ሉንድ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የሕንጻ ማሰሪያ ድጋፍ ማሰባሰቢያ

S:ta Maria Ethiopian orthodox church in Lund Sweden church building project. 
”የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን” ነህ. ፪፤፳

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፤ ስካንዲኒቪያን ሀገረ ስብከት ሥር  በስዊድን ሀገር ሉንድ ከተማ የምትገኘው ደብረ ምጥማቅ ሉንድ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በቅርቡ ከሉንድ ከተማ አስተዳደር በተረከበችው የቤተክርስቲያን መስሪያ ቦታ ላይ ሊሰራ የታሰበው የሕንጻ ፕሮጀክት ዲዛይን  ተጠናቆ ግንባታ ለመጀመር በእንቅስቃሴ ላይ እንገኛለን።

በመላው ዓለም የምትገኙ የቤተክርስቲያን ልጆች ይሄንን ታላቅ፣ ታሪካዊ የቤተክርስቲያን እና የሀገር ቅርስ  የሆነውን የእመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ ሥራ  እንድንፈጽም እርዳታችሁን እንፈልጋለን።

የገንዘብ ርዳታ ለማድረግ የምትፈልጉ ምዕመናን ከዚህ በታች የተገለጸውን የቤተክርስቲያኗን ዓለም አቀፍ የባንክ ሂሳብ ቁጥር  IBAN SE36 9500 0099 6042 1274 5642 ወይም በተከፈተው gofundme account  በመጠቀም ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ።

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ - +46-(0) 736-944-035 ላይ ይደውሉ።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!

ደብረ ምጥማቅ ሉንድ ቅድስት ማርያም ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳደር
 • Anonymous 
  • kr1,000 
  • 41 mos
 • Anonymous 
  • kr300 
  • 41 mos
 • Anonymous 
  • kr500 
  • 41 mos
 • Anonymous 
  • kr300 
  • 41 mos
 • Anonymous 
  • kr500 
  • 41 mos
See all

Organizer

ሉንድ ደብረ ምጥማቅ ማርያም 
Organizer
Lund, Sweden