Main fundraiser photo

Let Us Save The Lives of Kidney Patients

Donation protected
 

Dire Dawa is a city in Ethiopia with more than 500,000 population. Many are becoming sick with kidney failures. However, there are about 3 dialysis machines to serve the population. All hospitals, except one, lack dialysis machines.
 
The people of Dire Dawa are organizing this fundraising event to fund the fight against kidney disease, by purchasing the right number of dialysis machines proportional to the population of Dire Dawa; there by, alleviate the unbearable medical costs of dialysis procedures to many.
 
Let us all unite and zealously support this worthy cause by donating what we can today.
 
Our sincere and endless thanks to all of our supporters.
 
                                                              ______________________________ ////////////_________________________________

የዳያሌሲስ ማድረጊያ ማሽን ለድሬ ዳዋ ኩላሊት እጥበት ታካም የሕብረተሰብ ክፍል ለምን ያስፈልጋል?
 
ከ500 ሺህ በላይ ነዋሪ በላይ ያላት ከተማ ላይ ከአንድ ግለሰብ ሆስፒታል ከሚገኝ የዳያሌሲስ አገልግሎት ከሚሰጥ ሆስፒታል ውጪ በመንግስት የሕክምና ተቋማት ውስጥ አይገኝም::
 
በመሆኑም አንድ የኩላሊት አለመስራት (Kidney Failure) ያጋጠመው ታካሚ ቢያንስ በሣምንት ሦስት ጊዜ እንዲታጠብ (ዳያሌሲስ) እንዲያደርግ ይመከራል:: ለአንድ ጊዜ በአሁኑ ወቅት በግል የሕክምና ተቋም ለመታጠብም በቅድሚያ ብር 13,500.00 (አስራ ሦስት ሺህ ብር) ቅድሚያ በማስያዝ ለመታጠብ ብር 2,500.00 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ተጨማሪ ለእጥበቱ የሚሰጡት መዳህኒቶችን ለመግዛት ብር 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ) በድምሩ ለአንድ ጊዜ እጥበት ብቻ 4,000.00 (አራት ሺህ ብር) ያስፈልገዋል:: በሣምንት ሦስት ጊዜ ሲታጠብም 4,000.00 X 3= 12,000.00 ያስፈልገዋል ማለት ነው:: በወር ደግሞ ስናሰላው ወደ ብር 48,000.00 ያስፈልገዋል::
 
ይህ አሁን በመንግስት: በባለሃብቱ: በዳያስፓራ ማህበረሰቡ ሊገዛ የታቀደው የዳያሌሲስ የሕክምና መርጃ ማሽን ዋጋው ከ $8,000 USD እስከ $17,000 USD የሚገመት ሲሆን ግዢው ቢሳካ በከተማዋ ወሳኝ ቦታ በማድረግ ለነዋሪው ሕብረተሰብ በጣም በዝቅተኛ ዋጋ በቀን ቢያንስ ከ5 - 10 ለሚሆኑ ሕሙማን እንዲሰጥ ለማስቻልና አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል የሁሉም ሰብዓዊ ፍጡር የሆነን ሁል ድጋፍ ስለሚሻ ይህ የጎ ፈንድሚ ገቢ ማሰባሰቢያ ተከፍቷል::
 
በኩላሊት አለመስራት ችግር የሚሰቃዩ ወገኖችን ተገቢውን ሕክምና በተገቢው ዋጋ ያገኙ ዘንድ የእርስዎ ድጋፍዋጋው ከፍተኛ ነው::
 
በአገራችን አባባል እንደሚባለውም "ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም" እና ወገኖትን ይርዱ: ይደግፉ...ለሰዎች ሕይወት መትረፍ ምክንያት ይሁኑ‼️
Donate

Donations 

    Donate

    Organiser

    Dole Omer
    Organiser
    Houston, TX

    Your easy, powerful and trusted home for help

    • Easy

      Donate quickly and easily

    • Powerful

      Send help directly to the people and causes you care about

    • Trusted

      Your donation is protected by the GoFundMe Giving Guarantee