Main fundraiser photo

በጎንደር ለደረሰው ከ 90,000 ሕዝብ በላይ የመፈናቀል ችግር እንድረስ

Tax deductible
ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት  
Global Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE)  
PO Box 1836, Rancho Cordova, CA 95741 Telephone: (877)746 -4384
www.GlobalAlliancefortheRightsofEthiopians.org  
[email redacted]  

February 17, 2019

ልዩ መግለጫ

ግሎባል አሊያንስ ፣ ጎንደር ውስጥ በተፈጠረው ችግር ሳቢያ ፣ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመርዳት  አስቸኳይ ጥሪ አደረገ !!

በአገራችን ለውጥ ከተጀመረ ጀምሮ ለውጡ ባልጣማቸው ቡድኖችና ሃይሎች አማካኝነት በየጊዜው ህዝብ ለህዝብ ግጭቶች እየተፈጠሩ፣ ብዙ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን አጥተዋል። በብዙ ሺ የሚቆጠሩት ደግሞ ተፈናቅለዋል።  በቅርቡ በጎንደር ውስጥ በተፈጠረው የዚሁ ዓይነት አሰቃቂ ግጭት እጅግ ብዙ ቤቶችና ከብቶች በቃጠሎ ወድመዋል። በእሳት ተቃጥለው የሞቱ ዜጎችም ይገኙበታል።  በዚህ አሳዛኝ ግጭት ምክንያት ክ 90,000 በላይ ዜጎቻችን ተፈናቅለው አሁን በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ።

 

ከሁለት ሺ በላይ የሚሆኑ ዎገኖቻችንም በዚሁ ግጭት ምክንያት ሱዳን መግባታችው ታውቋል።  እነዚህን ለመርዳት ግሎባል አሊያንስ የሚችለውን ለመርዳት እየተዘጋጀ ነው። ግዜያዊ እርዳታ እንደሚያስፈልግም በማምመን ግሎባል አሊያንስ ቦርድ ባስቸኳይ 600,000 ብር ካለው የአስቸኳይ (Emergency Fund) ከተቀመጠው ገንዘብ በማንሳት እንዲላክላቸው ወስኗል።  ቢሆንም የኢትዮጵያ ህዝብ ተረባርቦ የእርዳታ እጁን ካልዘረጋ የግሎባል አሊያንስ እርዳታ አባይን በጭልፋ ነው የሚሆነው።

የፌደራላዊዉም ሆነ የክልሉ መንግስት የዜጎችን በሰላም የመኖር መሰረታዊ መብት የማስከበር ሃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡና ጥቃት አድራጊዎቹን በፍጥነት ለህግ በማቅረብ፣ እንደዚህ አይነቱ ህገ ወጥ ተግባር እንዳይደገም ትምህርት ሰጪ ጠንካራ እርምጃ እንዲወስዱ እናሳስባለን።  በተጨማሪም በባህላችን መሰረት ችግሩን በእርቅና በሰላም ለመፍታት በአገር ሽማግሌዎች የተጀመረው ጥረት ተሳክቶ ወንድማማች ማህበረስቦች እንደቀድሞው በፍቅር በስላምና በመከባበር በአንድነት እንዲኖሩ የሚመለከታቸው ሁሉ እንዲተባበሩ ወገናዊ ጥሪ እናቀርባለን።  ተፈናቃዮችን ወደ ቦታቸው መልሶ በማቋቋም አጣዳፊ ጉዳይ ላይ የፀጥታ ሃይሉ ተሳትፎ የህዝቡን ሥነ ልቡና በማረጋጋት ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለን እናምናለን። በመጨረሻም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምንገኘው ኢትዮጵያውያን በጎንደር ውስጥ ለተፈናቀሉት ዜጎቻችን በቶሎ እንድንደርስላቸውና ወደ ቀዮአቸውም በቶሎ ተመልሰው የመልሶ ማቋቋሙ ሥራ በአስቸኳይ እንዲጀመር የተቻለንን ያህል የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ እርዳታ እንድናደርግ ግሎባል አሊያንስ ጥሪ ያቀርባል!

Fundraising team: Global Alliance - Emergency Support Team (2)

Global Alliance
Organizer
Los Angeles, CA
GARE Global Alliance for the Rights of Ethiopians
 
Registered nonprofit
Donations are typically 100% tax deductible in the US.
Betru Gebregziabher
Team member

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.