Main fundraiser photo

ለዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና የካህናት ማሰልጠኛ እርዳታ

Donation protected
የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብር ኤል ገዳምና መንፈሳዊ ኮሌጅን ከ አደጋ እንታደግ።

ገዳማችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሰፊ አስተዋጾኦ አለው፡፡

1.   ከገዳማት ሥሪት ውስጥ ዋናውን የአንድነት ገዳም ሆኖ የተመሠረተ እንደሆነ እእንደ አብነት ማሳያ ማድረግ ይቻላል፤ 
2.   ለቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገግሎት ሁለገብ የሆኑ በርካታ ሊቃነ ጳጳሳትን፣ቆሞሳት፣ ቀሳውስትን፣መምህራነ ወንጌልን ያስገኘ፤
3.  ወላጅ የሌላቸውን ሕፃናት ከያሉበት ሰብስቦ በዘመናዊም ይሁን በመንፈሳዊ ትምሕርት አልቆ ለትልልቅ ደረጃ ያበቃ፤
4.  እንዲሁም በብዙ የቤተክርስቲያን አገልግሎት የደከሙ አረጋውያን የሚጦሩበት፤
5.  በአሁኑ ሰዓትም ካለው እንቅስቃሴ የተነሣ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወስኖ ካሉት መንፈሳውያን ኮሌጆች አንዱ አንዲሆን የተወሰነለት ታላቅ የትምህርትና የመንፈሳዊ ሕይወት ማዕከል ነው፡፡

ይሁንና ዘንድሮ በ2012 መጨረሻ ላይ በጣለው ዝናብ በፎቶና በቪድዮው ላይ ለማሳየት እንደተሞከረው ገዳሙ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ አደጋ ውስጥ ነው፡፡
ይህንን ጉዳይ እኛ በገዳሙ ፍሬ በረከት ያገኘን ደቀ መዛሙርት የቅውቀት ምንጭ የሆነው ገዳማችን እንዲህ ሆኖ በማየታችን እጅግ ልባችን በመነካቱ የምንችለውን በየአቅማችን የምንችለውን በማድረግ በቀረው ደግሞ እያንድ አንዱ ኦርቶዶክሳዊ ምእመን የመጠበቅና የማስቀጠል ግዴታ ስላለበት ሁሉም ችግሩን አውቆ ክርስቲያናዊ ግዴታውን እንዲወጣ ይህንን አቅርበናል፡፡ የደረሰው ጥፋት አጠገቡ ያለው የዝዋይ ሐይቅ የዝናብ መጠን በመጨመሩ ምክክንያት መግባት መውጣት በማይቻልበት ደረጃ የገዳሙን ይዞታ ሙሉ ለሙሉ ይዞታል፣ወቅታዊ የሆኑ ለገዳማውያኑ ቀለብ የሚያግዙ ስንዴ ፣ገብስ፣በቆሎ ምርቶች በሙሉ ወድመዋል። ቋሚ ተክሎች የነበሩ የብርቱካን የሙዝና የፓፓያ ተክሎች በውሃው ተውጠዋል የገዳሙ ታዳጊ ሕፃናትና ደቀመዛሙርት እንዲሁም መምህራን መንኮሳት አባቶች እንዲሁም አረጋውያን መውጫ መግቢያ በማጣት ላይ ይገኛሉ።  አስቸኳይ መፍትሔ ካለተበጀለት ከዚህም በላይ የከፋ ሊሆን ይችላል፡፡

 እርዳታ የሚያስፈልገው  አሸዋና ኮረት በማስጫን መንገድ ማውጣት፣ቢቻል እንዳይብስ ውሓውን መገደብ፣ከዚያም የገባውን ውሓ ብዙ የውኃ መምጠጫዎችን በመጠቀም ወደ ሐይቁ መመለስ፣ከዚያም ውኃ ወለድ በሽታዎች እንዳይከሰቱ መከላከያ ማድረግ፣በመጨረሻም ከእንግዲህ እንደዚህ ዓይነቱ አደጋ እንዳይፈጠር መደረግ ይኖርበታል። ለዚህም በባለሙያዎች የተጠኑ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው እንዲተገበሩ የሚያስችል ከፍተኛ ገንዘብ ያስፈልጋል። በመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከታችሁ ሁሉ ይህንን ታላቅ ገዳም ለማዳንና በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ የነበሩትን ውጥን ተግባራት ከግብ ለማድረስ የበኩላችሁን ኃላፊነት ትወጡ ዘንዱ በታላቁ አባት አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕና በሥራው ባለቤት በእግዚአብሔት ስም አደራ እንላለን።


 አስተባባሪ ኮሚቴው



Donate

Donations 

  • KIDIST DEMISSIE
    • $100 
    • 3 yrs
  • Tsega Diko
    • $100 
    • 3 yrs
  • Mekdes Woldu
    • $160 
    • 3 yrs
  • Abba Philipos Kebede
    • $100 
    • 3 yrs
  • Abba Philipos Kebede
    • $50 
    • 3 yrs
Donate

Organizer

Melake Tsion Kesis Belachew Dargie, Kesis Ashenafi Duga and Abba Philipos Kebede
Organizer
Alexandria, VA

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.