑ ትውልድ እናፍራ!

Tax deductible
የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ በላቀ የትምህርት ውጤታቸውና በቤተሰብ ገቢ ሁኔታቸው የተመረጡ ታዳጊ ተማሪዎችን ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ፣ ሴት ተማሪዎችን በልዩ ሁኔታ የሚያበረታታና ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችም እገዛ የሚያደርግ ፕሮግራም ነው።
እስካሁን ለስድስት ዓመታት ባካሄዳቸው 6 ዙሮች :-
  • ከ170 በላይ ተማሪዎችን በየወሩ በወጪ ደግፏል፣
  • ከ1000 በላይ ለሆኑ ሴት ተማሪዎች ወርሃዊ ንጽህና መጠበቂያ በየወሩ አቅርቧል፣
  • ለዓይነስውራን ተማሪዎች የሚያግዙ ድምፅ መቅጃዎችን አቅርቧል፣
  • ወደ ዩንቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የዝግጅት ወጪን ሸፍኗል፣
  • የኮምፒውተር ላብራቶሪዎችን የኔትወርክና ኤሌክትሪክ ዝርጋታ በባለሙያ አሰርቷል ፣
  • የሴት ተማሪዎች መፀዳጃ ቤት አሳድሷል ፣
  • እንዲሁም የመምህራን ማረፊያ ክፍል እድሳት እና አዲስ ሎከሮችን አሰርቷል፣
በተጨማሪም የግቢው አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ የማስተካካያ አሰርቷል፣ የመጽሐፍ ማሰባሰብ ዘመቻዎች አድርጓል፣የቤተመጽሐፍት ወንበሮች ድጋፍና የመጠጥ ውሃ ማጠራቀሚያ (water tank) ለግሷል፣ የፅዳት ዘመቻዎች አካሂዷል።
ሁሉም ሥራዎች የተሳኩት ግን ይህን በጎ ዓላማ ሰምተው በደገፉ ብዙ የተባበሩ እጆች ነው!!
ባለፉት ዙሮች በነበረው ተሳትፎ ከቀድሞ ተማሪዎች በተጨማሪ ሁሉም በጎ አሳቢ ኢትዮጵያውያንና፣
ጉዳዩን ከወዳጆቻቸው የሰሙ የውጭ ሀገር ዜጎችም ጭምር መሳተፋቸውን አይተናል። በመጪው የ2016 የትምህርት ዓመትም የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት ይህን በጎ ሥራ ለማስቀጠል ከዚህ በታች ያለውን ዕቅድ አውጥቶ በየዓመቱ የሚያደርገውን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ጀምሯል። እርስዎም ይሳተፉ ለወዳጆችዎም ያጋሩ!!

በዚህ ለ7ተኛ ጊዜ በሚደረገው “የጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ” ድጋፍ የሚከተሉትን 6 ዕቅዶች ለማከናወን ታስቧል፦

የጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት- የ2016 ዓ.ም ዕቅድ
  • 1. በትምህርት ውጤትና በቤተሰብ ገቢ ሁኔታ የተመረጡ 32 ተማሪዎችን ለአንድ ዓመት በወጪ ማገዝ ከመስከረም – ሰኔ ለእያንዳንዳቸው 1000 ብር (10 ወር * 32 ተማሪዎች * 1000 ብር) – 320,000 ብር

  • 2. ለ 250 እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ (Sanitary Pads) ለአንድ ዓመት ማቅረብ 150,000 ብር

  • 3. ሴት ተማሪዎች በወር አበባ ጊዜ ድንገተኛ ህመም ሲያጋጥም የእረፍት መውሰጃ እና መታጠቢያ ክፍል ለማሳደስ 66,200 ብር

  • 4. ለ5 ዓይነ ስዉራን ተማሪዎች ለትምህርታቸው የሚረዳ የድምፅ መቅጃ መሳሪያ መግዛት 20,000 ብር

  • 5. ወደ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ለሚገቡ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ድጋፍ ማድረግ እና የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ተማሪዎች ህክምና መጠባበቂያ በጀት 70,000 ብር

  • 6. የህብረቱን ስራዎች ባህር ዳር ላይ ለሚሰራ ጸሐፊ የዓመት ደሞዝ ከመስከረም እስከ ነሐሴ 5000*12ወር= 60,000 ብር

በድምሩ 686,200 ብር የሚገመት ወጪ በማድረግ እነዚህን ሥራዎች ለማሳካት ታቅዷል፡፡ እስካሁን ባለፉት 6 ዙሮች የነበረው የተማሪዎች እገዛ የተሳካው ይህን በጎ ሥራ የሰሙና የወደዱ ሁሉ ባደረጉት ያላሰለሰ የገንዘብ ፣ የሃሳብ እንዲሁም የጉልበት ድጋፍ ነው፡፡ በመሆኑም 7ተኛውን ዙር በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት ጥሪ ስናቀርብ ድጋፋችሁ እንደማይለየን በመተማመን ነው። (ከዚህ በፊት በጣና ቤተሰብ ስኮላርሽፕ የታገዙና ዩንቨርስቲ የገቡ ተማሪዎችን አስተያየት በYouTube ገፃችን ለማየት ይህንን ይጫኑ)

ኢትዮጵያ ውስጥ ያላችሁ በቀጥታ በሚከተሉት የሕብረቱ የጋራ የባንክ አካውንቶች ማስገባት ትችላላችሁ፤
- የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር፤ 1000408845622
- የዳሽን ባንክ አካውንት ቁጥር፤ 5020904670002
Dashen Bank Swift Code = DASHETAA
Or use other donation options on our website HERE

6ኛው ዙር የጣና ቤተሰብ ስኮላርሺፕ ጥር 2015 ዓም

================

About Tana Haik Alumni Network
In the year 2012, a few former-students who lived in Ethiopia and abroad volunteered to work together for the cause of giving back to their school, Tana Haik and the community. They established the alumni group with a vision: “Together, we can make a difference to bring a bright future for students in our community!”. It was launched by supporting the school through providing furniture and Internet service to the Library, and organizing donation of books. In just a few years, alumni from all over the world shared the vision and expanded dimension of the support to students and the school. Currently, there are alumni members from various batches and volunteers participating in annual fundraisers and campaigns to support current students.

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ስለ ጣና ሐይቅ የቀድሞ ተማሪዎች ሕብረት አጀማማር
የጣና ሐይቅ የተማሪዎች ሕብረት በኢትዮጵያና በውጭ ሀገር በሚኖሩ በጎ ፈቃደኛ የቀድሞ ተማሪዎች በ2014ዓም የተጀመረ ነው፡፡ ይዞም የተነሳው መርህ "በጋራ ስንሆን ለውጥ እናመጣለን፣ የተማሪዎችን የተሻለ የወደፊት መንገድም እንቀርፃለን" የሚል ነው፡፡ እገዛውን ሲጀምር የቀድሞ ተማሪዎችን በማሰባሰብ ለታዳጊ ተማሪዎች ሽልማት ሰጥቷል፣ መጽሃፍትን በመግዛት በስጦታ አበርክቷል፣ ትምህርት ቤቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጓል፡፡ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት ሕብረቱ ሰፍቶ በተለያዩ የትምህርት ዓመታት የጨረሱ፣በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚኖሩ የቀድሞ ተማሪዎችን እና ዓላማውን የሚደግፉ በጎ ፈቃደኞችን አቅፎ በጋራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

የሕብረቱ ዓበይት ዓላማዎች ፡-
ለተማሪዎች የገንዘብ እገዛ ማድረግ
የትምህርት ውጤትንና የቤተሰብ ገቢ ሁኔታን በመመዘን በየዓመቱ ለተመረጡ 32 ተማሪዎች ወርሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
በዚህም ተማሪዎቹ የሚኖርባቸውን የኑሮ ጫና በማቃለል ሙሉ ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ አድርገው የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ያግዛል፡፡

ለሴት ተማሪዎች ወርሃዊ የንጽህና መጠባቂያ ሞዴስ ማቅረብ
እገዛ የሚፈልጉ ሴት ተማሪዎችን በየዓመቱ በመመዝገብ 250 ለሚደርሱ ተማሪዎች በየወሩ የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ በትምህርት ቤት ውስጥ ያቀርባል፡፡
በዚህ ልዩ እገዛ ሴት ተማሪዎች በነፃነት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ያግዛል፡፡
በተጨማሪም ለአስቸኳይ ጊዜ የሚሆን ሞዴስ ማንኛውም ሴት ተማሪ፣ መምህራን እና የግቢው ሴት ሰራተኞች እንዲገለገሉ በማሰብ በመጠባበቂያነት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ልዩ እገዛ ማድረግ
ለዓይነስውራን ተማሪዎች በየዓመቱ ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚረዳቸው የድምፅ መቅጃ መሳሪያ ያቀርባል፡፡
በቀጣይም ሌሎች ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የማገዝ ዓላማ አለው፡፡

ለጣና ሐይቅ ት/ቤት የመሠረተ ልማት ሥራዎች ድጋፍ ማድረግ
ሕብረቱ ከዚህ በፊት የመጠጥ ውሃ ማጠራቀሚያ ገዝቶ ለትምህርት ቤቱ አቅርቧል፣ ለትምህርት ቤቱ ቤተመፅሐፍት መጽሐፍት የማሰባሰብ ዘመቻ አድርጓል ወንበሮች ለግሷል፣ በትምህርት ቤቱ ውስጥ የፅዳት ዘመቻዎችን አስተባብሯል፡፡
====================================================

የዚህ የቀድሞ የጣና ሐይቅ ተማሪዎች ሕብረት አስተባባሪዎች ነዋሪነታቸው በኢትዮጵያ፣በአሜሪካ እንዲሁም በአውሮፓ ሲሆኑ ስማቸው እንደሚከተለው ሰፍሯል፡፡

This scholarship is organized by the following former students and volunteers of Tana Haik

Tewodros Tesera – Maryland, USA
Solomon Nurga - Atlanta, USA
Dejenie Tarekegn – Maryland, USA
Tenager Bekalu - Helsinki, Finland
Geta Mehariw –Portland, USA
Solomon Kibret – California, USA
Meseret Ejigu - Bahir Dar, Ethiopia
Sileshi Minayehu – Bahir Dar, Ethiopia
Behailu Yirga - Bahir Dar, Ethiopia
Mastewal Alemu – Bahir Dar, Ethiopia
Eden Metaferia – Stockholm, Sweden
Bekalu Metalign - Addis Ababa, Ethiopia
Rahel Wondie – Addis Ababa, Ethiopia
Minwyelet Getinet – Grande Prairie, Canada
Lake Endalew - Virginia , USA
Yonatan Gossaye – London, UK
Misganaw Birhan - Turku, Finland
Henok Hailemariam– Maryland, USA

Tana Haik Alumni Network
You can find more information below

Website -

Social media page -
To be a member please fill membership form -
Donate

Donations 

  • Samuel Addis
    • $300 
    • 7 mos
  • Yibeltal Hunegnaw
    • $250 
    • 9 mos
  • Solomon Kibret
    • $300 
    • 9 mos
  • Yihenew Ewnetu
    • $200 
    • 10 mos
  • Anonymous
    • $100 
    • 10 mos
Donate

Organizer

Tana Haik Almuni Network
Organizer
Silver Spring, MD
Tana Haik Alumni Network Inc
 
Registered nonprofit
Donations are typically 100% tax deductible in the US.

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about

  • Trusted

    Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee