ወገኖቻችንን ከኮረና ቫይረስ እንታደግ

Foto de la recaudación de fondos ወገኖቻችንን ከኮረና ቫይረስ እንታደግ, 1 de 3Foto de la recaudación de fondos ወገኖቻችንን ከኮረና ቫይረስ እንታደግ, 1 de 3

  • M
  • D
  • Y
26 donantes
0% complete

Se recaudaron $4278 de $100 mil.

ወገኖቻችንን ከኮረና ቫይረስ እንታደግ

Donación protegida
የኮረና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከገኘቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የሚገኙ ወገኖቻችን የተቻላቸውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በመንግስት በኩል የታዘዘ ሲሆን የመንግስት ሰራተኞች በቤት ሆነው ስራቸውን እንዲከውኑም ትዕዛዝ ተላልፏል። ሌሎችም በቤታቸው መቆየት የሚችሉ ወገኖቻችንም ተመሳሳይ ተግባር ይፈጽማሉ። የመጠንቀቂያ ቁሶችንም በመጠቀም እራሳቸውን ከዚህ ቫይረስ የሚጠብቁ ይሆናል። 


ሆኖም ግን የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ አቅመ ቢስ ወገኖቻችን፣ አዛውንቶች፣ ወላጅ አልባ ወገኖች እንዲሁ በሰዎች ምፅወታ የሚኖሩ /የኔ ቢጤ/ ወገኖቻችን እና መሰል የአገራችን የዝቅተኛ ኑሮ ኗሪ ሰዎች በቤታቸው ለ15 ቀናት በሚቆዩበት ወቅት የዕለት ጉርስ እንደሚቸግራቸው ግልፅ ነው። ለነዚህ ቀናቶች ቤተሰብን አይደለም እራስንም የመመገብ አቅም የሌላቸው በመሆኑ የእኛን የወገኖቻቸውን እርዳታ በአፅንኦት ይፈልጋሉ። ስለሆነም እነዚህን ወገኖቻችንን ለማገዝ የጎፈንድ ሚ ገቢ ማሰባሰቢያ አዘጋጅተናል። 


መተጋገዝ እና መረዳዳት ኢትዮጵያዊ ባህላችን ነውና በየአቅማችን በመሳተፍ ወገኖቻችንን እንታደግ ለማለት እንወዳለን። የዚህ ግብ እቅድ 1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ብቻ በመሆኑ ይኼንን ትንሽ ውለታ ለሰፊው እና ለደግ ህዝባችን እናደርግለት ዘንድ ዳግም በድሃ ወገኖቻችን ስም እንጠይቃለን! 


ይኼ ገንዘብ በአስቸኳይ የሚፈለግ በመሆኑ በፍጥነት መሰብሰብ ያለበት ሲሆን ለወገኖቻችን በተሰበሰበው ብር አስፈላጊውን ቁስ ቢያንስ ለ15 ቀናት ማቆየት የሚችል ከመንግስት እና መንግስታዊ ካልሆነ አካል ጋ በመተባበር በተገቢ እንዲደርስና ለታቀደለት አላማም እንዲውል የምናደርግ ሲሆን በቅርቡም ይኼንን ተግባር በአግባቡ የሚፈፅም በጎ ፍቃደኛ ቡድን አቋቁመን ለወገኖቻችን አስፈላጊውን ሁሉ ለመፈፀም እንሰራለን። በሌሎች አገራት የተከሰተው አስከፊ እልቂት በምስኪን ወገኖቻችን እንዳይደገም የሁላችንም ሀላፊነት ነውና ዳግም በነዚያ ምስኪን ወገኖቻችን ስም እርዳታችሁን እንጠይቃለን። 


በተጨማሪም ወገኖቻችንን ለማስተማር እና በቫይረሱ ዙሪያ መጠነኛ ግንዛቤን ለማስጨበጥ  በመዲናችን አዲስ አበባ እየተዘዋወረ መረጃ የሚሰበስብ እና ትምህርት የሚሰጥ ቡድን ያቋቋምን ሲሆን ከነገ ጀምሮ ስራ የሚሰማራ ይሆናል። 


ተባብረን ወገን እናድናለን ሀሳባችንም ግቡን ይመታል። ልዑል እግዚአብሔር ይጨመርበት! 


አብረን እንጂ ለብቻችን አንድንም!!!
Donar

Organizador

Minew Shewa Tube
Organizador
Silver Spring, MD
  • Salud
  • Donación protegida

Un sitio fácil, eficaz y de confianza donde encontrar ayuda

  • Fácil

    Dona de forma rápida y sencilla

  • Eficaz

    Envía ayuda a la gente y las causas que te importan

  • Confiable

    Tus donaciones están protegidas por la Garantía de donaciones de GoFundMe