Main fundraiser photo

Help Amdom and his Family

Donation protected
ዓምዶም ገብረስላሴ አለንልህ እንበለው!

ዓምዶም ትምህርቱን ጨርሶ ከተመረቀ ቦሃላ፣ ትንሽ ሳይሰራ ከስራ ተባረዋል፣ ከስራ የተባረረበት ዋና ምክንያት ደግሞ የዓረና አባል በመሆኑ እና በድምፂ ወያኔ ሲተላለፉ እና ሲዘገቡ የነበሩ የውሸት ዳታዎች ስላጋለጠ ብቻ ነው። ዓምዶም ከስራ ከተባረረ ቦሃላ፣ በመላው ትግራይ በመንግስትም ሆነ በግል ስራ እንዳይቀጠር በትግራይ ሚዲያዎችም እንዳይቀርብ፣ ከህወሓት ጽህፈትቤት መመርያ ወርደዋል፣ ዓምዶም እስካሁንዋ ሳአት ድረስ ተባራሪ ስራዎች በመስራት ራሱን እና ቤተሰቡን ያስተዳድራል። ዓምዶም እስካሁንዋ ሳአት ድረስ በህወሓት ደህንነቶች 65 ጊዜ ታስረዋል። 
.
ዓምዶም ከማግባቱ በፊት፣ ጓደኛው የነበረችው ያሁንዋ ባለቤቱ እና የልጁ እናት፣ ከሱ ጋር እንዳትሄድ እንዳታገባውም ጭምር የህወሓት ደህንነቶች በገባችበት እየተከታተሉ ሲነግርዋት ና ሲዝቱባት ነበሩ። ዓምዶም እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራር፣ የቀን ተቀን ክትትል የሚደረግበት ወጣት ነው። ዛሬ ወደ ቤቱ ለመግባት ሲሞክር ባለቤቱ እና የሁለት አመት ልጁ፣ ወደ ቤታቸው እንዳይገቡ ተደርገዋል። ይህ የሆነበት ዋናው ሚስጥር ደግሞ፣ በቅርቡ የተገደለው የ፸ እንደርታ ወጣት ሽሻይ ኪሮስ፣ ለምን እንደተገደለ እና በማን እንደተገደለ ሚስጥሩን በፈይስቡክ ገፁ በመፃፉ እና መላው የኢትዮጲያ ህዝብ ስላወቀ ብቻ ነው። ዓምዶም ስለ ተገደለው የ፸ እንደርታ ወጣት በመፃፉም ፖሊስ ጣብያ ትፈለጋለህ ተብሎ ተጠርተዋል። በህወሃት የተገደለው ወጣት ሽሻይ ኪሮስ የዓንዶም የሰፈር ልጅ ነው።
.
ምርጫ ካልተደረገ ብሎ የሚጮሆው አውሬው ህወሓት፣ በትግራይ የሚገኙ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች መቆምያ እና መቀመጫ አሳጥቶዋቸዋል። ዓምዶም ህወሓት በጠራው እና በረከት ስምኦን በመራው መድረክ ንግግሩ ሳይጨርስ ስብሓት ነጋ እና ተከታዮቹ በጭብጨባ ንግግሩን አቋርጠዉታል። ከለውጥ ቦሃላ ዴሞክራሲ በትግራይ ያብብባል ያለው ህወሓትም በዓምዶም ንግግር ተሸንፎዋል። ዛሬ የህውሓት ቅልብተኞች ዓምዶም የቤት ኪራይ አልከፈለም ብለው ሲሳለቁበት ውለዋል፣ በአከራይ እና ተከራይ ውል መንስግት አመታዊ ግብር መጠየቅ እንጂ፣ ይህንን ሰው አከራይ ይህንን ሰው አታከራይ የማለት መብት የለውም፣ እነ ዓምዶምን ለማሸማቀቅ የሚደረገው ትንኮሳ ግን አሁንም ቀጥለዋል፣ ባለፉት ሁለት ወራቶች አምስት መቶ ብር የቤት ኪራይ ጭማሪ እንዲከፍልም ተጠይቀዋል።
.https://www.facebook.com/nasmelash1/videos/10213071052635249
ለአስር አመታት ስራ እንዳይቀጠር፣ ቤተሰቡንም እንዳይረዳ የተደረገው ዓምዶም እንድረስለት፣ አለንልህ እንበለው፣ ለቤት ኪራይ መክፈያ የለውም ብለው ለሚያሸማቅቁት እና ከትግሉ እንዲሸሽ ለሚፈልጉት የህወሓት ደህንነቶች እኛ ኢትዮጲያውያን ከጎኑ እንዳለን እናሳያቸው እንንገራቸው። ግፉ ከዓምዶም ከባለቤቱ አልፉ፣ በሁለት አመትዋ ህፃን ልጁ ጋር ደርሰዋል። አከራዩን አስፈራርተው ከዛ ቤት ሊያባርሩት ስለሚችሉ የቻልነውን እንርዳው አብረነው እንቁም። ከዛ ቤት ወጥቶ ሌላ አከራይ ደፍሮ ያከራየዋል የሚል ጥያቄም መልስ አልተገኘለትም። ኢትዮጲያውያን ሁላችን ከኢትዮጲያዊው ዓምዶም ገብረስላሴ ጋር እንቁም።
Donate

Donations 

  • Anonymous
    • $100 
    • 4 yrs
Donate

Organizer

natnael Asmelash
Organizer
Oklahoma City, OK

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.