COVID 19
Steuerlich absetzbar
ይህ የፍቅረ ቢጽ መረዳጃ ኮሚቴ በኦስተን ቴክሣስ የሚገኙ ሐበሾች የ COVID 19 ወረርሽኝን በመረዳዳትና በመደጋገፍ እንዲያሳልፉ በኦስተን ደ/ኃ/ቅ/ራጉኤል እና በማ/ስ/ቅ/ልደታ ለማርያም አብያተ ክርስቲያናት በአንድነት የተመሠረተ አስተባባሪ ኮሚቴ ነው።
ይህ ወረርሽኝ የታመመ ወገናችንን የሰውነት አካል የሚያዳክም ብቻ ሳይሆን፣ እናትን ከልጅ ጋር የሚያራርቅ በመሆኑ የታመመውንም ሆነ ያልታመመ ወገናችንን ስነ ልቡና የሚጎዳና በከፍተኛ ደረጃ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ የሚያስከትል በዘመናችን የተከሠተ መጥፎ ወረርሽኝ ነው።
ስለዚህ የወገናችንን ሕመም ሕመማችን አድርገን እንድናስታምም፤ የወገናችንን ችግር ችግራችን አድርገን እንድንቀርፍ ፤ በአጠቃላይ በወገናችን ላይ የደረሰውን የስነ ልቡና ስብራት እንድንጠግንና አለኝታነታችንን እንድንገልጽ የእርስዎ የወገናችን አጋዥነትና እርዳታ እጅግ ወሳኝ ስለሆነ ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ እጅዎን እንዲዘረጉና ወገንዎን እንዲረዱ በኃያሉ እግዚአብሔር ስም እንለምንዎታለን።
ለሚያደርጉልን እርዳታ ሁሉ በቅድሚያ እናመሰግናለን!!!
አቤቱ፥ ምሕረትህን አሳየን፥ አቤቱ፥ መድኃኒትህንም ስጠን።
መዝሙረ ዳዊት 85:7

Mitorganisatoren (2)
Yodit Asaminew
Organisator
Round Rock, TX
DEBRE HILE SAINT RAGUEL ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHDO CHURCH
Spendenbegünstigte

Tewodros Kidanne
Mitorganisator