Main fundraiser photo

ሰለሞንና ልጆቹን እንታደግ! Let's Save them!

Donation protected
ሰለሞን ተሰማ ይባላል:: ምርጥ የጠረጴዛ ኳስ ተጫዋች ሲሆን የሐረሪ ክልልን በመወከል ሃገሪቷ ውስጥ በተካሄዱ የተለያዩ ውድድሮች በመሳተፍና ሻምፒየን በመሆን ችሎታውን ያስመሰከረ የከተማዋንም ስም ያስጠራ ድንቅ ተጫዋች ነው:: የከተማዋ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በተለይም እግር ኳሱ ወደተሻለ ደረጃ እንዲያድግም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የሚለፋ ነው:: የከተማዋን ወጣቶች አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ በመሰብሰብና በማሰልጠን ለዚህ እንቅስቃሴው እንዲረዳውም ለስፖርቱ ካለው ፍቅር የተነሳ ድጋፍ ለማግኘት ሰው ፊት ቆሞ ገንዘብ በመለመን ወጣቶቹ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ የረዳ ቅን አሳቢ እና መልካም ሰው ነው::

ሰለሞን በአሁኑ ወቅት ሁለት የሶስት ዓመት መንታ ህፃናት ልጆቹ ሃይድሮ ሴፍሊስ በሚባል በሽታ ተጠቅተውበታል:: የዚህ ዓይነት በሽታ ተጠቂ የሆኑ ህፃናት ጭንቅላታቸው የሰውነታቸውን ውሃ ወደ ራሱ የመሰብሰብ ባህሪ ስላለውና እድገቱም ፈጣን በመሆኑ ህፃናቱ ጭንቅላታቸውን መሸከም አይችሉም:: በዚህም የተነሳ ህፃናቱ መቆምም ይሁን መቀመጥ አይችሉም:: በህክምናው በኩል ያለው የመጨረሻው አማራጭ ጭንቅላታቸው ላይ ከባድ ቀዶ ጥገና በማድረግ ቱቦ መቅበርና ውሃው ከጭንቅላታቸው ወደ ሆዳቸው እንዲፈስ ከተደረገ በሗላ በቆሻሻ መልክ ከሰውነታቸው እንዲወገድ ማድረግ ብቻ ነው:: ህክምናው ለማድረግ እጅግ በጣም ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ ሲሆን ሰለሞን እስካሁን ያለው ጥሪቱን አሟጦ በመጠቀሙ ከዚህ በሗላ ህፃናት ልጆቹን ለማሳከም አቅም የለውም:: ህፃናቱ በፍጥነት ቀዶ ጥገናው ካልተደረገላቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው:: ሌላው አሳዛኝ ነገር ቢኖር ከጭንቀት የተነሳ ራሱ ሰለሞን የስኳርና የደም ግፊት ታማሚ ሆኗል:: በአጠቃላይ ቤተሰቡ ስቃይ ላይ ነው::

ሰለሞን የእኛን ዕርዳታ በእጅጉ ይሻል:: በተለይም በመቦረቂያ ዕድሚያቸው በከፍተኛ ህመም ስቃይ ውስጥ ያሉት ህፃናት ህይወት መታደግ ከእግዚአብሔር ጋር የሁላችንም ኃላፊነት ነው:: በመሆኑም ይህን መልዕክት የምናነብ ሁሉ የአቅማችንን በመርዳት ህፃናቱ አፋጣኝ ህክምና አግኝተው ወደ ጤናቸው እንዲመለሱ የበኩላችችን እንድንወጣ በልዑል እግዚአብሔር ስም ተጠይቋል::

Solomon Tesema is a spectacular tennis player. He has represented the city of Harar and Harari region in various tennis tournaments and won championship titles. Besides playing tennis, he is an avid soccer personality in Harar city. He coaches and supports soccer players by fundraising for their expenses and contributed his part in the success of significant number of soccer players and youth. He is known for his willingness to help. Currently Solomon is in a difficult situation; his twin daughters are sick with Hydrocephalus, which is the build of fluid(water) in the cavities deep within the brain. As a result, they cannot sit, stand or walk. The only resort is to have a surgical operation to build a duct that brings the fluid back to the body to the digestive system. If they don’t get the surgical treatment immediately, their life is in danger. Solomon has exhausted all his money for their treatment so far. The surgical procedure costs hundred thousand of Ethiopian Birr. The worse thing is Solomon is getting sick as well with Hypertension and diabetics while taking care of his kids. Solomon need our financial support to cover his daughter’s surgical procedure cost. Please, chip in your part and share it in your social media pages, so that we can help his family. God bless you and thank you for your help.

My name is Zeleke Tsegaye Werssa. I am originally from Ethiopia. Now,  I live here in United states. Solomon Tessema, who I am raising funds for, is a friend of mine. The funds raised will  explicitly be used to undergo surgical operation for the twin kids of Solomon.  I am planning to send the money to the beneficiary via wire money transfer services.

Organizer

Zeleke Tsegaye
Organizer
Silver Spring, MD

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.