Main fundraiser photo

Dr.Bahiru Legesse's Final Treatment

Donation protected
ለቀዶ ህክምና ሀኪሙ ዶ/ር ባህሩ ለገሠ የቀረበ የእርዳታ ጥሪ
.
ዶ/ር ባህሩ ለገሠ በቀለ በደቡብ ክልል ዳዉሮ ዞን የተወለዱ ሲሆን ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ 1996 ዓ.ም ጂማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት ገብተው የህክምና ትምህርታቸውን በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቀዋል።
.
ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ለማገልገል ታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል በጠቅላላ ሐኪምነት ተቀጠሩ። በጊዜው ብቸኛ ሐኪም ሆነው የውስጥ ደዌ ፣ የቀዶ ህክምና ፣ የህፃናት ህክምና እንዲሁም የማህፀንና ፅንስ ህክምናን በላቀ የሥራ ተነሳሽነት ሰጥተዋል።
.
ከሁለት ዓመት የጠቅላላ ሐኪምነት ቆይታቸው በኋላ የጠቅላላ ቀዶ ሐኪምነት ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን አዲስ አበባ ህክምና ትምህርት ቤት አጠናቅቀው ዳግም ወደ ታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ተመልሰዋል።
.
ከስፔሻሊቲ ትምህርት ከተመለሱም በኋላ በጠቅላላ ቀዶ ሐኪምነት ባገለገሉበትም ወቅት በድንገተኛ ፣ ተመላላሽና ተኝቶ የቀዶ ህክምና አልፎም ሌሎች የህክምና ዘርፎችን በመደገፍ ከፍተኛ አገልግሎቶችን ለዳዉሮ ዞንና አጎራባች ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ሕዝቦች ቢያንስ ለ13,422 ተመላላሽ እና 2,435 ተኝቶ ህክምና ታካሚዎች አገልግሎት ሰጥተዋል::


ባላቸው ትንሽ ትርፍ ጊዜ የግል ክሊኒክ በመክፈት በሆስፒታሉ በተለያዩ ምክንያት አገልግሎት ለማግኘት የሚቸገሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በህክምናቸው ሲደርሱ ቆይተዋል ፤ ብዙ ድሆችንም በነፃ በማከምም ይታወቃሉ:: በዚህም በአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማህበረሰብ ዘንድ እጅጉን ተወዳጅና በልባቸውም በክብር የሚታወሱ ሐኪም ናቸው::
.
ነገር ግን እጅግ በሚያሳዝን መልኩ በቀን 14/01/2011 ዓ.ም በታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ለነበራቸው ሥራ ለመድረስ ከሐዋሳ ወደ ወላይታ ሶዶ ባቀኑበት ወቅት ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
.
በመሆኑም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ቲችንግ ሪፈራል ሆስፒታል ፣ በሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ፣ በኮሪያ ሆስፒታልና በአሌርት ሆስፒታል ሲረዱ ቆይተው ለተሻለ ህክምና በታይላንድ ወደሚገኘው ቡምራን ግራድ ሆስፒታል ሪፈር ተደረጉ።
.
ለህክምናው ያስፈልግ የነበረው ወጪም እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ በታላቅ ቅንነት ሲያገለግሉ የነበረው ህዝብ በመረባረብ ለአምስት ተከታታይ ወራት እንዲታከሙ ሆኗል።


በታይላንድ ቆይታቸውም ለተሻለ ውጤት epidural stimulation ለተባለ ህክምና ወደ ሌላ ሆስፒታል ሪፈር ተደርገው ነበር። ሆኖም ግን የታሰበው ህክምና እጅግ በጣም ውድ ከመሆኑ የተነሳ ዳግም አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገው ለመመለስ ወደ ኢትዮጵያ ከዓመት በፊት ተመልሰዋል።
.
አሁን ባለው ሁኔታ ዳግመኛ ወደ ታይላንድ ለመሄድ ስለታቀደ ከህክምና ሰጪ ሆስፒታል ማለትም ቶንቡሪ ሆስፒታል ጋር በተደረገው ግንኙነት የህክምና ወጪው የአየር ቲኬት ፣ የኮቪድ-19 ማቆያ ፣ የምግብ ፣ መኝታና ሌሎች ተያያዥ ነገሮችን ሳይጨምር 97,250 የአሜሪካ ዶላር (ወደ 4 ሚሊየን ብር) መሆኑ ታውቋል።
.
ስለዚህም ማንኛውም መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ፣ ግለሰብ እንዲሁም መላው ማህበረሰብ ለብዙዎች ለጋሽ ለነበሩ እጆች የእርዳታ እጃችሁን እንዲትዘረጉ በዶ/ር ባህሩ ለገሠ በቀለ ሥም በአክብሮት እንጠይቃለን::
.
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር - 1000259762077
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር - 0939498464
ለትብብርዎ እናመሰግናለን


Dr.Bahiru Legesse is a medical doctor (surgeon in his specialty) at Tercha general hospital, Ethiopia. He survived a terrible car accident,that left him with tetraplegia (paralysis below the neck). He has been seeking treatment at Alert Hospital, Addis Ababa. Unfortunately, that did not bring him much help. So team of experts at Alert hospital recommended him to have an advanced form of treatment that they hoped would bring back this devoted physician back to form. Different community groups, zonal health offices, individuals and the public brought hands of help together to send him to Thailand (Bumrungrad international hospital). He is right now making a very good progress. However, he is still short of finance to finish his  final phases of his treatment. As per the hospitals estimation, around 97,000 USD is sought to conclude his treatment. Therefore, we once again call for generous hands from all around the world, so that our dear brother Dr.Bahiru can be able to proceed with his final stages of his treatment in Thailand.
Donate

Donations 

  • Meseret Adera
    • $25 
    • 3 yrs
  • Addis Gemeda
    • $25 
    • 3 yrs
  • Tiruwork Alemu
    • $50 
    • 3 yrs
  • Bezuayehu Simein
    • $30 
    • 3 yrs
  • Abenet Zewdie
    • $100 
    • 3 yrs
Donate

Organizer

Meseret Enyew
Organizer
Frisco, TX

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.