Main fundraiser photo

ALEN (አለን!) Amhara Support

Tax deductible
የብሄር ማንነትን መሰረት ያደረገ መጠነ ሰፊ ጥቃትን ተከትሎ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ብሄር ተወላጆች ህይወታቸውን ለማዳን ከመኖሪያ ቀያቸውን በግፍ ተፈናቅለው በተጠለሉበት ዳስ ውስጥ የቤተሰቦቻቸውን እልቂት ያየ አይናቸው በእንባ ተውጦ እንደቆሻሻ ታፍሰው በተቀበሩ ዘመዶቻቸው መሪር ሀዘን ተቀምጠዋል:: ታይቶም ሆነ ተሰምቶ በማይታወቀው በዚህ ለከት የለሽ ግፍ ብዙዎች እጅግ አረመኒያዊ በሆነ ሁኔታ መተኪያ የሌላት ውድ ህይወታቸውን ሲያጡ በርካቶች ለእረጅም ዓመታት ለፍተው እና ጥረው ግረው ያፈሩትን ሀብት እና ንብረት በአንድ ጀንበር አጥተው ከተደገሰላቸው እልቂትም በተአምር አምልጠው በገዛ ሀገራቸው ላይ ስደተኛ ሆነዋል:: 

እነዚህን ተፈናቃይ ወግኖቻችንን ለመደገፍ ዓለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ስብስብ "አለን!" በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብሮችን ቀይሶ ድጋፍ ማሰባሰብ የጀመረ ሲሆን እርስዎም በእዚህ ሰብዓዊ እና ወገናዊ ድጋፍ ላይ የበኩልዎን አስተዋጽኦ በማድረግ በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችንን አለኝታ እንዲሆኑ ታሪክ የማይዘነጋው ጥሪ ቀርቦሎዎታል:: 

በግፍ ተፈናቅለው ለተደራቢ ችግር የተጋለጡ ንጹሀን ወገኖቻችንን እየደገፍን ማንነትን ኢላማ ያደረገ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም እንታገላለን!

የአለን! ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ

Donations 

  • Beth Christos
    • $100 
    • 3 yrs

Organizer

Alen Amhara
Organizer
Collierville, TN
Moresh Wegenie Amara Organization Inc
 
Registered nonprofit
Donations are typically 100% tax deductible in the US.

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.