Main fundraiser photo

VOLUNTEER TRIP

Donation protected
ብዙዎቻችን እንደምናውቀው በዚህ በላስ ቬጋስ ነዋሪ የሆነው ወንድማችን አቶ  ምኅረት ዓለሙ ለማያውቃቸው ሰዎች ሁሉ እጅግ የሚያስገርም በጎ ምግባራትን ሲሰራ የኖረ ነው። ለአብነት ያክልም የማያውቃቸውንና ከ 13 ቤተሰቦች በላይ የሆኑ ሰዎችን ከተለያዩ ሃገራት አጠቃላይ ወጪያቸውን በመሸፈን ሙሉ እስፖንሰር  በመሆን  ከማስመጣት አልፎ ባለ ሁለትና ሦስት ክፍል አፓርትመንት በመከራየት፤ የሚያስፈለጋቸውንም ወጪ ሁሉ በራሱ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ እየሸፈነ  እራሳቸውን እንዲችሉ የረዳቸው ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ይገኛሉ። አንዳንድ ሰዎች  ሆስፒታል ተኝተው ደም ሲያስፈልጋቸው ባያውቃቸውም ደሙን በነጻ ለግሷል። አንዲት የልጆች እናት እህታችን ሁለቱም ኩላሊቶቿ መስራት ባቆሙበት ጊዜ በአካል ሳያውቃት አንድ ኩላሊቱን ለመስጠት አጠገቧ ተገኝቷል። ሰውን ለመርዳት ገንዘብ ባጠረው ጊዜ እንኳ መኪናውን እስከ መስጠት ደርሷል። ወንድማችን ምህረት ባለው የቪዲዮና የፎቶ ግራፍ ሙያ ያላገለገለው ግለሰብና ማኅበረሰብ የለም። በአገር ቤትም በርካታ ወላጅ አልባ ህጻናትንና እንዲሁም ጧሪና ቀባሪ የሌላቸውን አረጋውያን ለበርካታ ዓመታት ሲረዳና ሲደጉም ኖሯል።

   ዛሬ ላይ ግን ወንድማችን ምኅረት  በደረሰበት ከፍተኛ የጀርባ አጥንት መጎዳት ምክንያት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛል።እነዚህ ለጋሽ እጆች አጥረውት ለራሱ መሆን ተስኖታል። እነዚያ ዘር፣ ቀለምና ሃይማኖት ሳይመርጡና ሳይሰለቹ ሰውን ሁሉ ለመርዳት የሚሮጡ እግሮቹ ዛሬ መንቀሳቀስ ተስኗቸዋል።አልጋው ላይ እንኳን መገላበጥ ተስኖታል። ስለዚህ በአካል ተገኝታችሁ መርዳት ያልቻላችሁ ሁሉ በዚሁ ድህረ ገጽ ላይ ይህንን ወንድማችንን ትረዱት ዘንድ መልዕክቱንም ታስተላልፉልን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ለተጨማሪ መረጃ  በ [phone redacted] ,  ይደውሉ።

Organizer

Mihrete Alemu
Organizer

Your easy, powerful, and trusted home for help

  • Easy

    Donate quickly and easily.

  • Powerful

    Send help right to the people and causes you care about.

  • Trusted

    Your donation is protected by the  GoFundMe Giving Guarantee.