የሐዋርያት መሰናዶ ት/ቤት የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ

በተለያዩ ያለማችን ክፍሎች የሚገኙ የጉራጌ ዞን የሙህርና አክሊል ወረዳ ተወላጆችና ወዳጆቻቸው ማህበረሰባቸውን ለማገዝ ባቀዱት መሰረት በተጀመረው በዚህ የድጋፍ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴ እርሶም የበኩልዎን  አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ያክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን። ማህበረሰባችን በግብርና የሚተዳደር በመሆኑ ያካባቢው ተወላጆች ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ልዩ ልዩ ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ቆይተዋል። ከነዚህም ውስጥ አንዱ በት/ቤቶች ውስጥ የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ እጥረት ነው። 

በዚህ ድጋፍም ባሁኑ ሰአት ለሁሉም አማካይ ለሆነውና ብዙ የአካባቢያችን ተወላጆችን እያገለገለ ላለው የሐዋርያት መሰናዶ ት/ቤት እጅግ የሚያስፈልጉ እገዛዎችን ለማድረግ ታስቧል። በእንቅስቃሴው የሚሰባሰበው ድጋፍም የሚከተሉትን ተግባራት ለማከናወን ይውላል:-

** የተለያዩ የትምህርት አይነቶች አጋዥ መጽሐፍትን በመግዛት ለመለገስ
** በመረጃ መረብ ላይ በቀላሉ የሚገኙ አጋዥ ጽሑፎችን አትሞ፣ አባዝቶና ጠርዞ ለማቅረብ
** ከባድ ችግር ያጋጠማቸው ተማሪዎችን በመሰረታዊ የትምህርት ቁሳቁስ ለማገዝ 

ለማድረግ የታሰበው ድጋፍ ዝርዝር  እዚህ ፋይል ላይ ይገኛል፤ ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች ደግሞ በዚህ የፌስቡክ ግሩፓችን ገጽ ላይ ይገኛሉ።

የሚደረገው ድጋፍ ያካባቢው ወጣቶች የሚኖራቸውን አገራቀፍ የትምህርት ተወዳዳሪነት በማሻሻል፣ ባሁኑ ወቅት በሚጠበቀው መጠን ጥሩ ያልሆነውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ፈተና ውጤትን ከፍ ለማድረግ ትልቅ እገዛ ያደርጋል። በተጨማሪም፣ የኛ የወገኖቻቸው "ከጎናችሁ ነን!" የማለትና አለኝታ የመሆን እገዛ ብዙ ተማሪዎችን በሞራል በማነቃቃት ስኬታማ የሚሁኑትን ቁጥር ከፍ ያደርገዋል። ይህ ደግሞ ወደፊት ተማሪዎቹ ከራሳቸው አልፈው የቤተሰቦቻቸውን የሌት ተቀን ኑሮ ማሻሻል እንዲችሉ ያግዛል።

ለዚህ አላማ መሳካት ለሚያደርጉት ቅን ድጋፍ በመላው ማህበረሰባችን ስም ከወዲሁ ልባዊ ምስጋናንችንን እናቀርባለን።

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር፣
የሙህርና አክሊል ተወላጆችና ወዳጆቻቸው።
***********************************************************
We respectfully request your support for this gofundme campaign which is organized by members and friends of the Muhir and Aklil woreda of the Gurage zone of Ethiopia currently living in different parts of the world.

People living in this rural community have been facing a number of challenges for so long, mainly because of their dependence on persistence farming. One of these challenges is shortage of basic materials to support education in schools. This campaign aims to provide a highly needed support to one of the schools which is currently serving many young people from all parts of our community: the Hawariat Preparatory School. Specifically, the voluntary support collected in this campaign will be used for:

** Buying reference books in different subjects to strengthen the school’s library
** Collecting materials freely available on the internet, printing, copying and binding
  them in multiple copies to further strengthen the library
**Supporting some students in need of basic stationary items for school

The detailed plan can be found here, while  other related information is available on the page of our Facebook group. 

Your support will significantly contribute to the improvement of the currently underwhelming college entrance examination results of young students in the rural community. In addition, such show of solidarity by all of us, its members and our friends, will boost the morale of many students in our community. It will stimulate their education and help more of them succeed. This will in turn help them improve not only their own but also their parents' lives in the future.

We are deeply grateful for your gracious support to this camapiagn on behalf of the entire community.

With Best Regards,
Members and Friends of Muhir and Aklil.

 • Meseret Hailu 
  • $50 
  • 62 mos
 • Selam Denbarga 
  • $100 
  • 62 mos
 • adane teka 
  • $100 
  • 62 mos
 • Solomon Woldeyohannes  
  • $100 
  • 62 mos
 • Alemyirga Gizaw  
  • $100 
  • 62 mos
See all

Organizer and beneficiary

Nigist Shawa 
Organizer
SeaTac, WA
Abaynesh HAILU 
Beneficiary

Your easy, powerful, and trusted home for help

 • Easy

  Donate quickly and easily.

 • Powerful

  Send help right to the people and causes you care about.

 • Trusted

  Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.