Main fundraiser photo

LeAmaraTegadlo Humanitarian Support



የዐማራውን ኅልውና አስጠብቆ፣ የዘረኛውን የወያኔን አገዛዝ በማስወደግ፣ አንድነቷ የጠነከረ፣ ሰላሟ የተሟላ፣ ዕድገቷ የተፋጠነ ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ፣ የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ እንቅስቃሴ በሁለንተናዊ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት እንደሆነ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያምናል። ለዚህም ለታሠሩ፣ ለተፈናቀሉ፣ ለተገደሉና በወያኔ እየተሳደዱ ላሉ የዐማራው ልጆች የሚያስፈልጋቸውን እገዛና ድጋፍ በውጭ የሚኖረው ዐማራና የዐማራው ወዳጅ የሆነ ሁሉ፣ በቀና መንፈስ ወገንን ከጥፋት የመታደግ ጥረት የበኩሉን እርብርብ ሊያደርግ ይገባል። ዛሬ በወያኔ ለተጎዱ ወገኖ የምንሰጠው ድጋፍ ሕዝባዊ እንቢተኝነቱን በቆራጥነት ለተያያዙት ወገኖች የሞራል ስንቅ በመሆን የሚያገልግል ከመሆኑም በላይ፣ ትግሉን ለድል እንዲበቃ ጋንን በጠጠር የመደገፍ ያህል ነውና፣ የዐማራው ልጅ፣ የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በአክብሮት ጥሪ ያቀርባል። ዐማራው ለወገኖቹ የሚሰነዝረው የድጋፍ እጁ ከሚፈለገው ቦታ እንዲደርስ ለማድረግ ሞረሽ ወገኔ የበኩሉን ዝግጅት ያደረገ በመሆኑ፣ ተጎጂ ወገኖቻችን ለመርዳት ፍላጎቱ ያላችሁ ወገኖች በየምትኖሩበት አካባቢ ላሉ የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት መሠረታዊ ማኅበራት፣ ወይም በእንሂድ እንደግፍ (GO FUND ME)  ወይም በቼክ፣ በፔይ ፓል  መርዳት የሚቻልበትን መንገዶች አመቻችቷል።

ዛሬ ለወገናችን ማድረግ የምንችለውን ነገር ሳናደርግ ቀርተን፣ እንቅስቃሴው ቢገታ ፀፀቱ የእኛ ብቻ ሳይሆን፣ በልጆቻችን ተወቃሽ የሚያደርገን ስለሚሆን፣ የምንችለውን ያህል እጃችን ለወገናችን እንድንዘረጋ ግፍ በሚፈጸምባቸው ወገኖቻችን ስም ጥሪአችን እናቀርባለን!

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
Donate

Donations 

  • Anonymous
    • $100 
    • 6 yrs
Donate

Organizer and beneficiary

Moresh Wogene
Organizer
Silver Spring, MD
Amara Dimts Radio
Beneficiary

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.