Foto principal de la recaudación de fondos

መኢአድን ይደግፉ

Deducible
በኢትዮጵያ የአንድነት ተቃዉሞ ጎራ ዉስጥ የሞራል የበላይነቱን የጨበጠዉን መኢአድን በመደገፍ ሀገር የማዳን ሀላፊነትዎትን ይወጡ !
-----------------------

 መኢአድ  በኢትዮጵያ የአንድነት ተቃዉሞ ጎራ ዉስጥ የሞራል የበላይነቱን የጨበጠ እንቅስቃሴ ያለዉ ነዉ:: ለመኢአድ የሞራል የበላይነትም  ሁነኛ ምክንያቶች አሉ:-

ለሰላሳ አመታት ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ፍትህ እና ለዜጎች እኩልነት አንድም ቀን ግንባሩን ሳያጥፍ የታገለዉ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድን)  ከመሃል አዲስ አበባ እስከ መላዉ ኢትዮጵያ ጠረፎች ኢትዮጵያዉያንን በጋራ የማንቀሳቀስ መሰረት ያለዉ ሀይል ነዉ:: ከመአህድ እስከ መኢአድ: ከመኢአድ እስከ ቅንጅት የዘለቀዉን የዲሞክራሲ የእኩልነት: የፍትህ እና የአንድነት ጥያቄ አንግቦ በዘረኞች እና በአምባገነኖች ፊት "የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ህዝብ ነዉና ኢትዮጵያዊ ሁሉ እኩል ፍትህ ዲሞክራሲ ነጻነት ብልጽግና ይገባዋል !" ብሎ ለሰላሳ አመታት ዘረኝነትን:አምባገነንነትን: ጸረ ኢትዮጵያዊነትን የታገል ታላቅ የህዝብ ድርጅት የሆነዉ መኢአድ ፍትህ እና ዲሞክራሲ በተጠሙ ኢትዮጵያዉያን አይን ሁሉ በታላቅ አክብሮት የሚታይ ድርጅት ነዉ::

መኢአድ ከፕሮፌሰር አስራት እስከ ኢ/ር ሀይሉ ሻዉል የደከሙበት ዜጎች በነገዳቸዉ የማይገፉበት ስርዓት: እኩልነት: ፍትህ : ዲሞክራሲ: ነጻነት : ብልጽግና እዉን ሳይሆን ከቶም እንቅልፍ አይወስደንም ሲሉ የተማማሉ እና አሁንም በጽናት የቆሙ ጀግኖች ድርጅት የተሰባሰቡበት ነዉ::

በአሁኑ ሰዓት መኢአድ በጽኑዉ የትግል አርበኛ በማሙሸት አማረ የሚመራ መሰረቱ የማይዋዥቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ መሰረት ያለዉ ድርጅት ነዉ::
የመኢአድ መሪ በትግል ጽንዓቱ እንደ ቀደሙት አባቶቹ ለቆመለት አላማ ታማኝ ነዉ:: ለኢትዮጵያ አንድነትም ቀናኢ መሆኑን ለሰላሳ አመታት ያስመሰከረ ነው:: ግንባሩን ሳያጥፍ የእድሜዉን ግማሽ በእስር ቤት ስለ ህዝቡ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ቢንገላታም ስለ ታላቂቱ ኢትዮጵያ በመታገሉ ደስተኛ ነዉ:: አቶ ማሙሸት አማረ በዚህ ፈታኝ ወቅትም በታላቅ የሞራል ልዕልና ላይ የቆመዉን የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድን) በፕሬዝዳንትነት እየመራ ስለ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ፍትህ : ሰላም : እኩልነት: ነጻነት እና ዲሞክራሲ ከጀግኖች ጓዶቹ ጋር ተሰልፎ ታላቅ ህዝብ የማንቃት እና የማደራጀት ስራዉን ቀጥሏል::


በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ የገባችበት መዉጫ ቀዳዳ ያጣዉ የአክራሪ የነገድ ፖለቲካ ስንኩል ህሳቤ ሀገሪቷን ሊያፈርሳት በሚንጥበት ወቅት የመኢአድ ለኢትዮጵያዉያን ተስፋ የሚሆን ራዕይን ያነገበ እንቅስቃሴ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ለዚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ራዕይም ታምኖ የቆመ ስብስብ መሆኑ የመኢአድን  የሞራል የበላይነት ያስረግጥለታል::

መኢአድ  "የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ህዝብ ነዉ:ኢትዮጵያም አንዲት ሀገር ነች :ዳር ድንበሯም ከቶም መደፈር የሌለበት ነዉ" ሲል በጽናት የቆመ ሀይል ነዉና ኢትዮጵያዉያን የሀገራዊ ተስፋን ከመኢአድ  ዉስጥ ሲፈልቅ በደስታ ያስተዉላሉ:: በዚህ የኢትዮጵያዊነት ምንጭ በድርቅ በተመታበት ዘመን  ከመኢአድ ራዕይ አድማስ ጥግ ግን ኢትዮጵያዊነት እንደ ኩል ዉሃ ኩልል ብሎ እየመነጨ ነዉ::ይሄም መኢአድ በአንድነት የተቃዉሞ ጎራዉ ዉስጥ የሞራል የበላይነቱን ጨብጦ እንዲዘቅ መሰረት ጥሎለታል::

 በመሆኑም በኢትዮጵያ የአንድነት ተቃዉሞ ጎራ  ዉስጥ የሞራል የበላይነቱን የጨበጠዉን መኢአድን  ይደግፉ ዘንድ  ሀገራዊ ጥሪ ቀርቦልዎታል::


Organizador

Shenkut Ayele
Organizador
Bethesda, MD
Moresh Wegenie Amara Organization Inc
 
Organización sin fines de lucro registrada
Las donaciones suelen ser totalmente desgravables en los EE. UU.

Un sitio fácil, eficaz y de confianza donde encontrar ayuda

  • Fácil

    Dona de forma rápida y sencilla.

  • Eficaz

    Envía ayuda a la gente y a las causas que te importan.

  • Confiable

    Tus donaciones están protegidas por la  Garantía de GoFundMe.