Hauptbild der Spendenaktion

Support አብርሆት Enlightenment Library

Spende geschützt
ዘመናዊ ትምህርት የመማር እድል ያገኘ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ሁለት ዓይነት የሞራል ግዴታ አለበት። አንደኛ በሞራል አንፆ ያሳደገው፣ በአብዛኛው ለራሱ ሳይማር፣ ካለችው አነስተኛ ጥሪት ቀንሶ ያስተማረው ህዝብ ውለታ አለበት። ሁለተኛው ደግሞ ነገ ላይ ልጆቹ ከእሱ የተሻለ እድል እና ህይወት እንዲኖራቸው ተስፋን ማበደር አለበት። ስለዚህ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የትላንቱን ውለታ የመክፈል እና ለነገው ትውልድ ተስፋን የማበደር የሞራል ግዴታ አለበት።

በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ መጻሕፍቱን በማሰባሰብ፣ በቴክኖሎጂ የተሟላ እንዲሆን በማድረግና ዘመናዊ አሠራር በመዘርጋት አስተዋጽዖ ማድረግ አለበት ብለን እናምናለን። እንደዚህ ከሆነ ዕውቀት እንደ ኢትዮጵያ ጅረቶች በየአካባቢው ይፈስሳል፤ ትውልድንም ያጠጣል። የነገዋ ኢትዮጵያ ከዛሬ በእጅጉ የተሻለች ትሆናለች፤ መሠረቷን እውቀት ያደረገች ሥልጡን ሀገር ትሆናለች።

 ይህ የድጋፍ ማሰባሰቢያ የተጀመረው በየኔታ ቲዩብ አዘጋጆች ሃሳብ አመንጪነት ሲሆን ዓላማውም በመላው ዓለም ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ለጋሾች አካላት ገንዘብ በማሰባሰብ ብዙ ሺህ መፅሃፍትን ከገበያ መግዛትና ለአብርሆት ቤተመጻሕፍት በስጦታ መልክ ማበርከት ነው።

ድጋፉ በሀገር ውስጥ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር 1000479157646 በኩል የሚሰበሰብ ሲሆን በውጪ ለሚገኙ ደጋፊዎች ደግሞ በዚህ የGofundme አካውንት አማካኝነት ይሰበሰባል።

በዚህ የድጋፍ ማሰባሰቢያ የተገኘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለታለመለት ዓላማ እንደሚውል ቃል እንገባለን። የቤተሰቦቻችንን እና የዕውቀት አባቶቻችንን ውለታ በመክፈል እና ለልጆቻችንና ለቀጣዩ ትውልድ ተስፋን በማበደር የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
Spenden

Spenden 

  • Habtamu dibaba
    • $30 
    • 2 yrs
  • Reta Yirga
    • $200 
    • 2 yrs
  • Seifu Yirga
    • $100 
    • 2 yrs
  • Anonym
    • $100 
    • 2 yrs
  • Kebede E Erbelo
    • $100 
    • 2 yrs
Spenden

Organisator

Yared Tolossa
Organisator
Royse City, TX

Deine einfache, effektive und sichere Anlaufstelle für Hilfe

  • Einfach

    Spende schnell und einfach.

  • Effektiv

    Unterstütze Menschen und Zwecke, die dir am Herzen liegen.

  • Sicher

    Deine Spende ist durch die  Spendengarantie von GoFundMe geschützt.