Main fundraiser photo

help seada mohammed formedical exp

Donation protected
ስሞት አታልቅሱ

ደራሲ፣ ጋዜጠኛ፣ጸሐፊ ተውኔት፣ ገጣሚ እንዲሁም ሁለገብ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ሰዓዳ መሐመድ በኩላሊት ሕመም እየተሠቃየች ነው፡፡

በ1990ዎቹ መጀመሪያ በኢትዮጵያ ሬዲዮ የቅዳሜ መዝናኛና ለወጣቶች ፕሮግራም ድራማ በመጻፍና አጫጭር ጽሑፎችን በማቅረብ የጥበብን ደፍ የረገጠችው ሰዓዳ ፣በዕለታዊ አዲስ ፣በሩሕ ፣በአልነጃሺ፣በአልዋህዳ ጋዜጦች በሪፖርተርነት በአዲስ አድማስ፣በእፎይታ ጋዜጣና መጽሔት በርካታ ጽሑፎችን አስነብባናለች፡፡

"እሾሃማ ወርቅ" የተሰኘ ቤሳ ልቦለድ በማስነበብም የደራሲነት ክህሎቷን አስመስክራለች፡ ይህ መጽሐፏ በርካታ ጥናትና ምርምር አድራጊዎችን የሳበ ነበር፡፡ በ"እፍታ" መጽሐፍ ከቁጥር ሁለት ጀምሮ ባሉ ተከታታይ መጽሐፍት ድርሰቶቿን አስነብባለች፡፡ ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ባሳተማቸው መጽሐፍትም የሷ ድርሰቶች ተካተዋል፡፡ ሰዓዳ ብዕረ ብርቱ ደራሲ ነች፡፡ በተለይ በድራማ አጻጻፍ የተካነች ሆና ብቅ ብላለች፡፡ በቴሌቪዥን ና የሬዲዮ ድራማዎች የሷ እጅ ያላረፈባቸው የዘመኑ ድርሰቶች ጥቂት ናቸው ማለት ይበቃል፡፡
ከ191-1996 በኢዶች የተለያዩ ድራማዎችን በመጻፍ ሥራዎቿ በቴሌቪዥን ፣በመድረክ ቀርቧል፡፡ ሰዓዳ ሁለገብ የጥበብ ሰው ነች፡፡ በ"ዘመን" የቴሌቪዥን ድራማና "በቤት ሥራ" ድራማ ላይ ከጸሐፊዎቹ አንዷ ነች፡፡

ወደፊት ብዙ ለመሥራት እየተዘጋጀች ሳለ የኩላሊት ሕመም ሆስፒታል እንድትምላለስ አድርጓታል፡፡ አሁን የዳያሌሲስ ሕክምና እያካሄደች ነው፡፡ ሐኪሞች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሊደረግላት ይገባል ብለዋል፡፡ ሕክምናውን ለማካሄድ ከፍተኛ ገንዘብ ተጠይቃለች፡፡ ገንዘቡን የመሸፈን አቅም ደግሞ የላትም፡፡ ሁላችሁም ጓደኞቼ ከንፈር ከመምጠጥ ታቅባችሁ እህታችንን እንታደጋት ሕይወቷን እናድን ፣የአቅማችንን እናድርግ፡፡

Donations 

  • Alt Abera
    • $30 
    • 6 yrs

Organizer

idris A idris
Organizer

Inspired to help? Start a fundraiser for someone you know

Help someone you know by raising funds and getting their support started.

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.