Main fundraiser photo

Bilal tv

Donation protected
አለም በወንጀል አዘቅት ውስጥ በተዘፈቀብት የሰው ልጅ የአውሬበሃሪ በተላበሰበት ውቅት አላህ ሱበሃነሁ ወተአላ ነበዩ ሙሃመድ (ሰ.አ.ወ.) ለአለማት ብርሃን ይሆኑ ዘንድ በመለእክተኝነት ላካቸው ፡፡ የኢስላም ብርሃን ዳግሞ በረሱል (ሰ.አ.ወ) ከፈነጠቀ በሁላ የመጀመሪያ ሙስሊሞች ተብለው የሚጠቀሱት ከመካ ተሰደው ወደ አትዮጵያ የመጡት ሶሐቦች (የነብዩ ሰ.ዐ.ወ ባልደረቦች) እንደነበሩ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በጣኦት ማመን እንዲቀርና አላህ(ሱ.ወ) ብቻ ማምለክና መገዛት እንዳለባቸው የተቀበሉትን ጥቂት ሙስሊሞች በመካ ከፍተኛ ስቃይና እንግልት ስለደረሰባቸው ሶሐቦቹ ወደ ሐበሻ እንዲሄዱ በታዘዙት መሰረት ለ15 ዓመታት በምድረ ኢትዮጵያ ኑረዋል፡፡ ኢትጵያ የኢስላም ብርሃን ቀዳሚ የፈነጠቀባት ከግማሽ ዜጋ በላይ ሙስሊም እንደሆነ የሚታመንባት ሀገር ናት፡፡ በኢስላም አሰተምሮ ያወቃችሁትን አነዲትም አያ ቢሆን ላላወቁት አሰተላልፉ የሚለው ሃሳብ የመረጃ መለዋወጥ ጥቅምን በገቢር የሚያሣይ ነው ፡፡ መረጃ መለዋዋጥ ለአንድ መህበሰብ የጥንካሬ ምንጭ ነው ፡፡ በተለይ በዚህ ዘመን አለም በግሎባላይዥሽን ተፅኖ በወደቅበት የመረጃ ጥቅም ከፍተኛ ነው ፡፡ መረጃን ለመለዋወጥ ደግሞ የመገኛኛ ብዙሃንን ማስፋፋት አስፈላጊ ነው ፡፡ ከመገናኛ ብዙሃን መሃከል ደግሞ በተለይ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ተፅኗቸው ከፍተኛ እየሆነ እየመጣ ይገኛል ፡፡ በሀገራችን የተለያዩ የቴሌቪዥን ሚደያዎች በተለያዩ አላማዎች እየሰሩ ይገኛሉ ፡፡ ቁጥራቸው ላቅ ያሉ ከእሰልምና ውጪ ላሉ አላማዎች የሚሰሩ ሚዲያዎች እነደ አሸን እፈሉ ይገኛሉ ፡፡ ያም ሙስሊሙን ማህበረሰብ ወደ ያልተፈለገ የስነ ምግባር ብለሸነት እነዲላበስ እደረጉት ነው ፡፡ በመሆኑም ለዚህ መፍትሄ የሚሆኑ በርከት ያሉ ኢስላምን የሚያሰተምሩ የቴሌቪዥን ሚዲያዎች ያሰፈለጉታል፡፡ ያሉት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በጣት የሚቆጠሩ በመሆናቸው ጊዜው በሚጠይቀው የመረጃ ልውውጥ ፍጥነት መሰረት በሃገርቤትም ሆነ በመላው አለም እስላምን ከቤተሰብ ከመውረስ ይልቅ ስለኢስላም ያወቀና በዲኑን በጥልቀት የተረዳ ማህበረሰብ ለመገንባት በርከት ያሉ ተለያዩ ሚዲያዎች መኖራቸው የግድ ነው ፡፡ ድርጅታችን ቢላል ሚዲያ ከተመሰረተበት 2003 ዓመተ ልደት አንስቶ ለ 9 አመታት በትጋት ሲስራ ቆይቷል ። ከኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ሰርቪስ ህጋዊ እውቅና በማግኘት በሚዲያ ስራ የተሌቭዥን ጣቢያዎች ጋር በጋራ እና በራሱ በሚያስተዳድራቸው 800 ሺ በላይ ተከታታዮች ባሏቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች ውጤታማ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ፡፡ለአብነት ያህል ከኢ.ቢ.ኤስ. ቲቪ፣ ከፋና ቲቪ ፣ከአፍሪካ ቲቪ ፣ ከዛውያ ቲቪ ጋራ የበዓላት ፕሮግራሞችን እና መደባኛ ፕሮግራሞችን በማዝጋጅት መልካም ስኬትን አስመዝግቧል ፡፡ከዚህም ባሻገር በዱባይ በተካታታይ ለስድስት አመታት የበአል ዝግጅቶችን ያዘጋጀ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያ ዘርፉም በኢትዮጵያ ከሚገኙ ማህበራዊ ሚዲያዎች ቢላል ቲውብ ቀደምቱ እና ብዙ ተከታዮች ያሉት ነው ፡፡ በዚህም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዝንዳ ተቀባነት አግኝቷል ፡፡ ስራውን በተጠናከረ መልኩ ለማከናወን እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ድምጽ የመሆን አላማን ሰንቆ ዕሰራ ይገኛል ፡፡ ይህም ሲባል ከእለት ተእለት የዳእዋ ፕሮግራሞች ባሻገር ሙስሊሙ የተሸለ የአስተሳሰሰብ አድማስ ላይ እነዲገኝ ፣ የመረጃ ጥማቱን እንዲያረካ እና በሃገሪቱ የሚገኙ ሙስሊም ማህበረሰቦች የሚደርስባቸውን መገፋት እንዲሁም ተፅኖ ለሌላው ማህበረሰብ ማሰተዋወቅ እና ስር ነቀል ለውጥ እንዲመጣ መስገንዘብ ላ ይሰራል ፡፡አለም እንደ አንድ መንደር በመረጃ የተሳሰረች እንደመሆንዋ መጠን በዚህም ቢላል ሚዲያ የበኩሉን ሚናና የኢስላምን አማና(አደራ) ለመወጣት በዘርፉ ፋዳ ያላቸው ሥራዎችን እሰራ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ እና ዱባይ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ እሥቱዲዮ እና ዘመናዊ የቀረጻ ግብአቶችን ያሟላ ሲሆን በዚህም ደረጃውን የጠበቀ የፕሮዳክሽን ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ፡፡ በሰው ሃይል አደረጃጀቱም ረጅም አመት በሙያው ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎችን እና ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎችን በማቀናጀት በተፈለገው ፍጥነት እና የጥራት ደረጃ በሃላፊነት የወሰዳቸውን ስራዎች በመከወን በጎ ምላሾችን አግኝቷል ፡፡ ስለሆነም ይህን በጎ ምላሽ በመንተራስ ወደ ቴሌቪዥን ጣቢያነት ከቢላል ሚዲያ ቤተሰቦች ጋራ በመሆን ለመቀየር በአላህ ሱብነሁ ወተአላ ፍቃድ እንሆ እንቅስቃሴ ጅመረናል ፡፡ላለፉት አመታት በማህበራዊ ድረገጾች በተለያዩ ዘርፎች ሙስሊሙን ማህበረሰብ ያገለገለው ሚዲያችንን ወደ መደበኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ ለመለወጥ ሲታቀድ የሁላችንንም ድጋፍ ይጠይቃል ፡፡ ኢሻ አላህ ይህን በጎ አላማችንን በአለማት ፈጣሪ አላህ ስም በቅርቡ እናሳካዋለን ኢንሻ አላህ ፡፡
Donate

Donations 

  • Anonymous
    • $50 
    • 4 yrs
Donate

Organizer and beneficiary

Abdurahim Ahmed
Organizer
Washington D.C., DC
Fozia Ababor
Beneficiary

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.