Main fundraiser photo

እኔ አቤል ወንድማችሁ ነኝ። አሁን ግን እርዳታ ያስፈልኛ

Donation protected










ወጣቱ አቤል ካሳሁን ብዙዎችን በመርዳት የኖረ

ዛሬ ግን የብዙዎችን እርዳታ ይፈልጋል !!

ወጣት አቤል ካሳሁን በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀው በበርካታ የምግባረ ሰናይ ተግባር ላይ ከፊት መስመር ተሰልፎ በሚችለው አቅም ሁሉ የድርሻውን የሚወጣ ሰብዓዊ ክብር የገባውና ኑሮውን ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም መኖር ያደረገ ወጣት ነው በተለይ አዲስ ዓመት ሲመጣ በደብተር ፣ በጽህፈት መሳሪያና በአልባሳት ተቸግረው እቤት የዋሉ የችግረኛ ቤተሰብ ልጆች የነገ ሀገር ተረካቢዎች በዚህ ምክንያት እቤት እንዳይውሉ በማድረግ ደብተር ፣ እስክርቢቶ አልባሰሰትና ሌሎች ቁሶችን በማሰባሰብ በርካታ ህፃናትን በመታደግ የድርሻውን ሲወጣ ቆይቷል

ነገር ግን አሁን ላይ አቤል በዚህ በጎ ምግባር የበለጠ ሰርቶ በርካታ ህፃናትን መታደግ እንዳይችል ከዚህ ተግባር የሚያሰናክለው የጤና እክል አጋጥሞታል ወጣት አቤል ካሳሁን በገጠመው ከፍተኛ የሆነ የልብ ህመም ለብዙ ጊዜ በስቃይ የቆየ ሲሆን አሁን ግን ህመሙ ከሚገባው በላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመባባሱ ህይወቱ አደጋ ላይ ይገኛል ወጣት አቤል ካሳሁንን ህይወት ለመታደግ በሀገር ውስጥም ይሁን በውጪ ሀገር ለመታከም ከ $20 000 ዶላር በላይ የሚያስፈልግ ሲሆን የወጣት አቤል ካደሰሁንን ህይወት ለመታደግ የተቻሎትን እገዛና ድጋፍ እንዲያደርጉ እየተማጸንን ለዚሁ ገቢ ማሰባሰቢያ በተዘጋጀው የጎፈንድ አካውንትና የባንክ አካውንት ቁጥር መርዳት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን

ለበለጠ መረጃ [email redacted]
Donate

Donations 

  • GORFU SITOTAW
    • $30 
    • 5 yrs
Donate

Organizer and beneficiary

Eyrus WoldeAmanuel
Organizer
Alpharetta, GA
Yared Kidanemariam
Beneficiary

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.