Main fundraiser photo

Wolaita Dicha Support Campaign

Donation protected

የወላይታ ዲቻ ቡድን በአፍሪካ እና በአለምአቀፍ መድረክ ገናና ስም ያለውን የግብጹን ዛማሌክ ቡድን ድል በማድረግ ለሀገራችን እግር ኳስ ተስፋ ከመፈንጠቁም በላይ የኢትዮጵያዊያን የድል አድራጊነት መንፈስን ቀስቅሷል። ይሄው ቡድን በቀጣይ ተጠናክሮ ባንዲራችን ከፍ እንዲያደርግና ለሌሎች ነባር ቡድኖችም ሆነ ለታዳጊዎች አርአያ እንዲሆን የሁላችን ድጋፍ ያስፈልገዋል። ከዚህ በፊት በኢንተርናሽናል ውድድር ተስፋ ፈንጥቀው የነበሩ የክልል ክለቦች በድጋፍ ማነስ ብዙም ሳይጓዙ ቀርተዋል። በኢንተርናሽናል ውድድር ጥሩ ውጤት ለማምጣት ከተሰጥኦ እና ተነሻሽነት ውጪ ልምድ ይጠይቃል። ድጋፍ የሌለው ቡድን ልምድ ለማዳበር የወዳጅነት ጨዋታ ማድረግ ያቅተዋል። በዚህ አመት የታዩ ተጫዋቾች በሚመጣው አመት የገንዘብ አቅም ወዳላቸው ቡድኖች ሲዘዋወሩ ቡድኑ ኢንተርናሽናል ልምድ ሊያዳብር ይቅርና እራሱን በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማቆየት ይቸገራል። በመሆኑም ቡድኑ የፈነጠቀው ጮራ በአቅም ማነስ ሳይጎመራ ከከሰሙ ቡድኖች መካከል ከደቡብ ክልል ብቻ እንኳን ወላይታ ቱሳ እና ሃዋሳ ከነማን መጥቀስ ይቻላል። ወላይታ ዲቻን ከዚህ እጣ ፈንታ ለመታደግ ለማንኛውም ሃገር ወዳድ ዜጋ አቅሙ የፈቀደውን ያህል ድጋፍ እንዲያደርግ ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ወላይታ ዲቻ የለኮሰውን ድል አድራጊነት ሳይከስም እናቀጣጥል!
የምንጊዜም ባላንጣችንን ግብጽን በገዛ ሜዳቸው  ባንዲራችንን ያነሳልንን ቡድን አላማ እናንሳ!
ዲቻ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት!


ኑናራ ዲያጌ ኡባ ጦንያጋ!


The Wolaita Dicha Football Club is an Ethiopian soccer team based in the Southern city of Wolaita Sodo. Recently this club with very humble means bested the likes of Zamalek of Egypt in the CAF Confederation Cup. Often such small town teams fizzle out after a year or two for lack of resources. They can’t arrange for necessary international friendlies that can help them gain experience. Instead of progressing in international games they may even be relegated from national leagues as players desert it for greener pastures in bigger cities. The purpose of this fundraiser is to generate money to support the Wolaita Dicha Football Club. We hope that this will motivate the club to progress in the current CAF Confederation Cup as well as strengthen it for future seasons. We appreciate any and all help you can give. Please donate and spread the word.

Donate

Donations 

  • Wondrad Lemma
    • $50 
    • 6 yrs
Donate

Organizer

Wolaita Dicha America
Organizer
Washington D.C., DC

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.