Main fundraiser photo

የወንድማችን የዘማሪ አሸናፊ ጉልቲ ሸክምን የመጋራት ጥሪ!!

Donation protected
የጌታ ሰላም እና ፍቅር በያላችሁበት ይብዛላችሁ!! ወንድማችን ዘማሪ አሸናፊ ጉልቲ በብዙ ዝማሬዎች እና አገልግሎቶቹ የተባረክንበት አራት ሙሉ አልበሞች እና ሶስት ነጠላ ዝማሬዎችን ከጌታ በመቀበል በኢትዮጵያ እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ በተለያዩ ቤተክርስቲያናት በመዘዋወር እንዲሁም በቋሚነት በቤሪያ የፀሎት አገልግሎት: በኤልሻዳይ ቴሌቭዥን ኔትወርክ: በዲሲ መካነ ኢየሱስ እያገለገለ ሚገኝ ሲሆን በተለይ ;- " ክርስትና ቢሉት ክርስቶስ ነው: ክርስቲያን ነኝ ካሉመኖር ነው" በሚለው ዝማሬ የማያውቀው አለ ብየ አልገምትም:: አሹ ቅን እና እሩህ ሩህ የእግዚአብሔር ሰው : በጌታ ቤት ጠዋት ማታ: ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይል ሲያገለግል የቆየ ሲሆን አሁን ከቅርብ
ዜ ወዲህ በከባድ ችግር እና ፈተና ውስጥ እያለፈ ይገኛል:: ሁላችንም በተለያዩ ፈተናዎች የምናልፍ ቢሆንም አንዳንዶቻችን ላይ ፈተናው ይከብዳል:: ስለሆነም ወንድማችን, ከሰባት ወር በፊት ወንድሙን አውሮፓ ድረስ በመሄድ ሲያስታምም የቆየ ሲሆን ወደ ሚኖርበት አገር ተመልሶ ወደ አገልግሎቱና ስራው ከመመለሱ አንድ ወር ባልሞላ
ዜ ውስጥ ወላጅ እናቱ ኢትዮጵያ ውስጥ በጠና መታመማቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ባለሆስፒታል ከማህፀናቸው ዕጢ የወጣላቸው ቢሆንም ከዛም በኃላ አለመሻላቸው ተከትሎ በሽታቸው በውል ተለይቶ ባለመታወቁ ወደ አሜሪካ ሀገር መምጣት ግድ ሆነባቸው:: አሜካን ሀገር ባለ ህክምና ሲረዱ የመሀፀን ካንሰር መሆኑ እና ካንሰሩም በፍጥነት እየተሰራጨ በመሆኑ በፍጥነት ኪሞ ህክምና ጀምረው በተደጋጋሚ ኪሞውን ወሰዱ ይሁን እንጅ ኪሞውን መሸከም ስላልቻሉ እየተራመዱ ከአገራቸው የወጡ እናት ዛሬ ላይ መንቀሳቀስ:መናገር ሁሉ ተስኗቸው ሙሉ በሙሉ በሰው እጅ ላይ ወደቁ:ሆስፒታሉም የሚያደርገውን ሞክሮ ከአቅሙ በላይ እንደሆነ እና ካንሰሩም ሙሉ በሙሉ ሰውነታቸውን እየተቆጣጠረው በመሆኑ የኪሞ ህክምናውን አቋርጠው ከሆስፒታል አስወጧቸው:: አሹ, ሆስፒታሉን በመለመን እርዳታ እንዲደረግለት ቢጠይቅም በየሁለት ሳምንት ሆዳቸው ውስጥ የሚሞላውን ውሀ እየቀዱላቸው እና ካንሰሩን ባለበት ቦታ እንዲቆይ የሚያስችል ማስታገሻ እየተሰጡ የቆዩ ቢሆንም አሁን ግን ሁሉም ነገር ከአቅም በላይ እየሆነ መጣ:: ከህመማቸው ጋር ተያይዞ የመጡትን ችግሮች በሙሉ አሹ ብቻውን
ወጣ አልቻለም:: እናቱን በየ30 ደቂቃው ማገላበጥ, መንከባከብ ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ ባለማድረጉ የሚሰራበት መስሪያቤት ከሆስፒታል የተላከላቸውን የትብብር ደብዳቤ ወደ ጎን በመተው ከስራ አገዱት:: እስከ ዛሬ ድረስ እንደምንም በራሱ መንገድ ካለማንም እርዳታ ነገሮችን ለመፍታት ቢሞክርም ነገሮች በሙሉ መልካቸውን በመቀየር እና ሌላ ተጨማሪ ችግር በመፍጠር ሁኔታዎችን አባባሱት:: በአሁኑ ሰአት እናቱን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ የተደረገው ሙከራ አየር መንገዱ አሁን ባሉበት የጤንነት ሁኔታ እንደማይችሉ ገልፀዋል:: እዚህ አሜሪካን ሀገር መቆየታቸው ደግሞየበለጠ ችግር ነው:: በዚህም ምክንያት ስራውን መስራት ያልቻለው አሹየ ለከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ተዳርጏል:: አሜሪካን ሀገር እንኳን ስድስት(6) ወር ቀርቶ አንድ ቀን እንኳን ካልሰሩ የማይኖርበት አገር እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን:: ከዚህ ጋር ተያይዞ እናቱም ለህክምና ስለመጡ የመኖሪያ ፍቃድም ስለሌላቸው ለህክምና ሚወጣው ወጭ የሚረዳው አካል ስለሌለ: ከሌሎች ወጭዎች ጋር ተደምረው ለከፍተኛ ጭንቀት ዳርጎታል:: ወገኖች ዛሬ ከወንድማችን ጎን የምንቆምበት
ዜ ነው:: እስከዛሬ በፀሎት እያገዛችሁ ያላችሁ ወገኖች እግዚአብሔር ይባርካችሁ! አሁንም በፀሎትም በገንዘብም እንደግፈው ስል በጌታ ፍቅር ጥሪ አቀርባለሁ!! ብሩካን ናችሁ!! Ashenafi phone number [phone redacted]

Ashenafi that many of us know from his wonderful gospel songs needs our financial help and the need is very urgent.
Donate

Donations 

  • Anonymous
    • $35 
    • 3 yrs
Donate

Fundraising team: Ashenafi Gulti & Mimi Tesfaye (3)

Meskiyos Melaku
Organizer
Silver Spring, MD
Ashenafi Debaba
Beneficiary
Ashenafi Debaba
Team member
Mimi Tesfaye
Team member

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.