Main fundraiser photo

Rehabilitation of Affected Eth. Soldiers & Family

Tax deductible
Join us and make a difference in rehabilitating the wounded soldiers of Ethiopia and their families. Some families lost their bread winners and others are wounded on the campaign of restoration of peace and security in various conflicts in Ethiopia. These families need our help.



  “ለሀገሬ ስታገል ለድንበሯ
   ተኝቻለሁ እኔ ከአፈሯ፤
    የትግል ታሪኬን ስታወሱ
    ቤተሰቦቼን ግን እንዳትረሱ!”
    ጥላሁን ገሠሠ

ሀገራችን ኢትዮጵያ በረጅም ግዜ ታሪኳ እልፍ አእላፋት ኢትዮጵያውያን ልጆቿ መተኪያ የማይገኝለትን ውድ ሕይወታቸውን መስዋዕትነት ከፍለው ሉአላዊነቷ ተከብሮ፤ዳር ድንበሯ ተጠብቆ ለመቆየቱ ታሪክ ምስክር ነው። የኢትዮጵያ ሕልውና በውድ ሊጆቿ ደምና አጥንት ለምልሞ የቆየ ውድ የትውልድ ውርስ ነው።

በቅርቡ ሀገራችን ውስጥ እየተካሄደ የነበረውን የፖለተካ ቅራኔ በሰለጠነና በሰላማዊ መንገድ መፍታት ባልፈለጉ ሃይሎች ቆስቋሽነት ከሕግና ሥርአት ባፈነገጠ መልኩ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት፤ ብሎም በሀገራችን ህልውና ላይ እጅግ ከባድ የማፈራረስ አደጋ ተጋርጦ እንደነበረ አናስታውሳለን። ይህ አደጋ በሰሜን እዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የተቀነባበረና አሰቃቂ ጥቃት በመፈጸም የተጀመረ ሲሆን ከአደጋው የተረፈው ሠራዊት ራሱን እንደገና አቋቁሞ በሰነዘረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ታላቅ መስዋዕትነት ከፍሎ ድል መቀዳጀቱ ይታወቃል።

ይህ የመከላከያ ሠራዊት ከሕዝባችን በፊት ቀድሞ መስዋዕት በመሆን የሀገሩን ዳር ድንበርና አንድነት በማስከበር ሂደት ውስጥ ህወሓቶች ’’መብረቃዊ ጥቃት’’ ካሉት የክህደት እርምጃ ጀምሮ በተጋፈጠው የሕግ ማስከበር ውጊያ ውስጥ አያሌ አባላቱ መስዋዕት ሆነዋል። በሺህ የሚቆጠሩ ቆስለዋል፤ አካለ ጎደሎ ሆነዋል። የአያሌ ወታደሮች ትዳር ፈርሶ ሚስቶች መበለት፣ ብዛት ያላቸው ሕጻናት ደግሞ ወላጅ አልባ ሆነዋል።

ይህ የጦርነቱን ገፈት ቀማሽ የሆነው መከላከያ በአጭር ግዜ ውስጥ ድልን ተቀዳጅቶ ሕግና ስርዓት የማስከበር ግዳጁን የተወጣው በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደጀንነትና ጸሎት መሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም። ሕዝባችን ከዳር እስከ ዳር ተንቀሳቅሶ በምግብ፣ በአልባሳት፣ በሕክምና በገንዘብና በሞራል እንደ አንድ ሰው በመሆን ሠራዊቱን መርዳቱ በአጭር ግዜ ውስጥ የተፈጠረውን ሀገራዊ አደጋ አስቀርቶታል።

መከላከያ ሠራዊታችን በደረሰበት የክህደት ጥቃት የተነሳ የደረሰበት የህሊና ጠባሳ በቀላሉ የሚፈወስ አይደለም። ለሀገሩ ዘብ ቆሞ የተሰዋ ወታደር ልጆችና ቤተሰቡ ከአደጋው አገግመው ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ተመልሰው እንዲገቡ የሚያስችል ከፍተኛ ወገናዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። አካሉ የጎደለ የመከላከያ አባል ለማገገም እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሞራልና የፋይናንስ ድጋፍ ያስፈልገዋል። ይህንን ድጋፍ ማድረግና አይዞህ ማለት የሚገባን ደግሞ እኛ የኢትዮጵያ ዜጎችና ወዳጆች ነን።

ሀገራችን ላይ የተቃጣው ጥቃት ይህ ብቻ አይደለም። በዚህ በአሁኑ ሰአት በሱዳን በኩል ያለው ድንበራችን ተጥሶ የመከላከያ ሠራዊታችንን ግዳጅ የበለጠ አክብዶታል። ይህ በሀገራችን የውጭና የውስጥ ጠላቶች በጋራ የተቀነባበረ አፍራሽ ትንኮሳ እንዲከሽፍ በግንባር ቀደምትነት መስዋዕትነቱ የሚጠበቀው ከዚሁ ከጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ነው።

በየአካባቢው የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ይህንን ሀቅ በመረዳት ለመከላከያ ሠራዊታችን የሞራል ድጋፍ የሚሆን እርዳታ በማሰባሰብ ላይ ናቸው። እኛም የሴንት ሉዊስ ኗሪዎች ይህንኑ የደጀንነት ግዴታ መወጣት እንዲሚጠበቅብን በሚገባ እንረዳለን።

     “ሁሉም ጥቂት ሰጠ፣ ጥቂቶች ግን ያላቸውን ሁሉ ሰጡ!”
     “All gave some, some gave all.”

 እንደሚባለው ብሂል መከላከያ ሠራዊቱ መተኪያ የማይገኝለትን ሕይወቱን በመስዋዕትነት ሲከፍል እኛ በምንችለው አቅማችን ጥቂት ጥቂት በመርዳት የሞራል አቅም እንድንሆነው በዚህ የድጋፍ ማሰባሰቢያ (GoFundMe) ዘመቻ እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጠይቃለን።

Ethiopian Community of Greater St. Louis

Donations 

  • Asegidew Wolle
    • $200 (Offline)
    • 3 yrs
  • Esayas Mamuye
    • $100 (Offline)
    • 3 yrs
  • Ayele Belayneh
    • $200 (Offline)
    • 3 yrs
  • Daneil Bekele
    • $500 (Offline)
    • 3 yrs
  • Getahun Abate (Dr)
    • $500 (Offline)
    • 3 yrs

Organizer

Ethio Stlu
Organizer
Olivette, MO
Ethiopian Community Association of Greater Saint Louis
 
Registered nonprofit
Donations are typically 100% tax deductible in the US.

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.