የወንጌላዊ ታምራት ገብሬን ቤተሰብ በመርዳት የመንግስቱን ስራ የመካፈል ጥሪ!!
የተፈጠረበትን ትክክለኛ ተልዕኮ አውቆ እና አላማውን ግብ አድርሶ የሄደ ዘመናችን የወንጌል ጀግና ወንጌላዊ ታምራት ገብሬ! ወንጌላዊው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለብዙ አመታት በቋሚነት በሙሉ ወንጌል እና በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ሲያገለግል የቆየ ሲሆን በዋናነት በወንጌል ስርጭት በሚሰራበት መስሪያ ቤት: በየመንገዱ : በየለቅሶ ቤት በህዝብ ማመላልሻ ትራንስፓርት : በየካፊዎቹ እየተገኙ ስለወንጌል መመስከር የመጀመሪያ እና የዕለት ተግባሮቹ ሲሆኑ ለብዙዎች ነፍሳት መዳን ምክንያት ሆኗል:: ወንጌላዊው ቅድሚያ ለሚሰጠው የሰማያዊው ተልዕኮ እራሱን አሳልፎ ከመስጠቱ የተነሳ ዋናውንና የዘላለም ቤቱን ሰርቶ ሲጨርስ ለምድራዊው ህይወቱ ያን ያህል ዛሬን ከመኖር ያለፍ እንቅስቃሴ አልነበረውም:: ግን በአጋጣሚ አባቱ " ዛሬ ወደኔ ትመጣለህ .." የሚለውን የከበረ ጥሪ ተከትሎ የቀረችውን በሰአታት የምትቆጠር ጊዜ ለወገኖቹ እና ለቤተሰቦቹ "..በወንጌል እንዳታፍሩ.." የሚል ማሳሰቢያ እና ማስጠንቀቂያ በማስተላለፍ : ጉዞ እንደሚጠብቀው እንደ ቸኮለ በመንገር ተሰነባብቷቸው እያዩት ወደ ተዘጋጀለት ዘላለማዊ ቤቱ እና አባቱ እቅፍ ሄደ:: ይህ ሲሆን ግን ባለቤቱ እና ከአብራኩ የወጡት ሶስቱ ሴት ልጆቹን ስለ ወንጌል አደራ ከማለት ውጭ ምንም ያወርሳቸው ንብረት አልነበረም:: ዛሬ የዚህ ጀግና ቤተሰብ የኛ የወገኖቻቸውን እርዳታ ይፈልጋሉ:: እርግጥ ነው እግዚአብሔር ማኖር ያውቅበታል ባለውለታውን ይረሳ ዘንድ ሰው አይደለም:: እኛ ግን ቅዱሳን: የተቻለንን ሁሉ በማድረግ ከዚህ ቤተሰብ ጎን እንድንሆን እና በዚህም በመንግስቱ መታሰብ ይሆንልን ዘንድ ዘሮቻችንን እንዝራ ብየ ጥሪየን አቀረብኩ : ብሩካን ናችሁ::
This is to clarify Mrs Tigist, she agree and appointed Pastor Beneyam Aboye to manage and withdrawal the money on behalf of her and her families.
After He withdrawal the money he will deliver the fund directly to her through direct wire transfer.