Main fundraiser photo

Please save kid Masiresha

Donation protected
ታላቁን ምህረትና ርህራሄ ከፈጣሪ እየተማፀንን ጥቂቱን ነገር ግን ከወገናችን እንጠይቃለን። ህፃኑ ገና ልጅ ነው። ምንም የማያውቅ ለጋ የአራት ዓመት ህፃን ማስረሻ ፀጋዬ ይባላል። በጭንቅላት እጢ ህመም የሰቆቃ ህይወት እየመራ ነው። ወላጆቹ ህፃኑን ለማሳከም ሥልሳ ሺህ (60,000) የኢትዮጲያ ብር ለህክምና መጠየቃቸውን ከመጀመሪያው ሆስፒታል መጠየቃቸውን አሳውቀውን ነበር። አሁን ግን ወደ 100 ሺህ መጠየቃቸውን ነው የሚናገሩት። ቤተሰቦቹ ህፃኑን ማሳከሚያ ገንዘብ የላቸውም። ስለዚህም የማሳከሙ እጣ ፈንታ ለኢትዮጲያ ህዝቦች ሆኗልና እባክዎን እንላለን። ፈጣሪም "ስጡ ይሰጣችኃል" ይላልና እንደቃሉ መኖርም መልካም ነው ከክፉ ጭንቀትም መከራም ይታደጋልና እንርዳው እንላለን።

ህፃኑን በግል በፌስ ቡክ እንድትረዱት ጠይቀን 16 ሺህ ብር ለጋስ ኢትዮጲያውያን ለግሰውናል። እግዚአብሔር ይስጥልን።

የህፃን ማስረሻ ወላጆች ከጥቁር አንበሳ ፤ ዘውዲቱ ፤ቅዱስ ጴጥሮስ፤ ሆስፒታሎች ሪፈር ተጽፎላቸው የመጨረሻ የህክምና ውጤቱም በአስቸኳይ ህክምናውን ማግኘት እንዳለበት ያልያ ግን የጭንቅላት እጢው አድጎና በውስጡ ውሃ እየቋጠረ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ህክምናውን ካላገኘ ከእጃቸው ሊያመልጥ ይችላል ተብሏልና እርዳታችሁን እንጠይቃለን። በኢትዮጲያ የሚገኘው ኮርያ ሆስፒታል መታከም እንዳለበት የህክምና ወጭውም ከቀድሞው ሥልሳ ሺ (60,000 ) ወደ መቶ ሺ (100,000) ብር ከፍ እንዳለ ዶክተሮቹ ተናግረዋል።

የህፃኑን ነገ ብሩህ ማድረግ ለህሊናም ጥልቅ ሰላም ይሰጣል። ለቤተሰቡም ትልቅ እረፈት ሲሆን በፈጣሪም እጅግ የተወደደ ስራ ነውና እባክዎን እንላለን። ወላጅ አባት ፀጋዬ አባተ። ሙሉ ኃላፊነቱ ለመውሰድ እኔው ሊባኖስ ዮሐንስ በስሜ የከፈትሁት ገንዘቡን ለመጠየቅ የሶስተኛ ወገን ማረጋገጫ ስለሚጠይቅ በቀላሉ በቶሎ ገንዘቡን ለማግኘት መሆኑ ይታወቅልኝ። የተለመደ ትብብራችሁን እባካችሁ እንላለን።

Organizer

Libanos Yohannes Bilatena
Organizer
Beaverton, OR

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.