Main fundraiser photo

ኢትዮጵያዊያን ሆይ! ኑ የእግዚአብሔርን ቤት እንስራ!

Donation protected
 በፍራንክፈርት ከተማ እጅግ ግዙፍ ቤተ ክርስቲያንና ማእከል የሚሆነው የገዛነው ሕንጻ በፊትለፊት  ሲታይ ይህንን ይመስላል፡፡


ኑ ቤቴን ሥሩ እኔም በርሱ ደስ ይለኛል ይላል እግዚአብሔር“ ት.ሐጌ ፩፣፰  




ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር እንዲሉ በመድኃኔዓለም ቸርነትና መልካም ፈቃድ፣ በካህናትና ምእመናን ትብብርና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከረጅም ዓመታት ያላሰለስ ጥረት በኋላ እነሆ በጀርመን ሀገር በፍራንክፈርት ከተማ እጅግ ግዙፍ ቤተ ክርስቲያንና ማእከል የሚሆን ሕንጻ መግዛታችንን በቅድሚያ ለመላው ኢትዮጵያውያን እናበስራለን፡፡
ይህ ቤተ ክርስቲያን አምልኮት የምንፈጽምበት ቅዱስ ቦታ ከመሆኑም በተጨማሪ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ደስታውንም ሆነ ሀዘኑን በጋራ የሚወጣበት፣ ሕጻናት ሃይማኖታቸውን፣ባህላችውንና ቋንቋቸውን የሚማሩበት በአጠቃላይ በውጭ ሀገር ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ቋሚ አድራሻና የሚያኮራ የታሪክ ቅርስ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

ይህን ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ከነበረው ከፍተኛ ውጣ ውረድ ባሻገር ለብዙ ዘመናት ምእመናን ያዋጡትን ገንዘብ ባንኩ ምንም ሳያስቀር ከብድር ውላችን ጋር ስላሰበው በአሁኑ ወቅት ቋታችን ባዶ መሆኑን ለመግለጽ ተገደናል፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያኑ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጥ ውስጣዊ ይዞታውን ማለትም መንበሩን፣ ቤተ መቅደሱን፣ ምንጣፉን፣ የድምጽ ማጉሊያውን፣ ወንበሮቹን፣ ኤሌክትሪኩን፣ ቀለሙንና አጠቃላይ እድሳቱን ወዘተ ለማሟላትና ወርሃዊ ዕዳውን ለመክፈል በርካታ ገንዘብ አስፈላጊ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ በዚህም መሠረት ይህ ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ አድራሻ፣ ቅርስና ማእከል በመሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሚችለውን ዕርዳታ እንዲለግስና የታሪክ አሻራውን እንዲያኖር ቤተ ክርስቲያን በመድኃኔዓለም ስም ጥሪዋን ታቀርባለች፡፡

Organizer

Sami Ze Nega
Organizer
Frankfurt

Inspired to help? Start a fundraiser for someone you know

Help someone you know by raising funds and getting their support started.

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.