Be’ata Lemariam Monastery Restoration Fundraising

      የታላቋና ከመቶ ዓመት በላይ ባለታሪክ የሆነችው የዳግማዊ ምኒልክ መታስቢያ፣ ታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም ህንጻ እድሳት የሚውል የገንዘብ እርዳታ በዩናይትድ ኪንግደምና አየርላንድ ለመሰብስብ በገዳሙ የዩኬና አየርላንድ እርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተቋቁሞና በሃገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ቡራኬና መመሪያ ተቀብሎ የሥራ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ምንም እንኳን ሥራችን በኮቪድ-19 እና ባለፈው ክረምት በሃገራችን በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለደረሰው ፍጅት፣ አስቸኳይ እርዳታ እንዲካሄድ ቅድሚያ በመስጠታችን፡ ቢጓተትም፣ አሁን ከጥቅምት ወር፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በጎፈንድሚ እርዳታውን የማሰባሰብ ሥራ ሂደቱ ጀምሯል።

በመቀጠልም፣ ኮሚቴው፣ የቅድሚያ የሥራ ዝግጅቶችን አድርጎ፣ የመጀመሪያውን የዕርዳታ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር በጎፈንድሚ (GoFundMe) ከጥቅምት ወር፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ገቢው እንዲሰበሰብ፣ ይህ በጎፈንድሚ (GoFundMe) ተክፍቶ በሥራ ላይ ውሏል። ከዚህም ጋር፣ መረጃ ሰጪ የሆነ መንፈሳዊ መርሃ-ግብር በህዳር 6/ እን ህዳር 20 ቀናት 2013 ዓ.ም በኦንላይን የእርዳታ ማሰባሰቢያ መንፈሳዊ የኦንላይን መርሃ-ግብር በዩኬ ባሉት አድባራት ዪቱዪብ (Youtube Prayer Channels) ማለትም፡
1. በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅ/ማርያም፡  (EOTC Daily Prayer)
2. በደብረ ገነት ቅድስት ስላሴ እና (Debre Genet Holy Trinity Church London)
3. በአውደ ወንጌል፣ (AWDE-Wongel) ከለንደን ውጪ ያሉ አድባራት መንፈሳዊ መርሃ-ግብር ቻናሎች ለማስተላለፍ መርሃ-ግብር ተይዟል።

በእለቱ ሁላችሁም በያላችሁበት ሆናችሁ መርሃ-ግብሩን በመከታተልና የምትችሉትን ያህል በጎፈንድሚው በማስገባት የበረከቱ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ የበአክብሮት ጥሪአችንን እናቀርባለን።

የተሰበሰበውም ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ታህሳስ 3፣ 2013 ዓ.ም ወደገዳሙ እንዲላክና እዛም፣ አንዲት ሳንቲም ሳትጎድል መድረሷን የሚያረጋግጥ መረጃ በመቀበል፣ ወደፊት በምናዘጋጀው የምስጋና መርሃ-ግብር ላይ ለማቅረብ ቃል እንገባለን።

ለዚህ የተቀደሰ፣ የወገንና የሃገር ቅርስ ማቆያና ከመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መንፈሳዊ በረከት የሚገኝበት ሥራ ሁላችንም ኢትዮጵያኖች ሁሉ አነሰ ሳንል፣ የምንችለውን ያህል፣ በዚህ ጎፈንድሚ በማሰገባት ተባባሪና፣ ሊንኩንም ላልሰሙ ለሌሎች በመላክ ትብብር እንድናደርግና የምንችለውን እንድረዳ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ስለ መልካም ትብብራችሁ በቅድሚያ በእመቤታችን ስም ምስጋናችንን እናቀርባለን።

እግዚኣብሔር ሥራችንን ይባርክልን፣ የቤ/ክችንንና የሀገራችንን አንድነትና ሰላም ያጽናልን።

በገዳሙ የተሰየመ የዕርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴው።

Tea’ka Negest Bata LeMariam Monastery is more than 100-years-old and was built by Empress Zewditu and is a treasure for numerous manuscripts, icons and other ecclesiastic and secular objects of great historical and spiritual significance for Ethiopia. Furthermore, the Church serves as a mausoleum for Emperor Menelik II, his wife Empress Tayitu and his Daughter Empress Zewditu.

The church in Tea’ka Negest Bata LeMariam Monastery (A church in commemoration of the Presentation of St. Mary into the Holy Temple) is located adjacent to the Grand Palace in Addis Ababa, Ethiopia.

Such a beautiful Church of huge historical importance is near collapse at this moment in time and is in immediate need of restoration work. Due to its old age and lack of maintenance the dome has been leaking and the Cupola (“Gulilat”) on top of it is in danger of falling off.

This is a call for all Ethiopians and all preservationists of the world to participate in saving this magnificent and Historic building from further collapse. Please donate, as much as you can to support this blessed and uniquely rewarding restoration work.

We would like to thank you in advance to support such a blessed cause and taking part in donating and sharing the link to other friends and families. 

May Our LORD Bless us all. 

The UK fundraising committee. 


Donations

 See top
 • Tsion Haileselassie 
  • £100 
  • 1 mo
 • እህተማርያም ግርማ 
  • £50 
  • 1 mo
 • Anonymous 
  • £50 
  • 1 mo
 • Anonymous 
  • £200 
  • 1 mo
 • Given to Kesis Dirshaye Today 
  • £50 
  • 1 mo
See all

Organizer and beneficiary

UK Beata Monastery Restoration Fundraising Committee 
Organizer
London, Greater London, United Kingdom
Teaka Negest Bata LeMariam Monastery Addis Ababa, Ethiopia 
Beneficiary
 • #1 fundraising platform

  More people start fundraisers on GoFundMe than on any other platform. Learn more

 • GoFundMe Guarantee

  In the rare case something isn’t right, we will work with you to determine if misuse occurred. Learn more

 • Expert advice, 24/7

  Contact us with your questions and we’ll answer, day or night. Learn more