Main fundraiser photo

እማት ጉራጌ ሚዲያን ይደግፉ!

Donation protected
ሠላም ሠላም

Emat Gurage Media ባለፈው አንድ አመት በተለያየ መልኩ የጉራጌን ህዝብ ሊያግዙ የሚችሉ የሚዲያ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል። በዚህ ጎፈንድ ሚ አካውንት በኩል የተሠበሠበው 2415 ዶላር ና ከዚህ ውጭ በደገፉን ግለሰቦች እገዛ ቢሮ ከፍተን እንቅስቃሴ እያደረግን እንደነበረ ይታወቃል። አሁን ላይም አንደኛ አመቱን ለማክበር ና የሚዲያ ፍቃድ ለማሟላት በመታገል ላይ ባለበት ሰአት ከደጋፊዎቹ ባሠባሠበው ሳንቲም የተገዙ ንብረቶቹና በተከታታይ ሊቀርቡ የነበሩ ዶክመንታሪዎቹ ከቢሮው ተዘርፈዋል።

በጠላት የተደረገውን ይሄን ጥቃት ተቋቁሞ በተሻለ ስራ ለመምጣት ከዜሮ መጀመር ግድ ሆኗል ለዚህ ደግሞ የሁላችንም ትብብር ይጠይቃል።

በተጠና ዘዴ ከተዘረፈው የ Emat Gurage Media ንብረት በላይ ከባዱ ላለፉት በተከተታይ ቀናት ለእናንተ ልናቀርባቸው የነበሩት ዶክመንታሪ ፊልሞች ከነ ባክ አፓቸው መሠረቃቸው ነው።

ዶክመንታሪዎቹም እነዚህ ናቸው

❶ #በውሀ_ታጥራ_ውሀ_የተጠማችው_ከተማ
በወልቂጤ ከተማ የውሀ ችግር ላይ ያተኮረ ዶክመንታሪ

❷ #እንሴኖ_ዶክመንታሪ
በመስቃንና ማረቆ ግጭት ዙርያ ያጠነጠነ ዶክመንታሪ

❸ #የጉራጌ_መንገድ_ስራ_ድርጅት_ከየት_ወደየት?
ብዙ ታሪኮችን የያዘ አመት የፈጁ ኢንተርቪዎችን የያዘ ዶክመንታሪ

❹ #የጉራጊኛ_ቋንቋ_ለትምህርት
በቋንቋ ዙርያ ምሁራን ፣ የቋንቋ ባለሙያዎች አመራሮች ሀሣባቸውን ከተለያየ ቦታ የሠበሠብንበት

❺ #ኧክልለንዳ_ዘንጋ
በጉራጊኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ዶክመንታሪ

❻ #ኧጉራጌ_ሁጅር_ምሩ?
በጉራጌ ብሄር ትክክለኛ ልብስ ላይ የተዘጋጀ ፕሮግራም።

❼ #ኧሰት
በጉራጊኛ ቋንቋ በእንሰት ዙርያ ከሀገር ሽማግሌ ጋር የተደረገ ቃለመጠይቅ

❽ #የአብሬት_ሼህ_መዉሊድ_ዶክመንታሪ
❾...

ሌሎችያላለቁ ስራዎች ና ለታሪክ የተቀመጡ ፋይሎች ደግሞ ብዙ ናቸው። ይሄንን ሁሉ የያዙ ላፕቶፖችና ሀርድ ዲስኮች በተለይሜ በአቶ ኤርምያስ ማንዋረ የተበረከተልን 5 ቴራ ባይት አቅም ያለው ትልቅ ሀርድ ዲስክ ተዘርፏል።

ግን አምናለሁ ሁሉንም እንመለስዋለን። የተከፈለውን ዋጋ ከፍለንም ቢሆን!


በመላው አለም የምትገኙ ወገኖቻችን ለዚህ አላማ ከጎናችን እንድትቆሙ በትህትና እንጠይቃለን።

ተስፋ ነዳ
ደራሲና ዳይሬክተር
ስልክ 0924410897
Facebook : Tesfa G Neda
Email :   [email redacted]
#እማት_ጉራጌ
Donate

Donations 

  • Anonymous
    • $50 
    • 3 yrs
  • Medina M
    • $100 
    • 3 yrs
  • Jemal T.
    • $5 
    • 3 yrs
  • Anonymous
    • $25 
    • 3 yrs
  • Anonymous
    • $10 
    • 3 yrs
Donate

Organizer

Mikias Getachew
Organizer
Alexandria, VA

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.