Main fundraiser photo

Let Us Build God’s House

Donation protected
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

 ወደ ተራራው ውጡ እንጨትንም አምጡ ቤቱንም ሥሩ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል እኔም እመሰገናለሁ ይላል እግዚአብሔር ። ትንቢተ ሐጌ 2 : 8 ::

የሚወደድ ተግባር ሳይኖረን የወደደን ፤ስንሸሸው የተከተለን፣  ከወደቅንበት ያነሳን  እግዚአብሔር አምላክ በባዕድ ሀገር ሃይማኖታችንን ረስተን ከቤተ ክርስቲያን ርቀን እንዳንጠፋ በየምክንያቱ ካህናቱን ከኢትዮጵያ እያመጣ እነሆ የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት ሳይጎድልብን ብዙ አመታትን አሳልፈናል።

          ይሁንና ልበ አምላክ ዳዊት የራሱን መኖሪያ ቤት ከታቦተ ጽዮን ማረፊያ ጋር አነጻጽሮ ቢከነክነው “ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጨአለሁ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በመጋረጆች ውስጥ እንደ ተቀመጠ እይ” (2 ነገ. 7፡2) እንደአለ የየራሳችን ቤት ኖሮን ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን እንደ ሕጉ ለቤተ መቅደስ የሚሆን ራሱን የቻለ ሕንፃ ሳይሰተካከልለት ቤተ ክርስቲያናችን ከተመሠረተ ከጥቅምት 1999 ዓ.ም እስካሁን  በኪራይ ቤት ስንገለገል እነሆ 8 ዓመታትን አስቆጠርን። 

በዚህ ልባችን የተነካ የሰበካው አገልጋዮችና ምእመናን ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ”ኑ የእግዚአብሔርን ቤት እንሥራ” (ነህ. 2፡20) የሚለውን መሪ ቃል በመያዝ  በቆራጥ ልቡና ተነሳስተን እንቅስቃሴ ላይ ብንሆንም አቅማችን ውስን በመሆኑ ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት እና ከበጎ አድራጊ የእግዚአብሔር ሰዎች የገንዘብ እገዛ እየጠየቅን እንገኛለን። ቢሰጥ የማያልቅበት እግዚአብሔር በረከቱን ያትረፍርፍልዎና ካለዎ ለታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቋሚ ማረፊያ ሕንጻ መግዥያ እገዛ እንዲያደርጉልን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በረከቱን ያድልልን።

The church officially launched its “Let Us Build God’s House” campaign on January 1st, 2015 and has collected over $60,000 up to date. The aim of “Let Us Build God’s House” campaign is to raise over $100,000 from the church members, community, and from other sources to help with the funding needed to purchase a property.


Please vist our Facebook page:
GeneteTsigeStGeorgeEOTC 

GOD BLESS!

Genete Tsige St. George EOT Church
1150 Fuller Drive, Dallas, Texas 75218 

Donations 

  • Anonymous
    • $10 
    • 9 yrs

Organizer

GeneteTsige ST George
Organizer
Dallas, TX

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.