Main fundraiser photo

A call to support Reyot Media expand

Donation protected
ርዕዮትን በሳተላይት፡፡

ስለኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እንነግር ዘንድ ደግፉን፡፡ ኢትዮጵያችን ታላቅ ሀገር ሆና ሳለ፣ ተነግሮ የማያበቃ የስልጣኔ፣ የአንድነትና ግሩም ውህደት  ታሪክ እያላት፣ ልጆቿ  እውነቷንና ውበቷን እንዳያውቁ በሚያፍኑ ዘረኞችና አምባገነኖች ምክንያት አገራችን ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቃለች፡፡

እውነቷንና ውበቷን እንዲናገሩ ይጠበቅባቸው የነበሩት የዜግነት ፖለቲካ እናቀነቅናለን ባይ ስብስቦችም በአመዛኙ ይህንን ግዴታቸውን አልተወጡም ብቻ ሳይሆን ጨርሶ ዘንግተውት ይታያል፡፡ ኢትዮጵያዊነት የሚያውጀው፣ የሚያስተጋባው፣ የሚገልጠውና የሚሰብከው ቁርጠኛ መገናኛ ብዙሀን ከምን ጊዜውም በላይ አሁን በእጅጉና በአስቸኳይ ያስፈልጋል፡፡

ይህም ኢትዮጵያን በእራሷ ቀደም እውነት ከዘውግ ህመሟ የመፈወስ ተግባር የርዕዮት ሚድያ የመፈጠር ምክንያት ነው፡፡ ስለሆነም፣ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ሊያሰፍን እየተንደረደረ ያለውን አፈና ተሻግሮ ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያዊ አጀንዳዎችን አለመወላወልና በቁርጠኝነት በአገር ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለማድረስ የሳተላይት ስርጭት መጀመር አማራጭ የለሽ ምርጫ ሆኗል፡፡

ይህንን እውነት ዘርቶ አገር የማዳን አላማ በሳተላይት ለማሰራጨት እንድንችል የሁላችሁም ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ያስፈልገናልና የሚቻላችሁን ሁሉ  አስተዋጽኦ እንድታደርጉ በኢትዮጵያ ፍቅር ትጠየቃላችሁ፡፡

ፍቅር ተግባር ይጠይቃል፡፡
ኢትዮጵያ ምንጊዜም በክብር ትኑር፡፡

ርዕዮት ሚድያ የኢትዮጵያዊነት ቁርጠኛ ድምጽ የሆነ፣ የኢትዮጵያችንን ልእልናና የአገራዊ ማንነታችንን ህልውና የሚሰብክ ቤታችሁ ነው፡፡  ርዕዮት ሚድያ ዘውጌ ፖለቲከኞች ያቆሙትን አንድ የሆነውን ህዝብ የሚነጣጥል ሀሰተኛ የትርክት አጥር በኢትዮጵያዊ እውነትና እውቀት  የሚያፈርስ የእናንተው መድረክ ነው፡፡

ታድያ ይህንን ኢትዮጵያን የመስበክ ቅዱስ ተልእኮ በበለጠ ጉልበት ለመቀጠልና በምስል ጭምር በመላ አለም ወዳላችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወደመድረስ ቀጣይ ምእራፍ ለመሸጋገር ደረጃውን የጠበቀ የምስል እስቱድዮ መገንባት አስፈልጎናል፡፡ ይህንን ለትውልዱ ኢትዮጵያዊነትን ሰብኮ አገርን የማዳን አላማ ከግብ እናደርስ ዘንድ የእናንተን የሁላችሁንም ያላሰለሰና ያልተቆጠበ ድጋፍ እንሻለንና እንድትረዱን በሀገር ፍቅር ትጠየቃላችሁ፡፡

ፍቅር ተግባር ይጠይቃል፡፡ አያቶች ነጻነቷን በደም መዋጀታቸው፣ አለም ደስታቸውን ጥለው የየግል ተምኔታቸውን ወድያ ብለው ስለህልውናዋና ስለልእልናዋ ማለፋቸው ስለዚህ ነው፡፡ አይተኬውን የሸለሟት፣ አይቻለውን የተሸከሙላት ስለዚህ ነው፡፡ ፍቅር ተግባር ይጠይቃል፡፡ የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ዛሬ ከእኛም የሚጠበቅ አለ፡፡

ኢትዮጵያዊነት ብቸኛው የመዳናችን መንገድ ነውና ይህንን ታላቅ ማንነት ለዚህ ትውልድ በመስበክ አገራችንን እናድን፡፡ ደግፉንና አገራችንን ከአጽናፍ አጽናፍ እንስበክ፡፡

 ኢትዮጵያ ምን ጊዜም በክብር ትኑር፡፡

Organizer

Reyot Ethiopia
Organizer
Reston, VA

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.