Main fundraiser photo

Help Babies, Kids,Children&their mothers in Prison

በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ 110,000 የሚሆኑ በሕግ ጥላ ሥር የሚገኙ የቅድመ ምርመራ እና የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባቸው እስረኞች እንዳሉ ያውቃሉ?

የአንድ ሰው ዕለታዊ በጀት 20 ብር (0.50 ዶላር) መሆኑንሳ?

በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ እስር ቤት ጎብኝተውስ ያውቃሉ? ለግንዛቤ ይሆን ዘንድ እባክዎን የሚከተለውን ጽሑፍ ያንብቡ።


እርስዎ 1 ዶላር ከለገሱ ለሁለት እስረኞች ዕለታዊ በጀትን ይሸፍናል ፡፡

10 ዶላር ከለገሱ ወላጅ/ አሳዳጊ በእስር ላይ ለሚገኝ/ትገኝ ለአንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ዓመታዊ የትምህርት ቤት ፍጆታ ቁሳቁሶችን ይሸፍናል ፡፡


Do you know there are about 110,000 pre-trial detainees and prisoners in Ethiopia? The daily budget per person is 20 ETB (0.5 USD). Have you ever visited a prison in Ethiopia? Please read the following text.

If you donate 1 USD, it covers a daily budget for two prisoners. If you donate $10, it covers annual school materials for one elementary school student whose parent/guardian is in prison.


ስምንት/ዘጠኝ ዓመታት ገደመ አቶ ተመስገን ታደሠ፣ አቶ ከበደ እና አቶ ዮሐንስ አንዲት የታሰረች ወጣት ሴት በሐዋሳ እስር ቤት ጎብኝተው ነበር ፡፡ ወጣቷ የከበደ እህት ነበረች ፡፡ ተመስገን እና ጓደኞቹ ለወጣቷ የተወሰኑ የግል ንፅህና መጠበቂያዎችንና ሌሎች መሠረታዊ የሆኑ አቅርቦቶችን ከለገሱ በኋላ የእስር ቤቱን ሰራተኞች መደበኛ ያልሆነ ቃለመጠይቅ በመጠየቅ በአጠቃላይ ሴት እስረኞች ስላሚያጋጥሟቸው በርካታ ችግሮች ምን እንደሆነ ተረዱ ፡፡

እስረኞቹ ሴቶች እንደ ምግብ፣ አለባሳት፣የግል ንፅህና መጠበቂያ አቅርቦቶች እና ሌሎችንም መሠረታዊ ነገሮች እንዳላገኙ ግልፅ ነበር ፡፡

ከእነዚህ እስረኞች መካከል አንዳንዶቹ ጡት የሚያጠቡ ሌሎች ደግሞ ነፍሰ ጡሮች ነበሩ፡፡ በወንጀል ተጠርጥረው ከመያዘቸው በፊት ነፍሰጡር የነበሩና እዚያው ማራሚያ ተቋም ውስጥ የወለዱ እናቶች፣ከእናቶቻቸው ተለይተው ሰፈር ብቀሩ ጠባቂ ስለማይኖር ከእናቶቻቸው ጋር አብረው በእስር ቤት የሚቆዩ ህፃናትም ነበሩ። የእስር ቤት ክፍሎች በቂ አለመሆንና እና ለህፃናትም ተገቢ የሆነ ተመጣጠኝ ምግብም አልነበረም ፡፡

ተመስገን እና ጓደኞቹ(አቶ ከበደ እና አቶ ዮሐንስ) ሴት እስረኞችና ልጆቻቸው በማራሚያ ተቋም ቆይታቸው ወቅት በወህኒ ቤት እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መቆየታቸውን ተገንዝበዋል ፡፡

ከላይ የተገለጸው ክስተት ፍቅርን ማጋራት በጎ አድራጎት ድርጅት የተሰኘው አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እንድመሠረት/እንዲቋቋም መነሻ ሆኗል።


ግባችን እስረኞች ጤናማ ሕይወት እንዲኖራቸው መርዳት ነው ፡፡ ዒላማ የምናደርጋቸውም ሴት እስረኞች እና ልጆቻቸው ናቸው ፡፡

ስለዚህ፦

1ኛ. እናቶቻቸው ነፍሳጡር ሆነው ከመግባታቸው የተነሳ በማራሚያ ተቋም ውስጥ የተወለዱ ህፃናትና እናቶቻቸውን፣

2ኛ. ከወላጆቻቸው ብለዩ ጠበቂ ስለሌላ ከእናቶቻቸው ጋር እስር ቤት የሚቆዩ ህፃናትና ታዳጊዎች፣

3ኛ. ወላጆቻቸው እስር ቤት በመሆናቸው ከትምህርት ገበታቸው ወደ ኁዋላ የቀሩ ወይም ትምህርት አቋርጠው ጎዳና የሚወጡ ህፃናትን አንዲንታደግ ፍቅርን ማጋራት በጎ አድራጎት ድርጅት ጥሪ ያቀርባል።


ድርጅቱ የሚንሰጣቸው አገልግሎቶች በዝርዝር ሲታይ፣

• አልባሳት ፣ የሴቶች እና ህፃናት የግል ንፅህና መጠበቂያዎች፡፡

• ለእስረኞች እና ለልጆቻቸው የተመጣጠና ምግብ ማቅረብ፣

• ወላጆቻቸው / አሳዳጊዎቻቸው ለተታሰሩ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ማሟለት፣

• ለእስር ቤት ቤተመፃህፍት መጻሕፍት ማደረጀት፣

• የወንጀል ባህሪ መዘዞችን በተመለከተ ሥልጠናዎችን መስጠት፣


ስለዚህ የወንጀል መጠንን ለመቀነስ እና እስረኞች ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉና ውጤታማ የህብረተሰብ አባላት እንዲሆኑ አስተዋፅኦ ለማበርከት ጥረት እያደረግን ነው ፡፡

ወንጀልን በጋራ መከላከላችን እንደተጠበቀ ሆኖ በወንጀል ተጠርጥሮ ማራሚያ የገባ ሁሉ ወንጀለኛ እንዳልሆነ በመገንዘብ ቀልጣፋና ትክክለኛ የፍርድ ሂዳት እንድሰፍንም በጋራ እንሠራለን!!


እባክዎን ይለግሱ!! የእርስዎን እርዳታ የሚፈልጉትን ለመርዳት ልብዎን ከፍተው እጅዎን ይዘርጉ!!

እናመሰግናለን!!


Do you know there are about 110,000 pre-trial detainees and prisoners in Ethiopia? The daily budget per person is 20 ETB (0.5 USD). Have you ever visited a prison in Ethiopia? Please read the following text. If you donate 1 USD, it covers a daily budget for two prisoners. If you donate $10, it covers annual school materials for one elementary school student whose parent/guardian is in prison.

Nine years ago, Temesgen and his friend (name?) visited a detained young lady at the Hawassa Prison. The young lady was Friend’s (mane) sister. After Temesgen and his friend (name?) donated some personal toiletries to the young lady, they asked the prison staff and learned about the vast problems faced by women prisoners. It was evident that the women prisoners did not have access to feminine hygiene products such as tampons, pads, period underwear. Some of those women prisoners were breastfeeding while others were pregnant. There was no enough and appropriate food for such vulnerable segments of the prison population. Temesgen and his friend (name) realized that the women prisoners stayed inside their prison cells during their menses because of a lack of pads.

That incident described above was the starting point of our NGO Sharing love….. Our goal is to help prisoners have a healthy life. Our target populations are women prisoners and their children. We provide:

• clothing, toiletries, feminine and personal hygiene products to prisoners.

• food items to prisoners and their children

• educational materials to students whose parent/parents are imprisoned

• books for prison libraries

• training about consequences of criminal behavior

We intend to contribute towards reducing the crime rate and helping prisoners integrate back into society to become productive members of

society.

Please donate and help us help those in dire need!

Thanks!










Fundraising team: Sharing LoveCharitable Organization (2)

Kebede Ergudo
Organizer
Raised $750 from 3 donations
Aurora, CO
Kifle Jikamo
Team member

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.