Main fundraiser photo

Support Artist Abebe Teka

Donation protected
ለአርቲስት አበበ ተካ ለህክምና የሚውል የገንዘብ ማሰባሰቢያ gofundme account

ድምፃዊ አበበ ተካ በሙዚቃ ህይወቱ በአሳተማቸው  የአልበም ስራዎቹ በጣም ተወዳጅነትን፣ ተደማጭነትን ፣ ታዋቂነትን የተጎናፀፈ ድንቅ አርቲስት ነው::

አበበ ተካ ፀባዬ መልካምና የፍቅር ሰው ነው ሲወድም ከእውነት ከልቡ መሆኑን አድናቂዎቹ ስለ ስብዕናው ትንታኔ አይሹም :: ቋሚ ስራው ምስክር ነው::

አበበ ተካ ሶስት ልጆቹን ብቻውን ለማሳደግ ደፋ ቀና ሲል ነጋ ጠባ በሃሳብ ሲባዝን  በ06/09/2019 እሁድ ዕለት ማታ ስራውን ሰርቶ እቤቱ በመግባት ላይ እያለ በእስትሮክ ተመታ ::

አበበ በአሁኑ ሰዓት ብዙም መናገር አይችልም ፣ ቀኝ ጎኑ ዝሏል ፣ ቀኝ እጁን ማንቀሳቀስ ተስኖታል 
በዚያ ላይ ለልጆቹ ማንም ስለሌለ በፅኑ ያስባል::

ይህ ድንቅ አርቲስት በስራዎቹ ያስደሰተን በሙዚቃ ጥበቡ ፍቅርን የሰበከን የፍቅር ፅናትን ያስተማረን አርቲስት ዛሬ በሆስፒታል አልጋ ላይ ሆኖ የህክምና ክትትል እያደረገ ይገኛል::

ስለሆነም በመላው ዓለም ለምትገኙ አድናቂዎቹ በሙሉ እንዲደርስ  Gofundme account   ከፍተን ልከናል::

ይህንን ድንቅ አርቲስት ከገጠመው ህመም እንዲያገግም ቅን የምታስቡ መላው አድናቂዎቹ በሙሉ ዛሬ አይዞህ የምትሉበት ፣ የምታፅናኑበት ፣ የምትታደጉበት መስኮት Gofundme account  ቀጥሎ የምትመለከቱት ነው::

ልቦናችሁ የፈቀደውን አድርጉ እንደየ እምነታችሁ በፀሎታችሁም አትርሱት::

እግዚያብሄር ይስጥልን 

ከቤተሰቦቹና ከሙያ ጏደኞቹ!


 
 

Organiser and beneficiary

Yehunie Belay
Organiser
Hayfield, VA
Abebe Teka
Beneficiary

Your easy, powerful and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help straight to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.