
ዳግማዊ ዋልድባ በካሊፎርኒያ ግዛት በሀገረ አሜሪካ
Steuerlich absetzbar
“በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ” ኤፌ2:22
በሰሜን አሜሪካ በመካከለኛው የካልፎርንያ ግዛት ሳን ሚግየል ከተማ፤ ሞንተረይ ካውንቲ የተቋቋመው እና አዲስ የተገዛው የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የአንድነት ገዳምን መንፈሳዊና ማሕበራዊ አገልግሎት ለማስፋፋት በቋሚነት ሊሠሩ ከታቀዱ ሥራዎች መካከል ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ዋና ሥራ አንዱ በዚህ አገር ተወልደው በማደግ ላይ ለሚገኙ ልጆቻችን እና በልዩ ልዩ ችግሮች ለሚሰቃዩ እና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን አስቸኳይና የተሟላ መንፈሳዊ አግልግሎት መስጠት የሚቻልበትን ቅድመ ሁኔታዎች በማዘጋጀት በተግባር ላይ ማዋል የኆኅተ ሰማይ ገዳም ዋና አላማና ራእይ ነው።
በአሁኑ ሰዓት የገዳሙን ቦታ እና አስፈላጊ የግዢ ሰነዶች ተረክበን ገዳሙን ለመንፈሳዊ አገልግሎት በማዘጋጀት ላይ የምንገኝ ሲሆን የፊታችን ሚያዝያ 13 እና 14 2015 ዓ.ም ብፁዓን አባቶች፤ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማሪያን፤ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም የክብር እንግዶች ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በሚገኙበት ቅዳሴ ቤቱ ይከበራል። እርስዎም በዚህ ታላቅ እና ታሪካዊ በዓል ላይ እንዲገኙልን የአክብሮት ጥሪያችንን እያቀረብን ከዚህ በፊት ለገዳሙ ቦታ ግዢ ላደረጋችሁት ድጋፍና አስተዋፀኦ በእግዚአብሔር ስም እያመሰገንን በቀጣይም ገዳሙ የተገዛበትን ቀሪ የብድር ገንዘብ ለመክፈል እንዲሁም የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ በድጋሚ የእርዳታ እጅዎን እንዲዘረጉ በቅዱስ ዮሐንስ እና በቅድስት አርሴማ ስም ጥሪያችችን እናቀርባለን።
ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የአንድነት ገዳም
Mitorganisatoren (9)
Saint JTBM Task Force
Organisator
Creston, CA
Gateway to Heaven Saint John the Baptist and Saint Arsema Ethiopian Orthodox Tewahedo Monastery
Spendenbegünstigte
Mulate Abate
Mitorganisator
Tersit Ceta Benvegnu
Mitorganisator
Eskinder Mengesha
Mitorganisator
Alebachew Yimer
Mitorganisator