Main fundraiser photo

Funeral for Solomon Atsbha

Donation protected
ሁሌም የምንወደው እና የምናከብረው ከልባችን የማይጠፋው ሰለሞን አፅብሃ ባልታሰበ እና ባልተጠበቀ ሁኔታ November 30, 2019 ከዚህች አለም ተለይቶናል። ከሁሉም የበለጠ ሰላም እና ደስተኛ በነበረበት ሰአት ማንም እንዲ ይሆናል ብሎ ባልጠበቀበት ሰአት ጓደኞቹን አልጋው ላይ ጋደም ብሎ በስልክ እያወራ በዛው በተኛበት እሱ እራሱ ሳያውቀው ወደ ማይመለስበት አለም ተቀላቅሏል። ይህ አጋጣሚ ለመላው ቤተሰቦቹ እና ለጓደኞቹ ልብን የሚሰብር በጣም የሚያስደነግጥ እና ለማመን የሚያስቸግር አጋጣሚ ሆኗል።

ሰለሞን አፅብሃ በሀገረ አሜሪካ መኖር ከጀመረ 24 አመታትን አስቆጥሯል, መጀመሪያ በኒው ዮርክ  ከተማ አራት አመት አካባቢ ከቆየ በኋላ ያለፉትን 20 አመት በቦስተን ነበር ነዋሪነቱን ያደረገው። ሰለሞን ማለት ከህፃን እስከ አዋቂ የሚወደው፣ ከሰው ጋር ተግባቢ፣ ሃቅኛ፣ ለአውነት ሟች፣ የቤተሰቡ መከታ፣ ለሃገር ተቆርቋሪ፣ ሰው አክባሪ እና ፈርሃ እግዚአብሔር በውስጡ የተሞላ ሰው ነበር። በህይወቱ ላይ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነገር ፈርሃ እግዚአብሔር፣ የሀገር ጉዳይ እና የቤተሰብ ነገርን ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ ሰው ላይ ሳይደርስ የራሱን ህይወት ቀጥ ለጥ አድርጎ መኖር ብቻ ነው የሚያስደስተው። በዚህ ጊዜ ውስጥ እህቱን እና ሁለት ልጆቹን ወደ አሜሪካ  በማምጣት እራሳቸውን ችለው ለቤተሰብም እንዲተርፉ አድርጓቸዋል, ይህ እንዲ እንዳለ እስካሁኗ ሰአት በቻለው አቅም ለቤተሰቡ እና ለጓደኞቹ ሁሌም ደራሽ ነው።

ሰለሞን አፅብሃ  በማህበራዊ ሚድያ በተለይ Paltalk  ፍትህ እና እኩልነት በአገራችን እንዲከበር ሀሳቡን በድፍረት እና በግልፅነት የሚሰጥ ወንድማችን ነበር።  ሰለሞን በፓል ቶፕክ ስሙ ሪችት ( Richit) በሚል ስም ይታወቅ ነበር፡፡

የሰለሞን አፅብሃ ልጆች ቢኒያም ሰለሞን እና ናትናኤል ሰለሞን አባታችንን እያሰባችሁ  ስለምታደርጉት የልብ ስጦታ  ከልብ ልናመሰግን እንፈልጋለን፡፡ አንድ በመሆን አባታችንን እያሰባችሁ ያላችሁን ፍቅር እና አክብሮት  በመግለፅ ለእያንዳንዷ ለምታደርጉት ነገር እግዚአብሔር ያክብርልን።

ፈጣሪ እግዚአብሔር ሁላችሁንም ባላችሁበት ይጠብቃችሁ!!!
ልጆቹ : ቢኒያም ሰለሞን እና ናትናኤል ሰለሞን

Organizer

Nathanael Solomon
Organizer
Jamaica Plain, MA

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.