Main fundraiser photo

በዲያስፖራ ለሚደረገው የዲፕሎማሲ ትግል ድጋፈዎትን ይለግሱ!

Donation protected
የኢትዮጵያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል እና የኢትዮጵያውያን አድቮከሲ ኔትወርክ እና አንድነት ለኢትዮጵያ ባለፈው ጊዚያት ሀገራችንን ከጆ ባይደን እና የተቀረው የምእራቡ አለም ጋዜጠኞች የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ለመታደግ የዲፕሎማሲ ዘመቻ እና የኮንግረስ እና ሴኔት ትግል ላይ አሻራዎትን ያሳርፉ ዘንድ የገንዘብ እርዳታ ማሰባሰቡ ይታወቃል።

በዚህም በርካታ መልካም ውጤቶችን ማስመዝገባችን የሚታስወስ ነው አሁንም ያንን ስራ እያሰራን እንገኛለን። ይሁን እንጂ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደገና በሀዘን ድባብ ውስጥ ገብታ ተስፋ ያደረግነው የአብሮ መኖር እሴቶች ወደ ዘረኝነትና ተረኝነት በማምራቱ የዲያስፖራውን ትግል እንዲወሳሰብ አድርጎታል። ዛሬ ኢትዮጵያውያን ድምጽ የላቸውም እኛም በማገናዘብ ለህዝባችን ምንም አይነት የዘር ቡድን ሳንለይ ድምጽ ለመሆን በአለም መድረክ ትላንት ስናደርግ እንደነበረው ሁሉ አሁንም ለዜጎች ድምጽ የመሆን ስራችንን በአለም አቀፍ መድረክ በማጠናከር ከሴኔት እና ኮንግረስ ጋር በመሆን አለም አቀፍ ህግጋት በኢትዮጵያ ይክበር ዘንድ ስራችንን ቀጥለናል። ይህንን ስኬታማ ስራ እየሰራን ሀገራችንን በዲፕሎማሲው መስክ እየተከላከልን ወደ አጥቂነት ለመሸጋገር የሚቻለንን ሁሉ በማድረግ ላይ ነን።  

ስለሆነም እንደትላንቱ የዲፕሎማሲ ዘመቻ ድጋፍ ላይ ታሪክ የማይዘነጋውን የእርሰዎትን አሻራ በድጋሜ ያሳርፉልን ዘንድ የገንዘብ እርዳታዎት ያስፈልገናል። 

ኢትዮጵያውያን በማንነታቸው ምክንያት አንገት የሚደፉበት ጊዜ በፍፁም ሊኖር አይገባም። ትግላችን ለህልውናችን በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመረባረብ የተቻለውን በገንዘብ ይረዳን ዘንድ አክብረን እንለምናለን። የኢትዮጵያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ይህንን ካለምንም ክፍያ በፍቃደኝነት ጊዚያችን መስዋእት በማድረግ ሲሰራ የእርሰዎት የገንዘብ አሻራዎትን በመተማመን ነውና እርዳታዎትን አሁኑኑ ያስቀምጡ!!!! 
Donate

Donations 

  • Anonymous
    • $100 
    • 2 yrs
  • Anonymous
    • $25 
    • 2 yrs
  • Amelework Eyasu
    • $100 
    • 2 yrs
  • Anonymous
    • $50 
    • 2 yrs
  • ISSAYAS D KEBEBU
    • $100 
    • 2 yrs
Donate

Organizer

Ethiopian American Civic Council
Organizer
Washington D.C., DC

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.