Main fundraiser photo

Support Zemenfes's fun. & family

Donation protected


English News:     http://www.wave3.com/story/31698955/update-immigrant-shot-killed-in-sleep-wanted-to-live-american-dream-boss-says

http://www.wave3.com/story/31742208/reward-offered-for-information-in-death-of-african-immigrant

                                             አሳዛኝ ክስተት

ዘመንፈስ ወልደማርያም ተኽለ ይባላል፣በ33  የዕድሜ ክልል የሚገኝ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነው። የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ወደ ሉዊስቪል ኬንታኪ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከመጣ አንድ አመት ከስድስት ወር ሆኖታል። ወደ አሜሪካ ሊመጣ ሲል ትዳር መስርቶ ነበርና አሁን የስምንት ወር ህፃን ልጅ አባትም ነው። ባለቤቱና ልጁ ወደ አሜሪካ እንዲመጡለት የኢሚግሬሽን ፕሮስስ ጀምረዋል።ከመጣ ጀምሮ ሰርቶ ያገኛትን፣ ሌላ የገቢ ምንጭ የሌላቸው ወላጆቹንና እሱን ተማምነው በቤት ክራይ የሚኖሩ ባለቤቱንና የ8 ወር ህፃን ልጁን እየላከ ሲጦር ቆይተዋል። ወላጆቹ ከ70 ዓመት በላይ የሚሆናቸው ሽማግሌዎች ናቸው።

ዘመንፈስ በሳምንት አንድ ቀን ነው እረፍቱ፣ ይቺ አንድ ቀን ጓደኞቹን በመጠየቅ ያሳልፋል። እንደወትሮው ሁሉ April 12 የታመመ ሰው ጥየቃ ሆስፒታል ውሎ ማታ ደክሞት መኝታ ቤቱ ገብቶ ተኝተዋል። ታድያ አገር ሰላም ብሎ በተኛበት አልጋው ክፉ ነገር ገጠመው። ከዘመንፈስ ጋር አብሮ የሚኖር ሌላ ኢትዮጵያዊ ከስራ 1:00 AM ሲል እቤት የመኪና ማቆምያ ቦታው ላይ ይደርሳል፣ መኪናው ለማቆም 10 ደቂቃ የሚሆን መኪና ማቆምያው ላይ ከቆየ በኋላ ወደ ቤቱ ለመግባት ወደ በሩ ሲደርስ ኣንድ መኪና በፍጥነት ወደርሱ ተጠጋና መኪናው ላይ ከነበሩት ሰዎች(ቁጥራቸው በውል ለማወቅ አልተቻለም)አንዱ ከመኪናው በመውረድ ያለማቋረጥ ወደ ቤቱ ወደ ነበረው ልጅ ላይ መተኮስ ጀመረ፣ ከተተኮሱት ወደ 10 የሚጠጉ ጥይቶች አንዷ በሚያሳዝን ሁኔታ ግድግዳውን በመብሳት ተኝቶ የነበረው ዘመንፈስን ስትመታ የተተኮሰበት ልጅ ግን በሂወት ሊተርፍ ችለዋል። በዚች ቅፅበት ባላሰበውና ያለጥፋቱ የዘመንፈስ ሂወት አለፈች። የገዳዮቹ ማንነትም እስካሁን ድረስ ሊታወቅ አለፈዋል።

ዘመንፈስ የድሃ ወላጆቹን ኑሮ የመቀየር ህልሙ፣ ልጁ በአካለ ስጋ የማየት ጉጉቱ፣ የመማርና የተሻለ ኑሮ የመኖር ምኞቱ ሁሉ ሳይሳካ ቀረ። ልጁም ያለ አባት ወላጆቹም ያለ ጧሪ ቀሩ፣ ባለቤቱም ከዘመንፈስ ጋር የሞቀ ትዳር ላይ የመኖርና ሌሎች ተጨማሪ ልጆች ወልዳ የመሳም ጉጉቷም አልሰመረም። በከተማው ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን እጅግ ያሳዘነ ክስተት ሆነዋል። በመሆኑም ዘመንፈስ ከመጣ ብዙ ግዜ ያልቆየና ሬሳው ወደ አገር ቤት ለመላክ የሚያስችል  አቅም ስለሌለ ሁሉም የቻለውን ያክል እንዲያግዘን በትሕትና እንጠይቃለን።

ፈጣሪ ለዘመድ ወዳጆችህ መፅናናትን ይስጥ ያንተም ነፍስ በሰላም ያሳርፍ።

ጓደኞቹ

Organizer

Mebrahtu Kindeya
Organizer
Louisville, KY

Begin your fundraising journey

Create a fundraiser for any person, cause, or nonprofit - it's free and every cause matters.

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.