Main fundraiser photo

24 ዓመታት የታሠሩትን መምህር እንደሥራቸውን እንርዳ

Donation protected
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
+++
ታላቅ የበረከትና ታሪካዊ የድጋፍ ጥሪ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ!!!!! 

" አሁን እንደምታስቡልኝ ........በመከራዬ ጊዜ ተባባሪዎች በመሆናችሁ መልካም አደረጋችሁ"

(ፊልጵ. 4÷ 10- 14)
 

በኢትዮጵያ ላለፉት 24 ዓመታት በግፍ ታስረው በመከራ የሚማቅቁት ሊቁ እንደሥራቸው አግማሴንና ቤተሰቦቻቸውን በገንዘብና በሙያ መርዳት ለነገ የማይባል ግዴታ መሆኑን ማኅበራችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመወያየት ውሳኔ ላይ ደርሷል።

እኚህ የቀለም ቀንድ የሆኑትን መምህር ከእስራት ለማስለቀቅና አስፈላጊውን የሕግ ድጋፍ ለማድረግ፣ በመከራ ስቃይና በሕማም ለሚሰቃዩ ልጆቻቸውና ያለምንም ድጋፍ ሰባት የሊቁን ልጆች ተንከባክበው ላሳደጉና ዛሬም ድጋፍ እያደረጉ ለሚገኙት ባለቤታቸው መጦርያና ድጋፍ ለማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንድንደርስላቸው ጥሪያችንን እያቀረብን እርስዎም  በቀላሉ የሚችሉትን በመለገስ መንፈሳዊና ኢትዮጵያዊ ኃላፊነትዎን እንዲወጡ ይህንን የበረከት ጥሪ እናስተላልፋለን።

ልብ ይበሉ፤ የእርሶ ድጋፍና ርዳታ በምድር የኅሊና እረፍት፣ በሰማይ የነፍስ ርስት የሚያገኙበት ነው። መቆጨት ከተግባር ጋር ለውጥ ያመጣል። ቁጭት ያለተግባር ተሸናፊነትን ያነግሳል። የምንችለውን እናደርጋለን፤ የማንችለውን ደግሞ ሁሉን ለሚያደርግ ለእግዚአብሔር አሳልፈን እንሰጣለን።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የሰሜን አሜሪካ ማኅበረ ካህናት አንድነት
Donate

Donations 

  • Getachew Gebremichael
    • $30 
    • 6 yrs
Donate

Fundraising team: ማኅበረ ካህናት ዘሰሜን አሜሪካ (2)

AWEKE SIDLEL
Organiser
Seattle, WA
Aweke SIDLEL
Beneficiary
Kesis Dereje Seyoum
Team member

Your easy, powerful and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help straight to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.