Main fundraiser photo

Help us defend our Church

Donation protected
የአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራልን በህግ ፊት እንታደግ ዘንድ የቀረበ የእርዳታ ጥሪ።
ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል በስደተኛ ኢትዮጵያውያን በ1987 እ.ኤ.አ ተመሰረተች። ብዙ ፈተናዎችንም በማለፍ በአባት እርዳታ በልጆችዋ ትጋት እና በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተራዳዒነት ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን የሚያኮራ ካቴድራል እስከመገንባትም ደረሰች። ዛሬ ግን በቤተክርስትያናችን ስር ተሰብስበን ለሀገራችን ሰላም መፀለይ በሚገባን ሰዓት ፤ ስለልጆቻችንን የወደፊት ህይወት እና ስለቤተክርስቲያኗ እድገት መትጋት በሚኖርብን ወቅት ካቴድራላችንን እና ማህበረ ምዕመናንን ያገለግሉ ዘንድ በተደጋጋሚ የመረጥናቸው የቦርድ አባላት ከኢትዮጵያዊ ስነ ምግባር በራቀ ድርጊት እመቤታችንን እና አገልጋይ ልጆችዋን አሳዝነዋል። ከሀያ ሁለት ዓመታት በላይ ያገለገሉንን ብፁዕ አባት አቡነ ያዕቆብን ሕገ ደንብ ጥሰው ለማሰናበት ከመወሰን አልፈው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ቀኖናዋን እና ትውፊትዋን ለማዳን የተሰደደውን እና የሁላችንም ተስፋ የሆነውን የህጋዊውን ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ አንቀበልም እስከ ማለትም ደረሰዋል።
በሚያሳዝን ሁኔታ በሎንዶን እና በዋሺንግተን የታየውን ሴራ በአትላንታም ሊደግሙት ከጅለዋል። እኛ በስደት የምንገኝ የካቴድራሉ አባላት ደክመን እና ለፍተን ለቤተክርስትያናችን መንፈሳዊ አገልግሎት ያስቀመጥነውን ገንዘባችንን ያለ ምእመናን ፍቃድ ኮረም የማይሞሉ የቦርድ አባላት ከመቶ ሺ ዶላሮች በላይ በማውጣት ለእኩይ ተግባራቸው የኮሮፖሬት ጠበቃ ቀጥረዋል። ወገኖቻችን፤ ዛሬ ህዝባችን በአምባገናዊ የመንግስት ስርዓት እያተሰቃየ ይገኛል። እዚህ ነፃነት እና የህግ በላይነት ባለበት የስደት ሀገራችን ላይ ሊሰፍን የሚሞከርን አምባገነናዊ ስርዓትን ግን በጋራ እውነትን ይዘን ልንታገለው ይገባል። በተለይም በያዝነው ጾመ ማርያም ወቅት በጾም፣በጸሎት ከመትጋት ጋር ትሩፋትንም ጨምራችሁ ለዚህም የተዘጋጀውን የህግ አገልግሎት ፈንድ ለመርዳት የበኩላችንን እንወጣ ዘንድ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም እንማፀናለን።
ከዚህ በፊት በለገሳችሁን እርዳታ የህግ ጠበቃ ቀጥረን፤በብጹእ አባታችን፣በስምንቱ በቦርድ አባላት እና በአባላት ላይ የተሰመረተውን መሰረተ ቢስ ክስ ተከላክለን ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በአባላት እንዲወስንና ስብበሰባው የሚከታተል በሰዓት $350 በጋራ የምንከፍለው ሞግዚት መድቦልናል። ለጠበቃ እና ለህግ አዋቂው ሞግዚት የሚከፈለው በመቀጠሉ ዳግመኛ እርዳታችሁን እንሻለን።የሚኖርዎትን ጥያቄ በአግባቡ እንመልስ ዘንድ የስልክ ቁጥርዎን ወይም የኢሜይል አድራሻዎትን ያሳውቁን እና ስለጉዳዩ ያለውን መረጃ ሁሉ (በተለይም የሚሰበሰበውን የእናንተው የገንዝብ እርዳታ አስመልክቶ) በወቅቱ እናደርሶታለን።
At a time our people back in Ethiopia are suffering from historical challenges, certain elected board members of the Cathedral have illegally attempted to terminate our archbishop Abune Yaekob, who has been serving our church for over two decades. Moreover, these individuals repeatedly failed to implement our Holy Synod directives and undermined the very nature of our Holy Synod in exile. Dear brothers and sisters, we are saddened to see what happened in London, England and Washington D.C. is now repeating itself in Atlanta. On the top of that, they are wasting thousands of dollars by suing their fellow board members and Abune Yaekob in a civil court.
Brothers and sisters, in the name of our God the almighty, and Sealite Mihret Kidist Mariam, we ask your help to support the legal fund that we have established for this cause. If you give us your number, we will be glad send you up to date information about the status of the case, financial disclosure and other information. Because it is your case too. If you have any questions, please do not hesitate to contact us.
Concerned Members of Sealite Mihiret Kidist Mariam Church
Donate

Donations 

  • Ayalnesh Kide
    • $50 
    • 7 yrs
Donate

Organizer and beneficiary

Atlanta Kidist Mariam
Organizer
Atlanta, GA
Yohannes Alemayehu
Beneficiary

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.